1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ትንሽዋ ጫሪ "ከማጀት"

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 4 2004

በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ባለፉት ሳምንታት ዉስጥ በጥበብ እንኑር በሚል ባዘጋጁት ባህላዊ መድርክ ላይ በርካታ ኢትዮጵያዉያን በተገኙበት የተለያዩ ባህላዊ ዝግጅቶች መካሄዳቸዉን የሚያሳይ ቅንብር ይዘን መቅረባችን ይታወሳል።

https://p.dw.com/p/14c3u
ምስል picture alliance/dpa

በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ባለፉት ሳምንታት ዉስጥ በጥበብ እንኑር በሚል ባዘጋጁት ባህላዊ መድርክ ላይ በርካታ ኢትዮጵያዉያን በተገኙበት የተለያዩ ባህላዊ ዝግጅቶች መካሄዳቸዉን የሚያሳይ ቅንብር ይዘን መቅረባችን ይታወሳል። በዚህ ዝግጅት ላይ ኢትዮጵያን ፖየትሪ የተሰኝዉ በአለም ዙርያ የሚገኙ ግጥም አፍቃሪዎችን እና ገጣምያንን የሚያሰባስበዉ የፊስ ቡክ ገጽ ባቀረበዉ የግጥም ዉድድር ተሳታፊዎች ቁጥር እጅግ ብዙ እንደነበር ሲገለጽ፣ በጥበብ እንኑር በተሰኝዉ የባህል መድረክ ላያ የዉድድሩ የአሸናፊዎች ስም ይፍ ሆንዋል ግጥሞቻቸዉም በምስል ተቀናብረዉ ቀርበዉ እድምተኛዉን አስደምመዋል። የበጥበብ እንኑር የባህል መድረክ የስነ-ግጥም ዉድድር አሸናፊ መካከል የሶስተኝነትን መዓረግ የያዘጭዉ የ23 አመት ወጣት ሚሮን አባተ በተለይ በኢትዮጵያ ፖየትሪ ማለት በፊስ ቡክ የኢትዮጵያዉያን ገጣሚዎች መገናኛ መድረክ በምታቀርባቸዉ እጅግ ዉብ እና ልብ ኮርኳሪ ግጥሞችዋ ትታወቃለች።

Ägypten Kairo Boot auf dem Nil Hochhäuser
በካይሮ የአባይ ወንዝምስል RIA Novosti

የ 23 አመትዋ ወጣት ሜሮን አባተ በግብጽ መዲና በካይሮ መኖር ከጀመረች አራተኛ አመትዋን ልትይዝ ጥቂት ወራት እንደቀርዋት ትናገራለች። ከአገር ቤት ወደ ግብጽ አገር የሄደችዉ በሰዉ ቤት ተቀጥሮ ለማገልገል በኮንትራት ስራ ነዉ። ማንበብ መጻፍ በተለይ ስነ- ግጥም ከልጅነትዋ ጀምሮ የምትወደዉ ነገር ቢሆንም በአሁኑ ህይወትዋ ግጥም፣ጓደኛዋ ተስፋዋ መሆኑን ትገልጻለች። በምታገለግልበት ቤት ዉስጥ ጠዋት ማለዳ በአስራ አንድ እና አስራ ሁለት ሰአት ስራዋን ጀምራ ከምሽቱ አራት ሰአት ወደ መኝታዋ መሄድ ሲፈቀድላት ቀን ስራ ላይ በልቧ የጻፈችዉን በህልናዋ ያሰበችዉን በግጥም መልክ ወረቀት ላይ ታሰፍራለች። አሁን ደግሞ በኮንፒዉተር ፊስ ቡክ ኢትዮጵያን ፖየትሪ በተሰኝዉ ገጽ ላይ ግጥሞችዋን እያወጣች ብዙ ወዳጅ አድናቂ ወገንን አትርፋለች። ሜሮን እንዴት ይህን መድረክ ልታገኝ ቻለች፣ የግብጽ ህይወትዋና የግጥም ተሰጥዋን በተመለከተ ሰፋ ያለ ቃለ ምልልስ ሰታናለች፣ ሙሉዉን ቅንብር ያድምጡ

አዜብ ታደሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ