1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ተጨማሪ የርዳታ ጥሪ ለኢትዮጵያዉያን

ሐሙስ፣ የካቲት 3 2008

የሴቭ ዘ ችልድረን ሐላፊዎች አሁን እንዳስታወቁት ለችግረኛዉ ምግብ ለማቅረብ የ245 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ ርዳታ ባስቸኳይ ያስፈልጋል።

https://p.dw.com/p/1HtvT
ምስል Reuters/E. Blair

[No title]

ኢትዮጵያን በመታዉ ድርቅ ለረሐብ ለተጋለጠዉ ሕዝብ መርጃ ተጨማሪ እርዳታ እንዲሰጥ ዓለም አቀፉ የሕፃናት መርጃ ድርጅት ሴቭ ዘ ችልድረን ተማፀነ።ለምግብ እጥረት ለተጋለጠዉ ከአሥር ሚሊዮን ለሚበልጠዉ ኢትዮጵያዊ መርጃ ለጋሾች 1,4 ቢሊዮን ዶላር እንዲሰጡ የኢትዮጵያ መንግሥት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በቅርቡ ጠይቀዉ ነበር።የሴቭ ዘ ችልድረን ሐላፊዎች አሁን እንዳስታወቁት ለችግረኛዉ ምግብ ለማቅረብ የ245 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ ርዳታ ባስቸኳይ ያስፈልጋል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ ዝርዝር ዘገባ አለዉ።

ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ