1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ታዳሽ የኃይል ምንጭ፧

ረቡዕ፣ ኅዳር 10 2001

ታዳሽ የኃይል ምንጭ፣ በአሁኑ ዘመን፧ በኢንዱስትሪ የበለጸጉትንና በመልማት ላይ የሚገኙትን አገሮች፧ ቀልብ የሳበ ጉዳይ ሆኗል።

https://p.dw.com/p/FyAv
ፀሐይምስል DW-TV

በዓለም አቀፍ ጠበብት ጥናት መሠረት፧ እያሳሰበ የመጣው የዓለም የአየር ንብረት መዛባትና በዚሁ ሳቢያ መታየት የጀመሩ የጥፋት ምልክቶች ናቸው። በመሆኑም፧ የባህር ወሰን ያላቸው በኢንዱስትሪ የገሠገሡት አገሮች ውቅያኖስ ጠረፍ አቅራቢያ ባህር ላይ በነፋስ ኃይል ኤልክትሪክ የሚያመነጩ አውታሮችን በብዛት በመትከል ላይ ይገኛሉ። ለምሳሌ ያህል ኔደርላንድ ባለፈው ወር፧ ከአምስተርዳም በስተሰሜን ምሥራቅ፧ ከጠረፍ ገባ በማለት ባህር ላይ Egmond aan Zee በተባለው ቦታ በ 200 ሚልዮን ዩውሮ፧ ለ 100,000 ቤቶች የኤልክትሪክ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ፧ በሰዓት 108 ሜጋዋት የሚያመነጩ 36 አውታሮች ተክላለች። ኔደርላንድ፧ እ ጎ አ እስከ 2010 ዓ ም ፧ 9% የኤሌክትሪክ አገልግሎትን፧ ከታዳሽ የኃይል ምንጮች ለማግኘት ነው ያቀደች። አራት ሺ ኪሎሜትር ያህል ርዝማኔ ያለው የዋህት ጠረፍ ያላት እስፓኝ በበኩሏ፧ ከያዝነው 2007 ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት ማለቂያ በፊት፧ ከተረፍ ትንሽ ወደ ባህር ገባ ብሎ፧ በነፋስ ኃይል ኤሌክትሪክ የሚያመነጩ አውታሮችን ለመትከል ቦታዎችን መርጦ ተግባራዊ የሚደረግበትን ደንብ ታጸድቃለች ተብሎ ይጠበቃል። ከ 27 ቱ የአውሮፓው ኅብረት አባል አገሮች መካከል፧ በነፋስ ኃይል በአመዛኙ የሚጠቀሙት፧ ጀርመን፧ ደንማርክና እስፓኝ ናቸው።

እስፓኝ፧ እ ጎ እስከ 2020 ዓ ም ከታዳሽ የኃይል ምንጮች፧ ሦስት እጥፍ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት እቅድ አላት። እስከተጠቀሰው ዓ ም፧ አውሮፓውያን፧ 20% የኃይል ምንጫፀውን ካታዳሽ የኃይል ምንጮች የማግኘት አቅድ ነው የዘረጉት። ዩ ኤኤስ አሜሪካም ውስጥ፧ በማሳቹሰትስ ፌደራል ክፍለ ሀገር፧ ከባህር ጠረፍ ጥቂት ፈንጠር ብሎ ባህር ላይ፧ 130 በነፋስ ኃይል የሚሠሩ አውታሮች ለመትከል በቅድሚያ ፈቀዱ ከፌደራሉ ግዛት ለማግኘት መቻሉ ተነግሯል። ለተፈጥሮ አካባቢ ብክለት የማያስከትሉ የኃይል ምንጮችን መሻት ወቅቱ አጥብቆ የሚጠይቀው ጉዳይ ሆኗል።

ሚያዝያ 11 እና 12 ቀን 1997 ዓ ም፧ በሰሜን ጀርመን በሃምበርግ ከተማ ከተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪቃ የኃይል ምንጭና የጀርመን ትብብር ነክ ጉባዔ በመነሣት፧ ባለፉት ሁለት ዝግጅቶቻችን፧ በአማዛኙ በውሃ የኃይል ምንጭነት ላይ ማትኮራችን ይታወስ ይሆናል። ኢትዮጵያ በተለዩ የተፈጥሮ የኃይል ምንጮች ከታደሉት አገሮች አንዷ መሆኗ የታወቀ ነው። ብዙ ታላላቅ ወንዞች ስላሏት፧ እነዚህን በመገደብ፧ ኃይለኛውን የፀሐይ ሙቀትና ብርሃን፧ በከፍተኛ አምባዎቿ በበጋ የሚያጋጥመውን ነፋስ፧ በከርሠ ምድር የሚገኘውን የእንፋሎትና የፍል ውሃ ኃይል በማጥመድ፧ በሰፊው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት አይሳናትም። ለዚህ፧ እርግጥ ነው፧ የዘመናዊው ቴክኖሎጂ አጠቃቀም እጅጉን ተፈላጊ ይሆናል። በሃምበርጉ ጉባዔ፧ ኢትዮጵያ ውስጥ በነፋስ ኃይል የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ስለሚቻልበት ፕሮጀክት Wind Energy Development in Ethiopia በሚል ርእስ የጥናት ውጤት ያቀረቡት፧ Lahmeyer International GmbH የተሰኘው ኩባንያ የፕሮጀክት ዋና ሥራ አስኪያጅ Manfred Gose

1.«በዚህ ጉባዔ ያቀረብኩት የጥናት ውጤት 120 ሜጋዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያመነጭ በነፋስ ኃይል የሚሠሩ አውታሮች የሚተከሉበት ጣቢያ ስለማስፈለጉ ነው። ይህም በአፍሪቃ እጅግ ትልቁ በነፋስ ኃይል የሚሠሩ አውታሮች የሚተከሉበት ጣቢያ ሳይሆን አይቀርም። በዚህ የነፋስ ኃይል በሰዓት 400 ጊጋዋት የኃይል ምንጭ ማግኘት ይቻላል። በጀርመን፧ በአማካዩ አንድ ቤተሰብ(አራት ሰዎችን የሚያጠቃልል) በዓመት የሚጠቀምበት የኤሌክትሪክ ኃይል ምንጭ መጠንበግምት በሰዓት 3,500 ኪሎዋት ነው።«

2.«የዚህ በነፋስ ኃይል የሚሠሩ አውታሮች ጣቢያም ሆነ ፓርክ፧ ገና በአቅድ ላይ ሲሆን፧ እ ጎ አ በ 2004 እና 2005 ዓ ም የነፋስ ኃይልን መጠን የሚለካበት ዘመቻ ተካሂዶ ነበር። ይህም በጀርመን የቴክኒክ ተራድዖ ድርጅት(GTZ) በኩል የተካሄደ ነበር። በተለያዩ አማራጭ ቦታዎች ነበረ የነፋስን ኃይል መጠን ለመለካት እርምጃ የተወሰደው። በ 10 ቦታዎች ነበረ እንዲያው ለመለካት እርምጃ የተወሰደው። ከ አሥሩም እንደገና አራት ተመርጠዋል። በመሆኑም ተግባራዊ ማድረግ የሚቻልበትን ጥናት ባለፈው ዓመት አጠናቀናል። በዚህ ተግባራዊ ሊሆን በሚችል ጥናት መሠረት አንድ በነፋስ ኃይል የሚሠሩ አውታሮች የሚተከሉበት ጣቢያ (ፓርክ) መጠኑ ምን ያህል ሊሆን እንደሚችል፧ ምን ያህል የኃይል ምንጭም ማመንጨት እንደሚችል፧ እንዴትም ኃይሉን ከአንድ ቦታ ወደሌላው ማስተላለፍ እንደሚቻል እንዲሁም፧ በውሃ ኃይልና በነፋስ ኃይል የሚሠሩ አውታሮችን ተግባር ማቀናጀት እንደሚቻል አሳይተናል።«

3.«ከአራቱም ቦታዎች ለጊዜው በቅድሚያ አንድ መርጠናል። እሱም የሚገኘው፧ ከመቐለ ከተማ አቅራቢያ አሸጎራ በሚባል ቦታ የሚገኝ ነው። በዚያም፧ በነፋስ ኃይል 120 ሜጋዋት መመንለት ይቻላል። በኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መሥመሮች በኩል፧ በውሃ ኃይል ከሚሠራ የኃይል ማመንጫ አውታር ጋር የሚገናኝበት፧ የሚቀዳጅበት ሁኔታ ተመቻችቷል። በነፋስ ኃይልየሚሠራ የኤሌክትሪክ ማመንጫ አውታር ጠቃሚነቱ በተለይ ኢትዮጵያን በመሰለ ሀገር፧ ሁለቱም በውሃ የሚሠራውና በነፋስ፧ ሁለቱንም ማቀናጀት መቻሉ ነው። በበጋ ዝናም በማይጥልበት ወቅት ኀይለኛ የነፋስ ኃይል አለ። ዝናም አዘውትሮ በሚጥልበት የክረምት ወቅት ደግሞ የነፋሱ ኃይል ይቀንሳል። ስለዚህ፧ በበጋ በነፋስ፧ በክረምት ደግሞ በውሃ ኃይል፧ የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት ሁለቱን በማስተባኣበር መጠቀም ይቻላል።«

Manfred Gose እንዳሉት፧ አንድ በነፋስ ኃይል የኤሌክትሪክ ማመንጫ ጣቢያ (ፓርክ) ለማቋቋም፧ 1.6 ሚልዮን ዶላር ያህል ወጪ ይጠይቃል

የፕሮጀክት ወጪ፧

የአውስትሬሊያ ነባር ተወላጆች(Aborigines) የዘር ምንጫቸው፧ አፍሪቃ መሆኑን፧ ተመራማሪ ጠበብት አረጋገጡ። አሁን በሚገኙበት የአውስትሬሊያ ክፍለ-ዓለም የሠፈሩት ከ ሃምሳ ሺ ዓመት ገደማ በፊት ከአፍሪቃ በመፍለስ ነው ሲሉ ያስታወቁት የብሪታንያው ኬምብሪጅ ዩኒቨርስሲ ተመራማሪ ጠበብት ናቸው። ዘመናዊው ሰው፧ Homo Sapiens ከተሰኘው ነጠላ የዝርያ ቡድን የተገኘ ሲሆን፧ አቦሪጂንስ፧ ከአፍሪቃ ወደ አውስትሬሊያ የፈለሱት፧ የተሰደዱት፧ ከ ሁለት ሺ የትውልድ ዘመን በፊት ነው። እስካሁን ሲያጠራጥር የነበእ የአውስትሬሊያ አቦሪጂንስ Java |Man ወይም፧ Homo Erectus ከተሰኘው ዝርያ ጋር ሳይቀላቀሉ አልቀሩም የሚለው ነባቤ-ቃል ነው። ይሁንና፧ የ 700 ያህል አቦሪጅንስና በፓፑዋ ኒው ጊኒ የሚኖሩ ሜላኔሺያን ሰዎች የዘር ምንጭ ኅዋስ ምርምር ውጤት እንዳሳየው ከሆነ ከ«ሆሞ ኤሬክተስ« የወረሱት የዘር ምንጭ ምልክት አልተገኘም።

የሄሮድስ መቃብር፧

Ehud Netzer የተባሉት የዕብራውያን(Hebrew) University የከርሠ-ምድር ታሪካዊ ቅርሳ-ቅርስ ተመራማሪ፧ ክርስቶስ በተወለደበት ዘመን ከሁለት ሺ ዓመት ገደማ በፊት የነበረውን ንጉሥ ሄሮድስ መቃብር ማግኘታቸውን አስታውቀዋል። Netzer እ ጎ አ ከ 1972 ዓ ም አንስቶ በፍለጋ ተሠማርተው እንደነበረ ታውቋል። ከኢየሩሳሌም በስተደቡብ 750 ሜትር ከፍታ ጎጥ ውስጥ የተገኘው የንጉሥ ሄሮድስ የድንጋይ መቃብር የንጉሡ ለመሆኑ ጥርጥር የለውም ነው ያሉት ኔትዘር ፧ ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ!

ከ 40-4 ዓመተ-ዓለም፧ በሮማውያን ተሹሞ፧ ይሁዳ የሚባለውን አገር ይጋዛ የነበረው ንጉሥ ሄሮድስ፧ በኢየሩሳሌም ሁለተኛውን የአይሁድ ቤተ-መቅደስ በቤት-ልሄም አቅራቢያም፧ ማሳዳና ሄሮዲዮን የተባሉትን አብያተ መንግሥት ያሳነጸ መሆኑም ይነገርለታል። ሄሮድስ፧ በመጽሐፍ ቅዱስ የማቴዎስ ወንጌል እንዳሠፈረው፧ ብዙ ኅጻናት ያስፈጀ ጨካኝ ንጉሥ ነበረ። የሄሮድስ የድንጋይ መቃብር የተገኘው ተፈረካክሶ ነው። ይህም ሆነ ተብሎ የተደረገ ሳይሆን እንዳልቀረ ተጠቅሷል። ከክርስቶስ ልደት በኋላ በ 66 እና 72 ዓ ም መካከል፧ ይሁዲዎች በባዕዳኑ ሮማውያን ገዢዎችና በእንደራሴአቸው ላይ አምፀው መሪር ውጊያ ማካሄዳቸው ነው የሚነገረው። Ehud Netzerየተገኘው መቃብርየሄሮድስ ስለመሆኑ ምን ያህል ያስተማምናል ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ እንዲህ ነበር ያሉት።

«የድንጋዩ መቃብር አሠራር የሚያስገርም ነው። በሄሮዲያም ከተወቁት መካነ-መቃብር በጣም የተለየ ነው። ከጥራቱም አኳያ ሲታይ፧ ይህ ስንፈልገው የነበረ መቃብር ለመሆኑ ምንም አልጠራጥርም።«

በአሁኑ ዘመን፧ በኢንዱስትሪ የበለጸጉትንና በመልማት ላይ የሚገኙትን አገሮች፧ ቀልብ የሳበ ጉዳይ ሳይሆን አልቀረም። ከምክንያቶቹ አንዱ በዓለም አቀፍ ጠበብት ጥናት መሠረት፧ እያሳሰበ የመጣው የዓለም የአየር ንብረት መዛባትና በዚሁ ሳቢያ መታየት የጀመሩ የጥፋት ምልክቶች ናቸው። በመሆኑም፧ የባህር ወሰን ያላቸው በኢንዱስትሪ የገሠገሡት አገሮች ውቅያኖስ ጠረፍ አቅራቢያ ባህር ላይ በነፋስ ኃይል ኤልክትሪክ የሚያመነጩ አውታሮችን በብዛት በመትከል ላይ ይገኛሉ። ለምሳሌ ያህል ኔደርላንድ ባለፈው ወር፧ ከአምስተርዳም በስተሰሜን ምሥራቅ፧ ከጠረፍ ገባ በማለት ባህር ላይ Egmond aan Zee በተባለው ቦታ በ 200 ሚልዮን ዩውሮ፧ ለ 100,000 ቤቶች የኤልክትሪክ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ፧ በሰዓት 108 ሜጋዋት የሚያመነጩ 36 አውታሮች ተክላለች። ኔደርላንድ፧ እ ጎ አ እስከ 2010 ዓ ም ፧ 9% የኤሌክትሪክ አገልግሎትን፧ ከታዳሽ የኃይል ምንጮች ለማግኘት ነው ያቀደች። አራት ሺ ኪሎሜትር ያህል ርዝማኔ ያለው የዋህት ጠረፍ ያላት እስፓኝ በበኩሏ፧ ከያዝነው 2007 ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት ማለቂያ በፊት፧ ከተረፍ ትንሽ ወደ ባህር ገባ ብሎ፧ በነፋስ ኃይል ኤሌክትሪክ የሚያመነጩ አውታሮችን ለመትከል ቦታዎችን መርጦ ተግባራዊ የሚደረግበትን ደንብ ታጸድቃለች ተብሎ ይጠበቃል። ከ 27 ቱ የአውሮፓው ኅብረት አባል አገሮች መካከል፧ በነፋስ ኃይል በአመዛኙ የሚጠቀሙት፧ ጀርመን፧ ደንማርክና እስፓኝ ናቸው።