1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኖቤል የሠላም ተሸላሚዎች-ሰወስትም-አንድም ሆኑ

ሰኞ፣ መስከረም 29 2004

ለኤለን ጆንሰን ሰርሌፍ፥ ለሌይማሕ ግቦዌና ለተወኩል ከርማን እኩል እንዲከፈል ወስኗል

https://p.dw.com/p/RqBf
ምስል picture-alliance/dpa

ሁለቱ ያንድ ሐገር ልጆች ናቸዉ።ግን የሩቅ ለሩቅ ዘመን ዉልዶች።እሷ ስትወለድ-እሳቸዉ ምክትል የገንዘብ ረዳት ሚንስትር ነበሩ።1972 (ዘመኑ በሙሉ እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር ነዉ።)እሷ ሰባተኛ ዓመት ልደትዋን ስታከብር ሰወስተኛዋ ተወለደች።የማይተዋወቅ ቤተ-ሰሰብ፥ የሩቅ ለሩቅ ዘመን ግኝቶቹ ለየብቻቸዉ ያነገቡት አላማቸዉ አቀራረባቸዉ።የትግል ዉጤት አንድ አደረጋቸዉ።ሽልማት ኖቤል።

የኖርዌ የኖቤል ኮሚቴ የሁለት ሺሕ አስራ-አንዱ ኖቤል የሰላም ሽልማት ለሴቶች ደሕንነት፥ ሠላምን ለማስፈን ሴቶች ሙሉ ተሳትፎ እንዲያደርጉ በሠላማዊ መንገድ ለታገሉት ለሰወስቱ፥-ለኤለን ጆንሰን ሰርሌፍ፥ ለሌይማሕ ግቦዌና ለተወኩል ከርማን እኩል እንዲከፈል ወስኗል።በሁሉም የማሕበረሰብ ደረጃ ልማትን ለማስፋፋት ሴቶች ከወንዶች እኩል ተፅዕኖ ማድረግ ካልቻሉ ዴሞክራሲና ዘላቂ ሠላም ማስፈን አንችልም።»
ቶርብዮርት ያግላንድ፥-የኖርዌ የኖቤል ኮሚቴ ሊቀመንበር።አርብ።
የሰወስቱ መሸለም መነሻችን፦ የሰወስትም-አንድም ትግላቸዉ እንዴትነት መድረሻችን ነዉ ላፍታ አብራችሁን ቆዩ።

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ