1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አለም አቀፍ የሠራተኛ ጉባኤና የኢትዮጵያ መምሕራን

ሐሙስ፣ ሰኔ 4 2001

አቶ ገሞራዉ ዤኔቭ የመምጣቸዉ ሰበብም-የኢትዮጵያ መንግሥት በነፃ መደራጀት በሚሹ መምሕራን ላይ ያደርሰዋል ያሉትን በደል ከመላዉ አለም ለተወከሉ ጉባኤተኞች ለማቅረብ ነዉ።

https://p.dw.com/p/I7Xo
ምስል AP GraphicsBank

11 06 09

የኢትዮጵያ መንግሥት በነፃ መደራጀት በሚሹ መምሕራን ላይ የሚያደርሰዉን በደልና ወከባ ያቆም ዘንድ አለም አቀፍ ማሕበራትና ድርጅቶች ግፊት እንዲያደርጉበት እራሱን ብሔራዊ የአስተማሪዎች ማሕበር ብሎ የሚጠራዉ ተቋም አስተባባሪ ጠየቁ።ኢትዮጵያ ዉስጥ ሕጋዊ ፍቃድ ያልተሰጠዉን ማሕበር የሚያስተባብሩት አቶ ገሞራዉ ካሳ ዤኔቭ-ሲወዘርላንድ በተያዘዉ አለም አቀፍ የሠራተኞች ጉባኤ ላይ እየተካፈሉ ነዉ።አቶ ገሞራዉ ለዶቸ ቬለ እንደገለፁት የኢትዮጵያ መንግሥት በነፃ መደራጀት በሚሹ መምሕራን ላይ ያደርሰዋል ያሉትን በደል ለጉባኤተኞች እያስረዱ ነዉ።ነጋሽ መሐመድ ዝር ዝሩን አጠናቅሮታል።


በ1941 ግድም የተመሠረተዉ የኢትዮጵያ መምሕራን ማሕበር (ኢመማ) ሕጋዊነት፥ የአባላቱ ፍላጎት፤ የመሪዎቹ ማንነት፥ አስራ-ስድስት አመት ሲያወዛግብ፥ ሲያሟግት፥ አንዳዴም ሲያጋጭ ቆይቷል።ባለፈዉ አመት ሰኔ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት ከዚያ በፊት የተላለፉ ዉሳኔዎችን በሙሉ ሽሮ እሁለት ከተገመሱት የማሕበሩ መሪዎች በመንግሥት ይደገፋሉ ለሚባሉት ፈረደ።
ፍርዱ ግን በአቶ ገሞራዉ ካሳ ቋንቋ የመምህሩን ልብ አልነጠቀም።
ድምፅ
ፍቃድ ግን አላገኙም።ሌሎች የተለያዩ ምክንያቶች ጠበቃቸዉ።እንደገና የፍርድ ቤት ሙግት ገጠሙ።የአለም መምሕራን ማሕበርንና የአለም ሠራተኞች ድርጅትን የመሳሰሉት አለም አቀፍ ተቋማት ግን እስካሁን ድረስ የሚያዉቁት ፍቃድ፥ ፅሕፈት ቤት የሌለዉን እንጂ በመንግሥት ድጋፍ የተመሠረተዉን ማሕበር አይደለም።
ድምፅ
የኢትዮጵያ መንግሥት እሁለት የተከፈሉትን ወገኖች ከማቀራረብ ይልቅ ላንደኛዉ ሙሉ ድጋፍ እየሰጠ ሌለኛዉ የማግለሉ ሰበብ ለሩቁ በርግጥ ግራ አጋቢ ነዉ-የሚመስለዉ።አቶ ገሞራዉ ግን ግልፅ ነዉ-ይላሉ።
ድምፅ
በዚሕም ምክንያት ይላሉ አቶ ጎሞራዉ መንግሥት ሊያስከብረዉ የሚገባዉን ሕገ-መንግሥት ሳይቀር እየጣሰ ነዉ።
ድምፅ
አቶ ገሞራዉ ዤኔቭ የመምጣቸዉ ሰበብም-የኢትዮጵያ መንግሥት በነፃ መደራጀት በሚሹ መምሕራን ላይ ያደርሰዋል ያሉትን በደል ከመላዉ አለም ለተወከሉ ጉባኤተኞች ለማቅረብ ነዉ።
ድምፅ
98ኛዉ አለም አቀፍ -የሰራተኛ ጉባኤ የተጀመረዉ ባለፈዉ ሳምንት ሮብ ነበር።ከአራት መቶ በላይ የማሕበራትና የድርጅቶች ተወካዮች ተካፍለዉበታል።በመጪዉ ሳምንት ሐሙስ ያበቃል።

ነጋሽ መሐመድ/ሸዋዬ ለገሠ