1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቱኒዚያ፤ የፀረ-ፅንፈኝነት ዘመቻ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 23 2008

ለወጣቶቹ ግልፅ መሆን አለበት። ከፅንፈኛዉ አስተሳሰብ የተሻለ ሌላ አስተሳሰብ እንዳለ አድርጎ የሚቀርብ መሆን የለበትም።ጥሩ እስላም ምንማለት እንደሁ ለወጣቱ ሲነገረዉ ወጣቱ አምኖ የሚቀበለዉ መሆን አለበት

https://p.dw.com/p/1Ixp7
ምስል picture-alliance/dpa

[No title]

30 ሺሕ የዉጪ ሐገር ዜጎች ኢራቅና ሶሪያ ዉስጥ ከመሸጉ ፅንፈኛ ታጣቂ ቡድናት ጋር ወግነዉ ይዋጋሉ ተብሎ ይገመታል።በባለሙያዎች እንደሚሉት ከዉጪ ሐገር ተዋጊዎቹ መካከል አንድ-አምስተኛዉiየቱኒዚያ ዜጎች ናቸዉ።ከነዚሕ ዉስጥ ደግሞ በመቶ የሚቆጠሩ ወደ ሐገራቸዉ ተመልሰዋል መባሉ ለቱኒዚያ መንግሥት እንደማስጠንቀቂያ ደወል ነዉ የታየዉ።የቱኒዚያ መንግሥት በበኩሉ የሐገሪቱ ወጣቶች ፅንፈኞችን እንዳይቀላቀሉ ለመከላከል ይረዳል ያለዉን የፀረ-ፅንፈኝነት ዘመቻ ጀምሯል።

የቱኒዚያዉ የሐይማኖት ጉዳይ ሚንስትር መሐመድ ኻሊል እንደሚሉት «ዘመቻዉ ከዓመታት በፊት መጀመር ነበረበት። ግን እራሳቸዉ የሚንስትርነቱን ሥልጣን የያዙት ባለፈዉ ጥር ነዉ።የፅንፈኝነት አስተሳሰብን በአስተሳሰብ የመዋጋት ዘመቻዉም ከትላልቅ ሥራዎቻቸዉ የመጀመሪያዉ ነዉ።

«በተለያዩ የሐገሪቱ ግዛቶች ከሚኖሩ ወጣቶች ጋር በቅጥታ እንገናኛለን።ግልፅ ዉይይት ማድረግ እንፈልጋለን።ለወጣቶቹ ትክክለኛዉን የእስልም (መርሕ) እንዲያስረዱ ፕሮፌሰሮችን፤ ሰባኪዎችን፤ኢማሞችን እንልካለን።»

ለሚንስትሩ «ትክለኛዉ እስልምና» ማለት መቻቻልን እና ግልፅነትን ያካተተ ነዉ።ከመንፈሳዊም ሆነ ዓለማዊ ምሁራን ጋር የሚደረገዉ ዉይይት ወጣቶችን ከፅንፈኛ አስተሳሰብ እና ከISIS ርዕዮተ-ዓለም ለመከላከል ያለመ ነዉ።ዘመቻዉ በእስር ቤቶችም ያነጣጠረ ነዉ።ሚንስትሩ እንደሚሉት የእስር ቤቱ ዘመቻ በተለይ በአሸባሪነት የተፈረደባቸዉ እስረኞች ሌሎችን እንዳያጠምዱ ለመነጠል ያለመ ነዉ

Zaytuna Moschee Imam Krise Islam Tunesien
ምስል Tarek Guizani

በዘመቻዉ እስካሁን ዉጤትም ሚንስትሩ የረኩ ይመስላሉ። ለፅንፈኞች የተጋለጡ ወጣቶች ይኖሩበታል ተብሎ በሚጠረጠረዉ የቱኒስ ክፍለ-ከተማ በቅርቡ የተደረገዉን ዉይይት፤ ሚንስትሩ፤ የበጎ ዉጤት አብነት ያደርጉታል።በወይይቱ 30 ሰዎች ተሳትፈዉ ነበር።ተሳታፊዎቹ በሙሉ ግን ከአርባ ዓመት በላይ ናቸዉ።«ወጣቶቹ የታሉይጠይቃሉ ሰሚራ።

«ዛሬ እዚሕ አንድም ወጣት አላየሁም።የታሉ ወጣቶቹ? ለነሱ ያለኝ ክብር እንደተጠበቀ ሆኖ ተሳታፊዎቹ በሙሉ ሽማግሌዎች ናቸዉ።እራሳቸዉን እንዲከላከሉ ወጣቶቹ መሳተፍ ነበረባቸዉ።(ዉይይቱ) የተደረገዉ ሁለተኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት ቢሆን ኖሮ ወጣቶቻችንን ምግኘት በተቻለ ነበር።»

ለዘመቻዉ የቴሌቪዥንና የራዲዮ አየር ሰዓት ተይዞለት «መጪዉ ጊዜ የተሻለ ነዉ» ዝግጅት ይሰራጭበታል።በአምደ መረብም የሚንስሩን መልዕክት የያዙ ቪዲዮዎች ተሰራጭተዋል።ዉይይት እንደሚደረግ የሚገልፁ መረሐ-ግብሮች አሉ።ዝርዝር መረጃ ግን የለም።ባለሙያዎች ባንፃሩ ዘመቻዉ ጥንቃቄ ያሻዋል ባዮች ናቸዉ።አልጄሪያዊቷ-ፈረንሳዊት ዱንያ ቦዛር እንደሚሉት በዘመቻዉ ወላጆች መሳተፍ አለባቸዉ።

Tunis
ምስል picture alliance / Dallas & John Heaton/Robert Hard

«ለወጣቶቹ ግልፅ መሆን አለበት። ከፅንፈኛዉ አስተሳሰብ የተሻለ ሌላ አስተሳሰብ እንዳለ አድርጎ የሚቀርብ መሆን የለበትም።ጥሩ እስላም ምንማለት እንደሁ ለወጣቱ ሲነገረዉ ወጣቱ አምኖ የሚቀበለዉ መሆን አለበት።ብዙ ሐገራት ይሕን ባለማድረጋቸዉ ሙከራቸዉ ከሽፏል።ወጣቱ ትክክለኛዉን እስልምና ለማሰራጨት በፈጣሪ ተመርጬያለሁ ብሎ ያምናል።ሌሎቹ በሙሉ እምነታቸዉ የታሳከረ ነዉ ብሎ ያስባል።ወጣቶቹን መያዝ የሚቻለዉ ስሜታቸዉ በትክክል ሲታወቅ ነዉ።ከወላጆቻቸዉ ጋር ሥንሰራ የተማርነዉ ይሕንን ነዉ።»

ወይዘሮ ዱንያ ፈረንሳይ ዉስጥ በስልክ አማካይነት የምክር አገልግሎት ይሰጣሉ።ወጣቶቹን የሚመክሩት ከወላጆቻቸዉ በሚሰጣቸዉ ጥቆማና መረጃ ላይ ተመስርተዉ ነዉ።

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ