1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ትኩረት በአፍሪካ

ቅዳሜ፣ ነሐሴ 29 2002

ሶማሊያ ብጥብጡ አይሏል። የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ኃይል ተጨማሪ ጦር አግኝቷል። በሌላ በኩል ሩዋንዳ ከመንግስታቱ ድርጅት ጋር ፍጥጫ ውስጥ ገብታለች።

https://p.dw.com/p/P4N1
ምስል AP

የሮመዳን ወር ከተጀመረ አንስቶ የሶማሊያ ብጥብጥ አይሏል። የሰላም አስከባሪው የአፍሪካ ህብረት ሰራዊት ከመቼው ገዜ በላይ ፈተና ውስጥ የገባበት ጊዜ አሁን ነው። የሶማሊያ ብጥብጥ እየተጋጋለ ባለበት በአሁ ጊዜ ኡጋንዳ ተጨማሪ ጦር ለመላክ ዝግጁ መሆኗን አስታውቃለች። አሁን ሞቃዲሾ የሚገኘው 6ሺህ የኡጋንዳና የቡሩንዲ ጦር ከአልሸባብ ጋር አንገት ለአንገት እየተናነቀ፤ የሽግግር መንግስቱ ጨርሶ እናዳይወገድ መስዋዕት እየከፈለ ይገኛል። በእስቸኳይ አቅሙ በሰው ኃይልና በገንዘብ ከልተጠናከረ የአልሸባብን ጥቃት በቀጣይ መመከት ስለመቻሉ ብዙዎችን ጥርጣሬ ውስጥ ከቷል። በሌላ በኩል ሩዋንዳ ጦሯን ከዳርፉር ልታስወጣ እንደምትችል አስጠነቀቀች። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሩዋንዳ ጦር የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚጠየቅበት ሪፖርት እያዘጋጀ መሆኑ ነው ሩዋንዳን ያስቆጣት።

መሳይ መኮንን

ሸዋዬ ለገሠ