1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ሙዚቃ

የቴዎድሮስ ካሳሁን ቃለ-መጠይቅ በዶይቼ ቬለ

ዓርብ፣ ግንቦት 11 2009

አቡጊዳ' ካላት ከመጀመሪያ የሙዚቃ አልበሙ አንስቶ እስካሁን በሙዚቃ አድማጮቹ ዘንድ ኮርኳሪና አነጋጋሪ በሆኑ ግጥሞች የታጀበዉ የሙዚቃ ሥራዉ ይወደድለታል።

https://p.dw.com/p/2dEyj
Tewodros Kassahun Musik Äthiopien
ምስል DW/L.Abebe

Unterhaltung Promo - MP3-Stereo

የሚያዜማቸዉን ሙዚቃዎች ዜማ ከግጥም ደርሶ ማቅረቡን ራሱ ይናገራል፤ አንዳንዶችም ይመሰክሩለታል። ግን ደግሞ የአባቱን ታዋቂ ገጣሚነት እየጠቀሱ የአባቱን ሥራዎች ነዉ የሚያንጎራጉረዉ የሚሉት አሉ። ቴዎድሮስ ካሳሁን ግን መልሱ አጭርና ቁርጥ ያለ ነዉ፤ «የራሴን ዜማና ግጥማ አንጎራጉራለሁ»። ታስሮም ነበር ቴዲ፤ የሙዚቃ ድግሶች (ኮንሰርቶችን) ሊያቀርብ ነዉ እየተባለም ተሰረዘ ሲባል ተሰምቷል። ቴዎድሮስ ካሣሁንን እሁድ በመዝናኛ ዝግጅታችን እንግዳ አድርገን እነዚህን ጉዳዮች አንስተንለታል።