1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ታሪካዊው የአረንጓዴዎች ድል በጀርመን

ማክሰኞ፣ መጋቢት 20 2003

እሁድ መጋቢት 18 ,2003 ዓ.ም የጀርመንን የፖለቲካ ይዘት በታሪክ መዝገብ ሰፍሯል ። ከትናንት በስተያ ታሪካዊ ድል የተቀዳጀው የአረንጓዴ ፓርቲ ሊቀመንበር ክላውድያ ሮት እንዳሉት በርግጥም እለቱ የጀርመንን ፖለቲካዊ ሂደት ለውጧል ።

https://p.dw.com/p/RDhP
የአረንጓዴ ፓርቲ አመራር አባላትምስል dapd

በ 2 ፌደራል ክፍለ ሀገር በተካሄደ ምርጫ ከዓመታት በፊት ይሆናሉ ተብለው ያልታሰቡ ውጤቶች ተገኝተዋል ። በደቡብ ምዕራብ ጀርመኑ ፌደራዊ ክፍለ ግዛት በባድን ቩርተንበርግ ምርጫ የአረንጓዴዎቹ ፓርቲ ለመጀመሪያ ጊዜ ለክፍለ ግዛት መሪነት የሚያበቃውን ድምፅ ሲያገኝ ለ 58 ዓመታት ከፌደራል ክፍለ ሀገሩ አመራር ያልተለየው የክርስቲያን ዲሞክራቶች ህብረት ፓርቲ ደግሞ ሥልጣኑን በምርጫ መነጠቅ ግድ ሆኖበታል ። በምዕራብ ጀርመኑ የራይንላድ ፋልትስ ፌደራዊ ክፍለ ግዛት ምርጫ የሶሻል ዲሞክራቶቹ ፓርቲ ከቀድሞ ያነሰ ድምፅ ሲያገኝ የነፃ ዲሞክራቶቹ ፓርቲ ደግሞ የምክር ቤት መቀመጫ እንኳን ማግኘት አልቻለም ። የዛሬው ዝግጅታችን በሁለቱ የጀርመን ፌደራል ክፍላተ ሀገር የተካሄዱት ምርጫዎች ያስገኙትን ታሪካዊ ውጤትና አንድምታውን እንዲሁም አስተምህሮቱን ይዳስሳል ።

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ