1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ትምሕርት ለሁሉም ዓመታዊ ዘገባ

ማክሰኞ፣ ጳጉሜን 4 2006

ኢትዮጵያ ትምህርት አገልግሎትን በማስፋፋትና መምህራንን በመቅጠር የተሻለ እድገት ካሳዩ ሃገሮች ተርታ ተመድባለች። እንደ ማኖስ አንቶኒኒስ ከሆነ ከኢትዮጵያ የአንደኛ ደረጃ መምህራን መካከል በቂ የሙያ ስልጠና ያገኙት 20 በመቶው ብቻ ናቸው

https://p.dw.com/p/1D9Tt
ምስል picture-alliance/dpa

አለም አቀፍ የትምህርት ሁኔታን በሃገራትና በክፍለ አህጉራት እየከፋፈለ የሚገመግመው አመታዊው የትምህርት ለሁሉም ሪፖርት ይፋ ሆኗል።ማስተማርና መማር-የትምህርት ጥራትን ለሁሉም ማዳረስ (TEACHING AND LEARNING: Achieving quality for all )የሚል ርዕስ የተሰጠው የዚህ አመት ባለ 496 ገጽ ሪፖርት የኢትዮጵያን የትምህርት ዘርፍ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ይዘረዝራል።እሸቴ በቀለ የሪፖርቱን ከፍተኛ የፖሊሲ ተንታኝ አነጋግሮ የሚከተለውን ዘገባ አዘጋጅቷል።

... 2006 ጀምሮ ኢትዮጵያ የትምህርት ተደራሽነትንና የክልሎችን ተሳትፎ በማሳደግ ከፍ ያለ ውጤት አስመዝግባለች። የአንደኛ ደረጃ ትምህርትን ያላጠናቀቁ ሰዎች ቁጥርም እ... 2000 ከነበረበት ከአስር አመታት በኋላ በሃያ በመቶ ቀንሷል ይላል የዚህ አመት የትምህርት ለሁሉም ሪፖርት ።

በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፤የሳይንስና የባህል ድርጅት ዩኔስኮ የገንዘብ ድጋፍ ይፋ በሚሆነው በዚህ ሪፖርት ቀድሞ ከፍተኛ ልዩነት የሚታይበትን የክልሎች የትምህርት ተደራሽነት በማጥበብ በኢትዮጵያ ለውጥ መታየቱን ያትታል።በአዲስ አበባ ና የሶማሌ ክልል መካከል የነበረው ልዩነት ከ63 በመቶ ወደ 49 በመቶ ዝቅ ማለቱን ሪፖርቱ በምሳሌነት አስፍሯል። አመታዊ ሪፖርቱ የኢትዮጵያን የትምህርት አፈጻጸም ሲገመግም ጠንካራና ደካ ጎኖችን አንስቷል ማኖስ አንቶኒኒስ የትምህርት ለሁሉም አለም አቀፍ ሪፖርት ከፍተኛ የፖሊሲ ተንታኝ ናቸው

Traugott Schöfthaler, Generalsekretär der Deutschen UNESCO-Kommission
ምስል dpa/lni

''የኢትዮጵያ መንግስት ትምህርትን በከፍተኛ ደረጃ ይደግፋል።ከአመታዊ በጀት ከፍተኛውን ለትምህርት ከመደቡ ሀገሮችም አንዱ ነው። እ... 2000 እና 2010 መካከል ለትምህርት የሚመደደበው በጀት በእጥፍ አድጎ አሁን ከአመታዊ በጀቱ አንድ አራተኛው ለትምህርት የተመደበ ነው።ይህ የመማሪያ ክፍሎችን ለመገንባትና መምህራንን ለመቅጠር የሚውል ነው።ይህ በጣም ጠቃሚ ነጥብ ነው። በዚህ ሪፖርት በፋይናንስ በኩል ኢትዮጵያ ያላትን አቅም በአግባቡ እየተጠቀመች እንዳልሆነ ተመልክተናል። ለምሳሌ ከሃገር ውስጥ በታክስ የሚሰበሰበው ገቢ አነስተኛ ነው።ኢትዮጵያ ከታክስ የምትሰበስበውን አመታዊ ገቢ ከ 11 በመቶ ወደ 20 በመቶ ማሳደግ ብትችል በ2015 የትምህርት ዘርፉን ለመደጎም የሚያስችል 435 ሚሊዮን ዶላር ማግኘት ትችላለች። ''

በሪፖርቱ መሰረት ኢትዮጵያ ትምህርት አገልግሎትን በማስፋፋትና መምህራንን በመቅጠር የተሻለ እድገት ካሳዩ ሃገሮች ተርታ ተመድባለች። እንደ ማኖስ አንቶኒኒስ ከሆነ ከኢትዮጵያ የአንደኛ ደረጃ መምህራን መካከል በቂ የሙያ ስልጠና ያገኙት 20 በመቶው ብቻ ናቸው። እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሃገሮች የትምህርት ዘርፉን በጥራት ለማሳደግ የሚያስችሏቸው አራት መሰረታዊ ነጥቦች በሪፖርቱ ተካተዋል።

''የመጀመሪያው መንግስታት የምርጥ መምህራንን ትኩረት መሳብ አለባቸው። አዳዲስ መምህራንን ማሰልጠን እና ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ ወሳኝ ጉዳዮች ናቸው። በኢትዮጵያ የመምህራን ስልጠና ፕሮግራም እጩ መምህራን ወደስራ አለም ሲገቡ የሚደረግላቸው ድጋፍ በምሳሌነት ይጠቀሳል። ሁለተኛው የመምህራንን ስልጠና ማሳደግ ነው። በብዙ ሃገሮች እንደሚታየው ለመምህራን የሚሰጠው ስልጠና የመማሪያ ክፍሎች ያሉበትን ነባራዊ ሁኔታ የዘነጋ ነው። መምህራን የተማሪዎቻቸውን ፍላጎት ቀድመው ማወቅ ይጠበቅባቸዋል።በትምህርት ስልጠናም በዚህ ረገድ ለሚገጥማቸው ችግር መፍትሄ ለመስጠት እንዲችሉ ማዘጋጀት ያሻል። ሶስተኛው መምህራን በሚፈለጉበት ቦታ መመደብ ነው። በብዙ ሃገሮች በአግባቡ ያልሰለጠኑ መምህራንን ወደ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የመመደብ ሁኔታ ይታያል።ይህ ተገቢ መፍትሄ አይደለም። መንግስታት ምርጥ መምህራንን እግጅ አስፈላጊ ወደሆኑበት የገጠር አካባቢዎችና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መመደብ መቻል አለባቸው።አራተኛውና የመጨረሻው መንግስታት ለመምህራን አስፈላጊውን ጥቅማ ጥቅም በመስጠት በሙያቸው እንዲቆዩ ማድረግ ነው።''

Unesco-Tag auf der Didacta 2011 in Stuttgart
ምስል Deutsche UNESCO-Kommission

በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፤የሳይንስና የባህል ድርጅት በአመት አንድ ጊዜ የሚያወጣው ይህ ሪፖርት እ... 2000 .ም ሴኔጋል ዳካር ላይ በተካሄደ አለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ስምምነት በተደረሰባቸው ስድስት መሰረታዊ ነጥቦች ላይ ትኩረት ያደርጋል። የህጻናት ክብካቤና ትምህርት፤አለም አቀፍ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት፤የወጣቶችና አዋቂዎች ክህሎት ስልጠና ፤የአዋቂዎች ትምህርት፤ የፆታ እኩልነትና የትምህርት ጥራት መሰረታዊ መመዘኛዎች ናቸው።

እሸቴ በቀለ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ