1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ እጩ

ዓርብ፣ መጋቢት 2 2008

በደቡብ ጀርመን ፤ ኑርንበርግ ከተማ በሚመጣው እሁድ ምርጫ ይካሄዳል። ምርጫው የውጭ ዜጎችን ከህብረተሰቡ ጋር ለማዋሃድ ለሚሰራው ምክር ቤት ሲሆን፤ ለዚህ ምርጫ እጩ ሆኗ አንዲት ትውልደ ኢትዮጵያዊት ቀርባለች።

https://p.dw.com/p/1IBJc
Kalkidan Bezabih
ምስል privat

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ እጩ

በደቡብ ጀርመን የባየርን ግዛት የኑርንበርግ ከተማ ትገኛለች። ግማሽ ሚሊዮን ገደማ ነዋሪ ያላት ከተማ ፤ ከጀርመን 15 ትልቅ ከተሞች አንዷ ናት። በዚች ከተማ ደግሞ የውጭ ዜጎችን ከህብረተሰቡ ጋር ለማዋሃድ የሚሰራው ምክር ቤት እሁድ ዕለት ምርጫ ያካሂዳል። ለምርጫ ከቀረቡት መካከል ትውልደ ኢትዮጵያዊት ቃልኪዳን በዛብህ አንዷ ናት።

ቃልኪዳንን ጨምሮ 81 እጩዎች ለምርጫ ቀርበዋል።ከነዚህም 33ቱ በመጨረሻ ተመራጭ ይሆናሉ።እጩዎቹ የውጭ ዜጎች ወይም የውጭ ዜግነት የነበራቸው እና ከጊዜ በኋላ ጀርመናዊ የሆኑ ናቸው። ቃልኪዳን በምትኖርበት የኑርንበርግ ከተማ ከተለያዩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ማህበራት እና ድርጅቶች ጋር በበጎ ፍቃደንነት ስታገለግል ቆይታለች። ስለሆነም ብትመረጥ የሚጠብቃት ስራ ብዙም አዲስ እንደማይሆንባት ነው የምትናገረው።በደቡብ ጀርመን ፤ ኑርንበርግ ከተማ የውጭ ዜጎችን ከህብረተሰቡ ጋር ለማዋሃድ ለሚያገለግለው ምክር ቤት እጩ ሆና በመወዳደር ላይ ከምትገኘው ትውልደ ኢትዮጵያዊት ቃልኪዳን በዛብህ ጋር የነበረንን ሙሉ ቃለ መጠይቅ በድምፅ ያገኙታል።


ልደት አበበ
ነጋሽ መሀመድ