1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ናይጀሪያና ኤኮዋስ

ሐሙስ፣ ኅዳር 6 2005

ባለፈው እሁድ በናይጀሪያ መዲና በአቡጃ የተካሄደው በማሊ ላይ ያተኮረው ጉባዔ፣ የምዕራብ አፍሪቃ የኤኮኖሚ ማኅበረሰብ አባላት የሆኑ አገሮችጦር እንዲያዝምቱ ስምምነት ላይ በመድረስ ነበረ የተደመደመው። ናይጀሪያ ታሪካዊ የመሪ ኀላፊነት አለብኝና

https://p.dw.com/p/16jaQ
ምስል PIUS UTOMI EKPEI/AFP/Getty Images

ጦሩን በበላይነት ካልመራሁ! ብላለች። ይሁን እንጂ ናይጀሪያ የራሷን ፀጥታ ማስከበር የቻለች ሀገር እንዳልሆነች በቅርቡ ታሪኳ በተደጋጋሚ እየታየ ነው። ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ በሰሜናዊው የአገሪቱ ከፊል ሰዎች በኃይል በተወሰደ እርምጃ መገደላቸው የሚታወስ ነው። አደጋ ጣዩ ባለፉት 2 ዓመታት አገሪቱን በማመስ ላይ የሚገኘው ቦኮ ሃራም የተባለው አክራሪ እስላማዊ ድርጅት ነው። ፊሊፕ ባርት፣ ናይጀሪያ በ ኤኮዋስ ይገባኛል ስለምትለው የመሪነት ድርሻና የውስጥ ችግሯ ያቀረበውን ዘገባ ተክሌ የኋላ እንደሚከተለው አጠናቅሮታል።

Mali Norden Kämpfer
ምስል AP

ናይጀሪያ በአሁኑ ጊዜ በራሷ ችግሮች እንደተጠመደች የምትገኝ ሀገር ናት። የኃይል እርምጃ የተከሠተባቸው ውዝግቦች፤ በኒጀር ደለል የመገንጠል ጥያቄ ያነሱ ኃይሎችና ከመደበኛው የእሥልምና ሃይማኖት ያፈነገጠው ቦኮ ሃራም የተሰኘው ሐራጥቃ በሰሜናዊው የእገሪቱ ክፍል አሸባሪ እርምጃ ከመውሰድ አልቦዘነም። ፖሊሶችና ጦር ሠራዊቱ ፣ ፀጥታ ለማስከበር ከመንቀሳቀስ ያረፉበት ጊዜ የለም። አሁን ኤኮዋስ የፀጥታ አስከባሪ ኃይል መሪ ይሻል። ማኅበረሰቡ፣ 3,300 ወታደሮች ወደ ሰሜን ማሊ ለመላክ ተዘጋጅቷል።

በዚያ አክራሪ ሙስሊሞች ክፍለ ሀገሩን በኃይል መቆጣጠራቸው የሚታወስ ነው። የፖለቲካ ምሁርና የ ኤኮዋስ ጉዳዮች ዐዋቂ ጆናታን አሬሙ ---

1,«በኒጀር ደለልም ሆነ ቦኮ ሃራም በሚንቀሳቀስበት በሰሜን፤ ምንም ዓይነት ሁኔታ ያጋጥም፤ናይጀሪያ ባጠቃላይ ፣ በምዕራብ አፍሪቃው የኤኮኖሚ ማኅበረሰብ ያላትን የመሪነት ድርሻ አያደበዝዘውም። »

በኤኮኖሚ ፤ አዎ የመሪነት ቦታዋ የሚያጠራጥር አይደለም። በውትድርናው ግን እንደድሮው አይደለም ባይ ናቸው የበናይጀሪያ ጉዳዮች ላይ ተመራማሪ የሆኑት ሃይንሪኽ በርግእሽትረሰር! ጦር ሠራዊቱ፤ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሥር፣ በዳርፉር ሱዳን ፀጥታ የማስከበር ኀላፊነትን በመወጣት ላይ ሲሆን፣ በሰሜናዊው የአገሪቱ ክፊል ከቦኮ ሃራም ጋር የሚያደርገው ግብግብ ፋታ አሳጥቶታል። AI እንደገለጸው፤ ጦር ሠራዊቱ በራሱ ዜጎች ላይ የጭካኔ ተግባር ከመፈጸም አልተቆጠበም። የብሪታንያው ዕለታዊ ጋዜጣ ዘ ጋርዲያን የናይጀሪያ ጦር ኃይል፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ ፣ እጅግ ቀላል የሚሰኝ ተልእኮ ቢሰጠውም እንኳ በብቃት ማከናወን የሚችል አይደለም። --ሃይንሪኽ በርግእሽትረሰር---

Ansar Dine Kämpfer in Mali
ምስል REUTERS

2,«ይህ እርስ በርሱ የሚቃረን ዐቢይ ጉዳይ ነው። ውስጣዊው ህገመንግሥታዊ የፀጥታ አያያዝና ናይጀሪያ በውጭው ዓለም ያላት ግምት! በተለይ በውትድርናው መስክ፤ ይህን አከራካሪ ዐቢይ ጉዳይ አሁን ከሞላ ጎደል፣ ያሉ ጉድለቶችን ተገንዝበው በርጋታ መመልከቱን መርጠዋል። ይህንም ሲያደርጉ ሁኔታዎች ከአቅም በላይ እንደሆኑባቸው በመገንዘብ ነው። »

የመሪነቱን ሚና እርግፍ አድርጎ ለመተው፤ ለትልቋ ምዕራብ አፍሪቃዊቷ ሀገር ከባድ ነው። ይህ ሚናዋ ደግሞ በታሪክ እየጎላ በመምጣት ላይ የነበረ ነው። ናይጀሪያ እ ጎ አ በ 1975 የምዓራብ አፍሪቃው የኤኮኖሚ ማኅበረሰብ እንዲመሠረትና ዋና ጽ/ቤቱ በመዲናዋ በአቡጃ እንዲሆን አበቃች።በ 1990ኛዎቹ ዓመታት የመጀመሪያውን የ ኤኮዋስ ወታደራዊ ተልእኮ በላይቤሪያ በበላይነት ነበረ የመራች።

ቁጥሩም ይናገራል። ከገሚሱ በላይ የሚሆኑት የአባል ሃገራቱ ዜጎች ናይጀሪያውያን ናቸው።የናይጀሪያ ኤኮኖሚ፤ የሪዎቹ 14 የማኅበረሰቡ አባል ሀገራት ተደምሮም ቢሆን የአርሷ ነው የሚበልጠው። የ ኤኮዋስን 2/3ኛ በጀት የምትከፍለው ራሷ ይጀሪያ ናት።

ባለፉት 10 ዓመታት በናይጀሪያ ሙስና እጅግ ሥር በመስደዱ፤ መጠነ ሰፊ የማኅበራዊ ኑሮ ችግር ከማስከተሉም፤ ሞራላዊ ተዓማኒነትን አሳጥቷል ፣ ስለሆነም፤ ሃይንሪኽ በርግእሽትረሰር እንደሚለው፣ በአካባቢው አገሮች፤ የመሪነት ድርሻ ሊኖረኝ ይገባል በሚለው አቋሟ ላይ ችግር ደቅኗል።

Nigeria - Armee im eigenen Land
ምስል picture-alliance/dpa

እንግሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪዪቱ ናይጀሪያ፣ በኮት ዲቯርና ቶጎ ውዝግቦችን ለማስወገድ ሚዛኑን የሚደፋ ድርሻ ለማበርካት ሳትችል መቅረቷ፣ በአርሷና ፈረንሳይኛ ቋንቋ በሚናገሩ አገሮች መካከል ልዩነቱን አስፍቶታል። በ ECOWASS እንግሊዝኛና ፈረንሳይኛ ቋንቋ ተናጋሪ ሃገራት፤ በቀድሞ ቅኝ ገዥዎቻቸው መርኅ ነው ለመጓዝ እስካሁን ጥረት የሚያደርጉት። አሁንም ሃይንሪኽ በርግእሽትረሰር-----

3,«ፈረንሳይኛና እንግሊዝኛ በሚናገሩ፤( በፍራንኮፎንና አንግሎፎን ) የምዕራብ አፍሪቃ አገሮች መካከል ባለፉት ዓመታት አከራካሪ ጉዳዮች እየጎሉ መጥተዋል።እናም ናይጀሪያ ከዚህ ቀደም ባደረገችው አስተዋጽዖ ሳቢያ የአመራሩ ድርሻ ለኔ ይገባል ማለቷ እንደማያዛልቅና የአካባቢው ኀያል መንግሥት መሆን የመቻልዋ ትልም ሊደፈን እንደማይችል ሳትገነዘብ አልቀረችም።»

ናንይጀሪያ፤ ሞራላዊ ተዓማኒነትም ፣ሆነ፣ ወታደራዊ የማጥቃት ኃይል የላትም።

የሆነው ሆኖ ወደ ማሊ ከሚላከው ከ 3,3000 ው ወታደሮች ላቅ በሚለው ጦር ሠራዊት፣ በዛ ያሉትን ራሷ ለማዋጣት ትፈ።ልጋለች። ኤኮዋስ ባለፈው እሁድ አቡጃ ላይ እንዳስታወቀው፣ ናይጀሪያ ከ 13 የአፍሪቃ አገሮች ዓለም አቀፍ ተባባሪ ኃይልም ሆነ ተልእኮ ጎን ትሰለፋለች። ከጆስ ዩንቨርስቲ፣ ቪክቶር አዴቱላ እንዲህ ብለዋል።

Guido Westerwelle zum Besuch beim nigerianischen Präsident Goodluck Jonathan in Abuja Nigeria
ምስል DW/Ubale Musa

4,«ናይጀሪያ በምዕራብ አፍሪቃ የተለያዩ አገሮች፤ ለሰላም መቆሙን ትገፋበታለች። ያም ሆኖ፤ እዚህ ላይ አንድ ነገር መገንዘብ የግድ ይላል። ለብቻ ጉዳዮችን መፈጸም እንደማይችል ከዚህ ቀደም ከተካሄዱ ድርጊቶችም ሆነ የሠራዊት ሥምሪቶች ለመገንዘብ ችላለች። የሌሎቹን የምዕራብ አፍሪቃ አገሮች ድጋፍ ማግኘት ያሻል። ጥቅሞችናን የዓለምአቀፉን የመርኅ ሥርዓት የጥቅም ፍለጋ ጥንካሬንም ከልብ ማጤን ያስፈልጋል።»

የአውሮፓው ኅብረት ነገ፤ ቃል በገባው መሠረት ሠራዊት ለማሠልጠን በሚልካቸው ጠበብት ጥያቄ ይመክራል። እ ጎ አ በኅዳር ወር ማለቂያ፤ የተባበሩት መንግሥታት፣ እና የአፍሪቃ ኅብረት፤ በአቅዶች ላይ ውሳኔ ያሳላፍሉ። ከዚያም በኋላ፤ የሰሜን ማሊን ፀጥታና መረጋጋት የሚያረጋግጡ ወታደሮች ይሠማራሉ።

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ