1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«ትግራይ በተናጠል ምርጫውን ታካሂዳለች»ዶክተር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል

ሐሙስ፣ ግንቦት 6 2012

የትግራይ ክልላዊ መንግስት በተናጥል ምርጫ እንደሚያካሂድ የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ተናገሩ፡፡ የብልፅግና ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሐላፊ አቶ አወሉ አብዲ የትግራይ ክልል መንግስት በክልሉ ምርጫ ማድረግ አይችልም ፤ ካደረገም መንግሥት አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

https://p.dw.com/p/3cDz1
Äthiopien Addis Abeba | Debretsion Gebremikial, TPLF
ምስል DW/M. Hailesilasie

የትግራይ ክልል ምርጫውን በተናጥል እንደሚያካሂድ ገለጸ

የትግራይ ክልላዊ መንግስት በተናጥል ምርጫ እንደሚያካሂድ የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ተናገሩ፡፡ ዶክተር ደብረፅዮን ለክልሉ መንግስታዊ መገናኛ ብዙሐን በሰጡት መግለጫ በሀገር ደረጃ ምርጫ ማካሄድ አይቻልም ተብሎ የሚደመደም ከሆነ ህዝብና የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያሳትፍ ምክክር መደረግ አለበት ብለዋል፡፡ የፌደራሉን መንግስት የሚመራው የብልፅግና ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሐላፊ አቶ አወሉ አብዲ በበኩላቸው የትግራይ ክልል መንግስት በክልሉ ምርጫ ማድረግ አይችልም ፤ ካደረገም መንግሥት አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል ሲሉ አስጠንቅቀዋል። 

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

ታምራት ዲንሳ

አዜብ ታደሰ