1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቻይና እና ያወጣችው የሰብዓዊ መብት የተግባር ዕቅድዋ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 9 2001

ቻይና ለሀገርዋ የመጀመሪያ የሆነውን የሰብዓዊ መብት የተግባር ዕቅድ አወጣች።

https://p.dw.com/p/HYTn
ምስል picture-alliance / dpa

በዚሁ ዕቅድ መሰረት፡ መንግስት የሴቶችንና የውሁዳን ብሄረሰቦችን መብት ለማስከበር፡ ለአካል ተጎጂዎች አስፈላጊውን እንክብካቤ ለመስጠት፡ የጸጥታ ኃይላት በእስረኞች ላይ ይፈጽሙታል የሚባለው የቁም ስቅል ማሳያ ተግባርን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ጥረት እንደሚያደርግ ተመልክቶዋል። በዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት በአምነስቲ ኢንተርናሽናል ባልደረባ በወይዘሮ ቬሬና ሀርፐር አስተያየት፡ ይኸው የተግባር ዕቅድ ጥሩ ርምጃ ሊባል የሚችለው በተግባር ተተርጉሞ ሲታይ ብቻ ነው።

ይልማ ኃይለሚካኤል/አርያም ተክሌ/ሸዋዬ ለገሠ