ታዳሽ ፣ የፀሐይ ኃይል ምንጭ ፕሮጀክት
ረቡዕ፣ መጋቢት 11 2005እንደነበረ ይታወስ ይሆናል። ኢትዮጵያ ውስጥ ፕሮጀክቶች ካሏቸው ድርጅቶች መካከል « ሄሊዮዝ»ና አንዳንድ «የፀሐይ ሱቅ » የሚል ዓይነት ስም የያዙ በፀሐይ ኃይል ኤሌክትሪክ በማመንጨት ፣ ለቤተሰብም ሆነ ማኅበረሰብ አገልግሎት መስጠት እንደሚቻል ፤ በሐኖፈሩ የዘንድሮ ዓለም አቀፍ ትርዒት የፈጠራ ውጤቶቻቸውን ያሳዩ ኩባንያዎች ነበሩ።
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ፣ እንደሚታወቀው፣ በኢንዱስትሪ የበለጸጉ በቴክኖሎጂውም የደረጁ መንግሥታት ፤ የኃይል ምንጭ ን በተመለከተ ዐቢይ ግምት በመስጠት ላይ ያሉት ታዳሽ የኃይል ምንጭ ለሚባለው መሆኑ የታወቀ ነው። ይህ፣ ለተፈጥሮ አካባቢ ጠንቅ አለመሆኑ የሚነገርለት ፣ በፀሐይ በነፋስ በውሃና በመሳሰለው ላይ ያተኮረው የኃይል ምንጭ ዘርፍ ፤ ገና በማደግ ላይ በሚገኙት አገሮች ቢስፋፋ እጅግ እንደሚበጅ ከቶ አያጠራጥርም።
በዚህ በጀርመን ሀገር ፤ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ከጀርመናውያን ጋር በመተባበር፣ በፀሐይ ኃይል የሚሠራ የኃይል ምንጭ ፤ በተለይ ወደ ውስጥ ገባ ላሉ ንዑሳን ከተሞችና መንደሮች ያላቸውን ጠቀሜታ በመገንዘብ እንዲቀርብ በማድረግ ላይ ሲሆኑ ፣ ከእነዚህ መካከል በደቡብ ምዕራብ ጀርመን ካርልስሩኸ አቅራቢያ «ብሩኅሳል» ላይ የሚገኘው ፣ «አልፋ-ቤት ኢትዮጵያ » (ፊደል ኢትዮጵያ ) እንደማለት ነው)
በዚህ ስያሜ የሚጠራው ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ፣ በጉራጌ አውራጃ በያንቤሊ ሰባካ ፕሮጀክቱን ያስተዋወቀው ድርጅት ነው። አስተባባሪው አቶ ሳሙኤል ኤታና ሁዋ ነው። እርሱም፣ ይኸው ድርጅት ስላበረከተው ድርሻ እንዲህ ያብራራል።
ተክሌ የኋላ
ሂሩት መለሰ