1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሴኔጋላዊትዋ የፈረንሳይ መንግሥት ቃል አቀባይ

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 1 2011

የዛሬ ሦስት ዓመት ፈረንሳዊ ዜግነትን የተቀበሉት የ39 ዓመትዋ የፈረንሳይ መንግሥት ቃል-አቀባይ ሲቢት ናዳይ፤ ትምህርታቸዉን የተከታተሉት ፈረንሳይ ዉስጥ ነዉ። በጎርጎረሳዉያኑ 2017 ዓ.ም የምርጫ ዘመቻ የኤማኑኤል ማክሮ የማኅበራዊ መገናኛና የኮሚዩኒኬሽን ቡድንን በኃላፊነት በመምራት የአሁኑ ፕሬዚዳንት ማክሮ ላገኙት ድል ከፍተኛ ሚናም ተጫዉተዋል።

https://p.dw.com/p/3GVnW
Frankreich Sibeth NDiaye
ምስል Getty Images/AFP/E. Feferberg

ፕሬዚዳንት ማክሮ ለመመረጣቸዉ ከፍተኛ ሚናን ተጫዉተዋል

በትዉልድ ሴኔጋላዊት የሆኑት አዲስ ተመረጭዋ የፈረንሳይ መንግሥት ቃል-አቀባይ በዚህ ሥልጣን ላይ የመጀመርያዋ ጥቁር በመሆናቸዉ ሰሞኑን የፈረንሳይ ፖለቲካ መድረክ ብሎም የመገናኛ ብዙኃንን ትኩረትን ስበዉ ነዉ የሰነበቱት። የዛሬ ሦስት ዓመት ፈረንሳዊ ዜግነትን የተቀበሉት የ39 ዓመትዋ  የፈረንሳይ መንግሥት ቃል-አቀባይ ሲቢት ናዳይ፤ ትምህርታቸዉን የተከታተሉት ፈረንሳይ ዉስጥ ነዉ።  ሲቤት ናዳይ በሴኔጋል ጠንካራ የፖለቲካ መሰረት ያላቸዉ ወላጆቻች አላቸዉ።  በጎርጎረሳዉያኑ 2002 የሶሻሊስት ፓርቲ አባል በመሆን የፈረንሳይን የፖለቲካ መድረክን የተቀላቀሉትም ገና በአፍላ እድምያቸዉ ነበር። በጎርጎረሳዉያኑ 2017 ዓ.ም በፈረንሳይ በተካሄደ የምርጫ ዘመቻ የኤማኑኤል ማክሮ የማኅበራዊ መገናኛና የኮሚዩኒኬሽን ቡድንን በኃላፊነት በመምራት የአሁኑ ፕሬዚዳንት ማክሮ ላገኙት ድል ከፍተኛ ሚናም ተጫዉተዋል። ሲቤት ናዳይ በሥራ ታታሪ እና ጠንካራ ይሁኑ እንጂ ለጋዜጠኞች የማይመቹ ናቸዉ የሚሉ ትችቶችም ይሰነዘሩባቸዋል። ፕሬዚዳንት ማክሮ ሲቤትን በዚህ ስልጣን ላይ መሾማቸዉ በሚቀጥለዉ ወር በአዉሮጳ ኅብረት በሚካሄደዉ የፓርላማ ምርጫ ሃገር ዉስጥ ከፍተኛ ፉክክር ስለሚጠብቃቸዉ ያደረጉት ስልታዊ ርምጃ  ነዉ ተብሎአል። ፕሬዚደንቱ በዚህ ርምጃቸዉ ምናልባትም በምርጫዉ የአፍሪቃና የአረብ ዝርያ ካላቸዉ ፈረንሳዉያን ከፍተኛ ድምፅን ሊያገኙ ይችላሉ ተብሎአል። የፓሪስዋ ዘጋብያችን ስለአዲስዋ የፈረንሳይ መንግሥት ቃል አቀባይ ማንነት አጠር ያለ ዘገባ ልካልናለች።  


ሃይማኖት ጥሩነህ     


አዜብ ታደሰ 
ነጋሽ መሐመድ