1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ትኩረት በአፍሪቃ

ቅዳሜ፣ ግንቦት 15 2001

የዛሬው ትኩረት በአፍሪቃ መሰናዶዋችን በዋናነት ሶማሊያ ላይ የሚያጠነጥን ይሆናል። በሙስና የተጨማለቁ ሶስት የአፍሪቃ መሪዎች ፈረንሳይ ውስጥ ክስ ሊመሰረትባቸው መሆኑንም ይመለከታል። ጋዜጦች ስለ አፍሪቃ በየአምዶቻቸው ያስነበቡትም ቅኝት ተደርጎበታል። ዝርዝሩ በአውሮጳ ወኪሎቻችን በድልነሳው ጌታነህና በይልማ ሀይለሚካኤል ቀርቧል።

https://p.dw.com/p/HvzC
የታሰሩ የባህር ላይ ወንበዴዎች
የታሰሩ የባህር ላይ ወንበዴዎችምስል AP

የዓለም የንግድ መርከቦችን ለከፍተኛ ችግር ያጋለጠውን የሶማሊያ የባህር ላይ ውንብድና ለማስቆም፤ ሃያላኑ መንግስታት የጦር መርከቦቻቸውን ግዙፍ መልህቆች ነቅለው ወደ ኤደን ባህረ-ሰላጤ ቀዝፈዋል። በቤልጂግ ብራስልስ ጉባኤ ተቀምጠዋል። የሱማሊያ መንግስት በሀገሩ ፀጥታን ያሰፍን ዘንድ፣ ብሎም የባህር ላዩን የውንብድና ስጋት ከምንጩ እንዲያደርቅ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ሊያሸክሙት ቃል ገብተዋል። የሶማሊያ የባህር ላይ ወንበዴዎች ግን በፈጣን ጀልባዎቻቸው መንቀዥቀዣቸውን ዛሬም ድረስ ሊያስቆማቸው የቻለ የለም። በድልነሳው ጌታነህ

ሰውዬው በአፍሪቃ ከአንደኛው ሐገር መሪ ቢሆኑም፤ በሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ዩሮ ፓሪስ ከተማ ውስጥ ባለ ዘጠኝ ክፍል የመኖሪያ ቪላ ገዝተዋል። ለአንዲት ሴት ልጃቸው ደግሞ ባለ ሰባት ክፍል ቤት ከነመዋኛ ገንዳው እዚያው ፓሪስ ውስጥ በጅ ብለዋታል። ሰውዬው ገንዘባቸው በቀላሉ የሚያልቅ አይመስልም። ለወንድማቸው ልጅ ደግሞ፤ እነ ማርቼዲስና ፖርሼን ጨምሮ፤ ሰባት መኪናዎችን ሲያሻህ እንደጫማ ቀያይራቸው ሲሉ ቁልፎቹን አስረክበውታል። በሙስና የሚዘረፍ የአፍሪቃ ገንዘብ አውሮጳ ላይ እንዲህ በቀላሉ የሚሟጠጥ አይመስልም። በይልማ ሀይለሚካኤል

ድልነሳው ጌታነህና/ይልማ ሀይለሚካኤል

ማንተጋፍቶት ስለሺ