1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ናይሮቢ-የአፍሪቃ ቀንድ ችግረኞችና የእርዳታ ጥያቄ

ሐሙስ፣ ሰኔ 26 2000

ናይሮቢ-የአፍሪቃ ቀንድ ችግረኞችና የእርዳታ ጥያቄ

https://p.dw.com/p/EVbq

በአፍሪቃ ቀንድ ሐገራት ለረሐብ የተጋለጠዉ ሕዝብ አቸኳይ እርዳታ ካልደረሰዉ ባካባቢዉ ከፍተኛ ሠብአዊ ድቀት እንደሚከሰት የርዳታ ድርጅቶች አስጠነቀቁ።አለም አቀፉ የሕፃናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) ን ጨምሮ ዘጠኝ ግብረ-ሠናይ ድርጅቶች ዛሬ በጋራ ባወጡት መግለጫ እንዳሉት ድርቅ፥ግጭት፥ የምግብና የነዳጅ ዘይት ዋጋ ንረት፥ በሽታና ድሕነት ተደራርበዉ አስራ-አራት ሚሊዮን የሚገመት የአፍሪቃ ቀንድ ሕዝብን ወደ አስከፊ ድቀት እየገፉት ነዉ።በምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪቃ የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት ተጠሪ ፐር ኤንገባክ እንዳሉት ለከፋ ችግር የተጋለጡትን «ሕፃናት ሕይወት ለማዳን» የመረባረቢያዉ ጊዜ አሁን ነዉ።በተደራራቢዉ ችግር ክፉኛ የተጎዱት ሶማሊያ፥ ኢትዮጵያና ኬንያ ናቸዉ።።ሶማሊያ ዉስጥ 3.5 ሚሊዮን፥ ኢትዮጵያ 4.6 ሚሊዮን ኬንያ ዉስጥ 1.2 ሚሊዮን ሕዝብ አስቸኳይ ርዳታ ያስፈልገዋል።የከፊል ኤርትራ፥ የጁቡቲ፥ እና የዩጋንዳ ሕዝብም ተመሳሳይ ችግር እየታየበት ነዉ።