1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኒዠር እና አሳሳቢው የረሀብ አደጋ

ቅዳሜ፣ ሐምሌ 16 1997

ምዕራብ አፍሪቃዊቱ ሀገር ኒዠር አሳሳቢ የረሀብ አደጋ ተደቅኖባታል። ከሁለት ሚልዮን የሚበልጥ ሕዝቧም አስቸኳዩ የምግብ ርዳታ ይቀርብለት ዘንድ ዓለም አቀፍ የርዳታ ድርጅቶች ባቀረቡት ጥሪ መሠረት፡ ርኣታው ቀስ በቀስ መቅረብ ይዞዋል። ግን፡ ይኸው ዘግይቶ መቅረብ የጀመረው የምግብ ርዳታ ተጎጂውን ሕዝብ ከተደቀነበት የመሞት ሥጋት ሊያድነው መቻሉ እያጠራጠረ ነው የተገኘው።

https://p.dw.com/p/E0ji