1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ተፈናቃዮች ተመለሱ

ዓርብ፣ መጋቢት 13 2011

ከምሥራቅ ሐረርጌ ከባቢሌ ወረዳ ተፈናቅለዉ 8 ወር ያሕል በተለያዩ አካባቢዎች ጊዚያዊ መጠለያ ዉስጥ ሠፍረዉ የነበሩ አብዛኞቹ ተፈናቃዮች ወደየቀየዉ መመለሳቸዉን የአካባቢዉ ባለሥልጣናት አስታዉቀዋል

https://p.dw.com/p/3FW8K
Äthiopien Flüchtlinge kehren in Dörfer zurück
ምስል DW/Mesay Teklu

ተፋናቆዮች ተመለሱ፣ ቤት ግን የላቸዉም

በኢትዮ-ሶማሌና በኦሮሚያ አዋሳኝ ድንበሮች ከ2009 ማብቂያ ጀምሮ በተደረጉ ግጭት ከቤት ንብረታቸዉ የተፈናቀሉ ሰዎች ወደየቀያቸዉ እየተመለሱ ነዉ።በተለይ ከምሥራቅ ሐረርጌ ከባቢሌ ወረዳ ተፈናቅለዉ 8 ወር ያሕል በተለያዩ አካባቢዎች ጊዚያዊ መጠለያ ዉስጥ ሠፍረዉ የነበሩ አብዛኞቹ ተፈናቃዮች ወደየቀየዉ መመለሳቸዉን የአካባቢዉ ባለሥልጣናት አስታዉቀዋል።የምስራቅ ሐረርጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ፅ/ቤት ለDW በስልክ እንደገለፀው መጠለያ ከነበሩ 40 ሺሕ ዜጎች አብዛኞቹ ወደ ቀድሞ መኖርያ ተመልሰዋል።ፅፈት ቤቱ እንዳለዉ ቀሪዎቹ ተፈናቃዮች ባገባድደነዉ ሳምንት ማብቂያ  ሙሉ በሙሉ በየቀየቸዉ ይገባሉ።ይሁንና የአብዛኞቹ ተፈናቃዮች መኖሪያ ቤቶች በመፍሩ ቤቶቹን ለመጠገን የአካባቢዉ መስተዳድር ድጋፍ እንዲደረግለት ጠይቋል። 

መሳይ ተክሉ 

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ