1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ታንዛንያ የወርቅ ማዕድን ሃብት

ማክሰኞ፣ የካቲት 12 2005

ታንዛንያ የተፈጥሮ ማዕድን ባለ ሃብት ናት። በምስራቅ አፍሪቃዊትዋ ሀገር ታንዛንያ 36 ሚሊዮን አዉንስ ወርቅ፤ ማለት ወደ አንድ ሚሊዮን ኪሎ ግራም የወርቅ ክምችት እንዳላት ይገመታል። በዚህም በአፍሪቃ አህጉር በወርቅ ሃብት ክምችት ከደቡብ አፍሪቃ እና ጋና ቀጥላ ሶስተኛ ደረጃን እንድትይዝ ያደርጋታል። ህዝቧ ግን የዚህ ሃብት ተጠቃሚ አይደለም።

https://p.dw.com/p/17gdp
Eine Verkäufern zeigt die Goldsteine, die „Intruder“ auf dem Schuttberg der Goldmine gesammelt haben und die sie weiterverkauft. *** Bilder Deutsche Welle, Julia Hahn, November 2012 Ort: Dorfmarkt von Kewanja, nahe Nord Mara Goldmine, Nord Mara Region, Tansania *** http://en.wikipedia.org/wiki/North_Mara_Gold_Mine North Mara Gold Mine is an open pit gold mine in the Tarime District of the Mara Region of Tanzania. It is operated by African Barrick Gold. It is one of four gold mines African Barrick Gold, a subsidiary of Barrick Gold, operates in Tanzania, the other three being Tulawaka, Bulyanhulu and the Buzwagi Gold Mine. In the financial year 2009, the four operations produced a combined amount of 716,000 attributable ounces of gold.
ምስል DW/J. Hahn

በ1990 ዎቹ መጨረሻ የማዕድን ማዉጫ ቦታዎችን መንግስት በቅናሽ ቀረጥ እና በአነስተኛ ክፍያ የስራ ፈቃድ የማግኘት ዕድልን ለዉጭ ሀገር ኩባንያዎች ከሰጠ በኋላ በበርካታ የማዕድን ማዉጫ ቦታዎች ላይ ፤ በአካባቢዉ ነዋሪዎች እና ድርጅቱን በሚያንቀሳቅሱት አካላት መካከል ዉጥረት ተቀሰቀሰ። በተለይ በኬንያ አዋሳኝ በሚገኘዉ ሰሜናዊ ምዕራብ ታንዛንያ ዳርቻ በሰሜናዊ ማራ አካባቢ ግጭቱ ጠንክሮ ይታያል።

Häuser einer Familie in Kewanja. Hier hat ein junger Mann gelebt, der am 6. November 2012 von einem Polizisten nahe der Nord Mara Goldmine erschossen wurde. *** Bilder Deutsche Welle, Julia Hahn, November 2012 Ort: Dorf Kewanja, nahe Nord Mara Goldmine, Nord Mara Region, Tansania *** http://en.wikipedia.org/wiki/North_Mara_Gold_Mine North Mara Gold Mine is an open pit gold mine in the Tarime District of the Mara Region of Tanzania. It is operated by African Barrick Gold. It is one of four gold mines African Barrick Gold, a subsidiary of Barrick Gold, operates in Tanzania, the other three being Tulawaka, Bulyanhulu and the Buzwagi Gold Mine. In the financial year 2009, the four operations produced a combined amount of 716,000 attributable ounces of gold.
ምስል DW/J. Hahn

በዚህ አካባቢ ያለ ወርቅ ማዕድን ሌላ የሚንቀሳቀስ ነገር የለም፤ ስለዚህም በርካቶች ጥቂት ግራም ወርቅን ለማግኘት ሲሉ ብቻ ህይወታቸዉን አደገኛ ሁኔታ ላይ ሲጥሉ ይታያል። ኬዋንጃ ከተማ ከኬንያ ድንበር በመኪና የግማሽ ሰዓት መንገድ እንኳ አይርቅም። ታንዛንያዊዉ ጁማኔ ቁመቱ ረጅም ካለዉ ቁልል ስብርባሪ ድንጋይ ላይ ሁለት ሜትር ሽቅብ እየቧጠጠ ወጣ። በጁ በያዘዉ ጠርሙስ የቀዳዉን ጭቃ የቀላቀለ ዉሃ ጎንጨት አድርጎ አንድ ግራጫማ ከሆነ የሚያንጸባርቅ ድንጋይ ላይ ረጭቶ በአዉራ ጣቱ ፋቅ ፋቅ እንዳደረገዉ ወርቅማ መልክን በማየቱ ፊቱ በፈገግታ ተሞላ። ከዝያም በፍጥነትያገኘዉን ድንጋይ ስባሪ እሱሪዉ ኪስ ከተተ፤

ጁማነ እራሱን የሚጠራዉ «አጥር ሰባሪ» ሲል ነዉ። ይህ ማለት ማዕድን ማዉጫ ቅጽር ግቢ ያለፈቃድ በመግባት ከአፈር ቁልሉ የሚገኝ ስብርባሪ ማዕድን የሚለቅሙ ሰዎች መጠርያ ነዉ። በዓለም ግዜፉ የወርቅ አምራች ኩባንያ በእንግሊዘኛ ምህፃሩ (ABC)የተሰኘዉ ሲሆን፤ የዚህ ኩባንያ ቅርንጫፍ የሆነዉ ባሪክ ካናዳ የተሰኘዉ ኩባንያ ነዉ። ጁማነ ቅጥር ግቢዉ በመግባት የሚለቅመዉ ኩባንያዉ የማይፈለግ ብሎ ከጣለዉ ድንጋይ ቁልል ዉስጥ በመምረጥ ነዉ። ቢሆንም ኩባንያዉ ይህንን የማይፈለግ ብሎ የቆለለዉን ድንጋይ ማንም እንዳይነካ በዘበኛ ያስጠብቀዋል።

እዚህ ከሶስት አንዱ ነዋሪ ድንጋይ ቁልሉ ላይ እየወጣ የወርቅ ማዕድን በመፈልግ የሚተዳደር ነዉ። አብዛኛዉ ደግሞ ወጣት ነዉ፤ ህፃናትም ይገኙበታል። ጁማነ 20 ዓመቱ እንደሆነ ይናገራል። እዚህ አፈር ቁልል ላይ የሚያገኘዉን የወርቅ ስብርባሪ የሚሸጠዉ በዚሁ በገጠር ባለ ገበያ ዉስጥ ነዉ። በወር ወደ 200,000 ሺሊንግ እንደሚያገኝ ይናገራል፤ ወደ አንድ መቶ ይሮ መሆኑ ነዉ። በዚህም ጁማነ በአካባቢዉ ከፍተኛ መተዳደርያን ከሚያገኙት ነዋሪዎች ይመደባል። በድንገት በዚሁ አፈር ቁልል አካባቢ ፀጥታዉ ደፈረሰ፤ ጁማነ በእጁ እያመላከተ አንድ ጥቁር አረንጓዴ መለዮ የለበሰ ፖሊስ ከሩቅ መምጣቱን ያሳያል።

«ተመልከት! ፖሊስ ሰዎችን እያባረረ ነዉ። ሁሌም በዉጥረት ዉስጥ እያደረገን ነዉ። እዛ ጋ ያለዉም የታጠቀ ፖሊስ ነዉ። ዝም ብለዉ ነዉ ሰዉ ላይ የሚተኩሱት ሰዎች ይሞታሉ! ብዙ ግፍ እየደረሰብን ነዉ»

የማዕድን ማዉጫ ኩባንያዉ አካባቢዉን፤ በታጣቂዉች እንዲሁም በብሄራዊ ፖሊሶች በጥብቅ ያስጠብቃል። ጠባቂዎቹ አስለቃሽ ጋዝ፤ እንዲሁም ሽጉጥ የታጠቁ ናቸዉ። በአካባቢዉ ላይ ብዙን ግዜ የቆሰለ ወይም የሚሞት አይጠፋም። በጎርጎረሳዉያኑ 2012 ዓ,ም ብቻ እንደ መንግስት መገኛኛ ብዙሃን በማዕድን ማዉጫ ኩባንያዉ አካባቢ ስምንት ሰዎች ተገለዉ ተገኝተዋል። በዚህም ያለፈቃድ ግቢ ዉስጥ እየገቡ አፈር ቁልሉ ላይ የወርቅ ስብርባሪ በሚፈልጉ ሰዎች የሚያሰሙት ቁጣ በጣም በርትቶአል።«Baraki ዉስጥ ያሉ ሰዎች ስለሰዉ ግድ የሌላቸዉ ብቻ ናቸዉ። ለዚህ ነዉ እኛ ላይ ልክ ዉሻ እንደሆን ሁሉ አነጣጥረዉ የሚተኩሱብን። ፖሊሶቹም ኩባንያዉ የሚላቸዉን ነገር ብቻ ነዉ የሚያደርጉት። እንደ አሻንጉሊት ኩባንያዉ የፈለገዉን ነገር ነዉ የሚታዘዙት» ከዚህ ማዕድን ማዉጫዉ ከሚያወጣዉ የአፈር ቁልል በስተጀርባ እጅግ ከፍተኛ ገንዘብ ይሰራል። በሰሜናዊ ማራ በሚገኘዉ የማዕድን ማዉጫ ፤ ለብዙ ግዜ ድርጅቱን የሚያስተዳድሩት ኩባንያዎች ተቀያይረዋል። ከጎርጎረሳዉያኑ 2006 ዓ,ም ጀምሮ ABG የተሰኘዉ ኩባንያ ማዕድን ማዉጫዉን በማስተዳደር ላይ ይገኛል። ይህ ኩባንያ በታንዛንያ አስር ዓመታት ያስቆጠረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በታንዛንያ የሚገኙ አራት የወርቅ ማዕድን ማዉጫ ቦታዎችን በማስተዳደር ላይ ይገኛል። እንደ ኩባንያዉ ገለፃ በሰሜናዊ ማራ የማዕድን ማዉጫ ቦታ በአካባቢዉ ከሚኖሩ 360 ሰራተኞች ተቀጥረዋል። ሌሎች 1500 ሰራተኞች ደግሞ በሌላ አስቀጣሪ ድርጅት በኩል ተቀጥረዉ ኩባንያ ዉስጥ በማገልገል ላይ ናቸዉ። ይህ ኩባንያ ለአካባቢዉ ነዋሪዎች ጥሩ ስራ ፈጣሪ ግን አልሆነም። የማዕድን ማዉጫ ኩባንያዉ ለአካባቢዉ ላይ ለሚኖሩት በግምት 70,000 ነዋሪዎች በጣም ጥቂት ሰራተኞችን ነዉ የቀጠረዉ። ጥቂት ተቀጣሪ ግን ለድርጅቱ በርካታ ገቢን ያስገኛል። እንዲህ አይነቱ የአሰራር ችግር በጥሪ ሃብት ምርቱ ዘርፍ የተለመደ መሆኑ የማይታበል ነዉ።

Ein Sicherheitszaun schirmt die Nord Mara Goldmine nach außen ab. *** Bilder Deutsche Welle, Julia Hahn, November 2012 Ort: Nord Mara Goldmine des Konzerns African Barrick Gold, Nord Mara Region, Tansania *** http://en.wikipedia.org/wiki/North_Mara_Gold_Mine North Mara Gold Mine is an open pit gold mine in the Tarime District of the Mara Region of Tanzania. It is operated by African Barrick Gold. It is one of four gold mines African Barrick Gold, a subsidiary of Barrick Gold, operates in Tanzania, the other three being Tulawaka, Bulyanhulu and the Buzwagi Gold Mine. In the financial year 2009, the four operations produced a combined amount of 716,000 attributable ounces of gold.
ምስል DW/J. Hahn

በሰሜናዊ ማራ የሚገኘዉ የወርቅ ኩባንያ ABG በ ጎ,አ 2011 ዓ,ም 200 ሚሊዮን ይሮ ገቢን አግኝቶአል። የኩባንያዉ አስተዳዳሪ Garya Chapman, ኩባንያዉ ስለ አካባቢዉ ማህበረሰብ ሃላፊነት እንደሚሰማዉ እንዲህ ይናገራሉ።

«ከግዜ ጋር ቀጣይነት እና በእኛ እና ማህበረሰቡ ዘንድ እምነትን ለማግኘት በመስራት ላይ ነን ይህንንም ከዳር እናደርሳለን፤ ቢያንስ ከማህበሩ ክብር እናገኛለን። እንድንወደድም እንፈልጋለን፤ ግን መከባበር እና የጋራ ስራ አይነተኛዉ እና ተፈላጊዉ መንገድ ነዉ።»የአፍሪቃዉ ባሪክ የተሰኘዉ የወርቅ ማዕድን ማዉጫ ኩባንያ አንዳንድ በሰራቸዉ ስራዎች ኩራትም አለዉ። ለምሳሌ ከማዕድን ማዉጫዉ ቦታ እንብዛም የማይርቀዉ (INGWE SECONDARZ SCHOOL) ኢንግቬ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተጠቃሽ ነዉ። በ 2012 ዓ,ም ABG የፈራረሱትን የመማርያ ክፍሎች አድስዋል፤ በመቀጠል የመመገብያ ክፍልና አንድ የመማርያ ህንጻን ገንብቶአል። ታድያ ይህ ሁሉ ሲያደረግ ኩባንያዉ ለአካባቢዉ ነዋሪዎች የስራ እድልን ፈጥሮአል ነዉ። የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር Joash Mageka የማዕድን ኩባንያዉ አደረገ የተባለዉን ስራ ደመቅ አድርገዉ ያሞግሳሉ።

«ብዙ ነገር ነዉ የተቀየረዉ! ትምህርት ቤቱ በርግጥ አሁን ጥሩ ሆንዋል። ለዚህም በጣም ኮርቻለሁ። ከዚህ በፊት በርካታ ተማሪዎች ከትምህርት በኋላ ያለፈቃድ በማዕድን ማዉጫዉ እየገቡ ሌላ ስራን ይሰሩ ነበር ። አሁን ግን ይህ ነገር እምብዛም አይታይም። መማራቸዉ አሳዉቆአቸዋል።» ABG የወርቅ ማዉጫ ኩባንያ ታንዛንያ ዉስጥ ከጎ 2010 ዓ,ም ጀምሮ 20,6 ሚሊዮን ዶላር ለማህበረሰባዊ መረኃ-ግብሮች ወጭ ማድረጉን ይገልፃል። ይህ ደግሞ ሲሰላ ኩባንያዉ ካስገኘዉ ገቢ ዉስጥ አንድ በመቶ ያነሰ ይሆናል። እንደ ኩባንያዉ ቃል አቀባይ በተለይ ባለፉት ሁለት አመታት አብዛኛዉ ወጭ የፈሰሰዉ በሰሜናዊ ማራ ለሚገኙ ነዋሪዎች ተደርጓል።

የዉጭ ኩባንያ በቦታዉ ላይ ሳይመጣ የአካባቢዉ ነዋሪዎች በራሳቸዉ መንግድ በጥቂቱም ቢሆን ወርቅ እያወጡ ይተዳደሩ ነበር። በሚያገኙትም ገቢ ኑሮአቸዉን ይገፉ ነበር። በ1990 ዎቹ መጨረሻ አለማቀፎቹ የማዕድን አዉጭ ኩባንያዎች ወደ አገሪቱ ከገቡ በኋላ ትናንሾቹ ማዕድን ቆፋሪዎች ስራ ቦታቸዉን አጡ። የአካባቢዉ የወርቅ ንግድ በዉጭ ያሉትን ነዋሪዎችንም ወደቦታዉ እንዲመጡ ሳይጋብዝ አልቀረም። ለምሳሌ በጎረቤት ኬንያ ነዋሪ የነበረዉ ዴቪድ አሩምባ ከአንድ አመት በፊት ወደ ሰሜን ማራ በዚሁ በወርቅ ንግድ ለመተዳደር መጣ። የ 25 ዓመቱ ዴቪድ አሩንባ ከቤተሰቡ መካከል ብቸኛዉ ትምህርትን ያገኘ ነበር፤ ማራ በህገ-ወጥ በማዕድን ማዉጫ ቅጽር ግቢ እየገባ በቁልሉ አፈር ላይ የወርቅ ስብርባሪን የመፈለጉ ስራን መተግበር እንደማይፈልግ እንዲህ ይናገራል፤

Gokona-Tagebau: In der Nord Mara Mine wird das Gold in mehreren offenen Tagebaugruben gefördert. Täglich wird dazu Gestein aus dem Boden gesprengt. *** Bilder Deutsche Welle, Julia Hahn, November 2012 Ort: Nord Mara Goldmine des Konzerns African Barrick Gold, Nord Mara Region, Tansania *** http://en.wikipedia.org/wiki/North_Mara_Gold_Mine North Mara Gold Mine is an open pit gold mine in the Tarime District of the Mara Region of Tanzania. It is operated by African Barrick Gold. It is one of four gold mines African Barrick Gold, a subsidiary of Barrick Gold, operates in Tanzania, the other three being Tulawaka, Bulyanhulu and the Buzwagi Gold Mine. In the financial year 2009, the four operations produced a combined amount of 716,000 attributable ounces of gold.
ምስል DW/J. Hahn

« ሌላ ሥራን ለመስራት ወስኛለሁ። አብዛኞች ይገደላሉ ወይም ይቆስላሉ። እኔ ሁልግዜ ፖሊስ መጣብኝ አልመጣብኝ እያልኩ በፍርሃት መኖርና መስራትን፤ ወይም ስህተተኛ ሆኜ መገኘትን አልፈልግም። ስለዚህም አንድ ትንሽ ድርጅት አቋቁሜያለሁ። በዚህ ደግሞ ነፃ የሆነ ዉስጣዊ ስሜት አለኝ» ዴቪድ በካዊንጃ አንድ የመኪና ማጠብያ ሳሎን ከፍቶአል። በሰሜናዊ ማራ ነገሮች ትክክል ያልሆኑበት ጉዳይ ምን ይሆን? ይህ ጥያቄ በዳሪሰላም ለሚገኘዉ የታንዛንያ መንግስት የቀረበ ጥያቄ ነበር። በታንዛንያ የማዕድን ሚንስትር Sospeter Muhongo ራሳቸዉ የመጡት ከሰሜናዊ ማራ አካባቢ ነዉ። የስነ- ምድር ትምህርትን የተከታተሉት የታንዛንያዉ የማዕድንን ሚኒስትር፤ ይህንን ስልጣን የያዙት በቅርብ ግዜ ሲሆን፤ በሀገሪቱ የሚገኙ ትላልቅ ኩባንያዎች የበለጠ ቀረጥ እንዲከፍሉና ማህበረሰቡ የሚያስፈልገዉን ነገር እንዲያሟላ የበለጠ እንቅስቃሴ አድርገዋል። ግን ሚንስትሩ ከመሾማቸዉ በፊት ባለፉት ዓመታት የአገሪቱ ፖለቲካ ስላሳደረዉ እንቅፋት እና አለመሻሻል ማወቅም ሆነ መናገር አይሹም፤ « ሁሉንም ነገር ለማድረግ እየሞከርን ነዉ፤ ወደፊትምበዚህ አካባቢ ሰላም እና የፀጥታዉን ሁኔታ ለማስጠበቅ የተቻለንን ሁሉ እንጥራለን። ይህን ለማደርግ ከሁሉ በፊት የትምህርት ስልጠና ላይ መዋለ ንዋይን ማፍሰስ ይኖርብናል። ሰዎች በደንብ ስልጠናን ከወሰዱ እና ከተማሩ አስተሳሰባቸዉም ይቀየራል»በኩዋንጃና አካባቢዋ ግን እስካሁን የተቀየረ ነገር የለም። በህገ-ወጥ መንገድ በመሸጥ ላይ ያለዉ ወርቅ ግን ጥቅምን እያስገኘ ነዉ። በገጠር መንደሩ ዳርቻ ላይ በአንድ ሰዋራ ስፍራ ከወርቅ ማዉጫ ኩባንያዉ ቅፅር ግቢ በመግባት አፈር እና ድንጋይ ቁልሉ ላይ ከድንጋይ ጋር ያለዉን የወርቅ ስባሪን በመሰብሰብ ትንሽ ግራም የምትመዝን ድብልብል ወርቅ ያወጣሉ። በመጀመርያ ወርቅ የያዘዉን ድንጋይ እስኪልም ከፈጩ በኋላ በተቋጠረ ዉሃ ዉስጥ ከተዉ ሜርኩሪ በመጨመር ለጤንነት አደገኛ በሆነ ሁኔታ የወርቁን ከድንጋይ በመለየት በአንድ ላይ ይሰበስቡታል።በዚሁ ቦታ ላይ የሚሰራ እንድ ማንነቱን መናገር ያልፈለገ ሰዉ የአሰራሩ ዘዴ እጅግ ለጤና ጎጂ መሆኑን እና ስለጤንነቱም በጣም እንደሚጨነቅ ይናገራል። «እያንዳንዱ ሰዉ ቤተሰቡን ለመመገብ በቂ ገንዘብ ማግኘትን ይፈልጋል። እኔ ቀደም ሲል በግብርና ስራ እተዳደር ነበር፤ በግብርና አንድ ዓመት ሰርቼ የማገኘዉ ነዉ፤ አሁን በምሰራዉ በዚህ ስራ በአንድ ቀን የማገኘዉ» ወጣቱ በእጁ ላይ አንዲት ትንሽ ድብልብል ምናልባትም ከአንድ ግራም የምትሆን ያነሰች አስቀምጦ ያሳያል። ይህችን ቅንጣት ወርቅ ሲሸጠጥ ምናልባት ወደ ሃያ ይሮ ግድም ነዉ የሚያገኘዉ። ታንዛንያ ካላት የጥሪ ሃብት አንድ ኢምንት የምትሆን ቅንጣት፤ ግን ለደሃይቱ ሰሜናዊ ታንዛንያ ነዋሪ ይህ ገንዘብ መተዳደርያ ነዉ።

ዩልያ ሃን/ አዜብ ታደሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ