1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ታንዛንያና ባህሏ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 16 2005

ምሥራቅ አፍሪቃዊቷ ሀገር ታንዛንያ በተለይ በአገር ጎብኚዎች ዘንድ ፣ እንጎሮንጎሮ እና ሴሬንጌቲ በተባሉት ቦታዎች በሚገኙት የዱር እንስሳትና ዓራዊት ክልሎች ትታወቃለች። ከዛ ባለፈስ የታንዛንያን ባህል ምን ይመስላል?

https://p.dw.com/p/19UFK
Blick auf den Strand von Jambiani an der Ostküste der Insel Sansibar, Tansania. Aufnahme vom Oktober 2004. dpa 8266011
Tansania: Sansibar - Jambianiምስል picture-alliance/dpa

ስምንት ጎረቤት ሀገራት እና የህንድ ውቅያኖስ የሚያዋስኗት ምስራቅ አፍሪቃዊት ሀገር ታንዛንያ ከቅኝ ገዢዋ ብሪታንያ ነፃ የወጣችው እኢአ ታህሳስ 9, 1961 ዓ ም ነበር። በታንዛኒያ ከስድስት ዓመት በፊት በተደረገ የህዝብ ቆጠራ ህዝቧ ከ41 ሚሊዮን በላይ እንደሆነ ተረጋግጧል። በሰሜን ታንዛንያ እና በጠረፍ አካባቢ በርካታ ሙስሊሞች ይኖራሉ። ከህብረተሰቡ ከ30-40 ከመቶው የእስልምና ዕምነት ተከታይ ነው። በዛንዚባር ደሰት እስከ 98 ከመቶው ሙስሊም ነው። በትልቁ የታንዛኒያ ግዛት ደግሞ የክርስትና ዕምነት ተከታዮች ይመረክታሉ። ከ 30-40 ከመቶው ካቶሊኮች ናቸው። በታንዛንያ በአጠቃላይ 128 የተለየያዩ ቋንቋዎችም ይነገራሉ።

Eine tansanische Frau mit einem Kind, aufgenommen am 4.2.2003 in Daressalam auf einer Straße, die zum Flughafen führt.
ምስል dpa - Bildarchiv

ከመቶ ዓመታት በላይም ከአረብ ሀገሮች እና ቀድሞ እንደ ታንዛንያ በብሪታንያ ቅኝ ግዛት ስር ከነበረችው ህንድ ወደ ታንዛንያ የተሰደዱ ሰዎች በሀገሪቱ ይኖራሉ። ብዙ የህንድ ዝርያዎች በሀገሪቱ ስለሚኖሩም የምግብ እና የአሰራር ባህላቸው የሀገሬው አመጋገብ ላይ ይስተዋላል ወይም አስተዋፅዎ አድርጓል ይባላል።

ብዙ ቋንቋ እና ብሔር ስላላት ሀገር ባህል ወ/ሮ ጥሩ ወርቅ ወርቁ ያጫውቱናል። ወ/ሮ ጥሩ ወርቅ በዳሬ ሰላም ሲኖሩ 13 ዓመታት ተቆጥረዋል። እሳቸውም ታንዛኒያዊ ባለቤት እና ሁለት ልጆች አሏቸው።

ስለ ታንዛኒያ አመጋገብ፣ አለባበስ፣ የደስታ እና የሀዘን ጊዜ የመሳሰሉትን ነጥቦች ወ/ሮ ጥሩ አንስተንላቸዋል። ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ