1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ታንዛንያ የመጀመርያዋን ሴት መከላከያ ሚኒስትር ሾመች

ሰኞ፣ መስከረም 3 2014

የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን በሃገሪቱ የመጀመሪያዋን ሴት የመከላከያ ሚኒስትር ሾሙ። የ61 ዓመትዋ ፕሬዚዳንት ባካሄዱት የካቢኔ ሹም ሽር ሦስት ሚኒስሮችንም አባርዋል።

https://p.dw.com/p/40GjW
Tansania Dodoma | Präsidentin Samia Suluhu Hassan
ምስል Habari Maalezo

የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን በሃገሪቱ የመጀመሪያዋን ሴት የመከላከያ ሚኒስትር ሾሙ። ፕሬዚደንት ሳሚያ ትናንት ባካሄዱት የካቢኔ ሹም ሽር መከላከያ ሚኒስቴር ሆነዉ ወደ ስልጣን የመጡት ሴት የመከላከያ ሚኒስትር፤ ባለፈዉ ነሐሴ ወር የታንዛንያዉ መከላከያ ሚኒስትር ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸዉን ተከትሎ ነዉ።  ፕሬዚዳንትዋ ትናንት ባከናወኑት የካቢኔ ለዉጥ በሟቹ ፕሬዚዳንት ጆን ማጊፉሊ ከሃገሪቱ ምክትል የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትርነት የተነሱትን የቀድሞ ባለስልጣን፤ የታንዛንያ የኃይል ሚኒስትር አድርገዉ ሾመዋቸዋል። የቀድሞዉ የታንዛንያ የአካባቢ ጥበቃ ምክትል ሚኒስቴር በጎርጎረሳዉያኑ 2019 ዓመት ፕሬዚዳንት ማጉፉሊን በመተቸታቸዉ ነበር ከስልጣን የተባረሩት። ባለስልጣኑ ከመባረራቸዉም ሌላ ፕሬዚዳንት ማጊፉሊን ይቅርታ እንዲጠይቁ ተገደዉ ነበር። የታንዛንያዋ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን ባካሄዱት የካቢኔ ሹም ሽር የሃገሪቱን የኮምዩኒኬሽን ሚኒስትር ፤ የትራንስፖርት ሚኒስትር፤ እና የኃይል ሚኒስቴር በአጠቃላይ ሦስት የካቢኔ ሚኒስትሮችን ሹመት ማንሳታቸዉም ተነገግሮአል። ፕሬዚዳንቷ አዲስ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግም ሾመዋል። ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ላይ የፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊን ድንገተኛ ሞት ተከትሎ የታንዛንያ የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዚዳንት ሆነዉ ወደ ስልጣን የመጡት  የ 61 ዓመትዋ ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን፤ ለአምስት ዓመታት የየሟቹ ፕሬዚዳንት ጆን ማጊፉሊ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው አገልግለዋል።

አዜብ ታደሰ 

እሸቴ በቀለ