1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አሜርካ የአርባ ምንጭ የአየር ጣብያዋን ዘጋች

Merga Yonas Bulaማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 26 2008

የዩናይትድ ስቴትስ አየር ኃይል ከአዲስ አበባ 400 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘዉ በአርባ ምንጭ ከተማ በመሠረተዉ ጦር ሠፈር አልሸባብና ሲወጋ ነበር።

https://p.dw.com/p/1HYUB
MQ-9 Reaper Drohne Drohnenkrieg Ziel Drohnenangriff Afghanistan
ምስል picture-alliance/AP/Air Force/L. Pratt

[No title]

ከመጀመርያዉ ይህ የአየር ጣቢያ የሲቢል የነበረ ቢሆንም በጎርጎሪዮስ አቆጣጠር 2010 የዩናይትድ ስቴትስ ከኢትዮጵያ ተረክባ በሚሊዮን በሚቆጠር ዶላር ወጪ የአየር ጣብያዉን አሻሽላ የሰዉ አልባ አዉሮፕላን መዝመቻ ጣብያ አድርጋዋለች።

ይሁንና አየር ጣቢያዉ ለአሜሪካ ጦር ኃይል ለዉጊያ አገልግሎት መዋሉን የአሜሪካም ሆኑ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት እስካሁን ድረስ አላመኑም ነበር። አልፎ አልፎ ብልጭ ያሉ ዘገቦችም አየር ጣቢያዉ ለዉጊያ ሳይሆን መረጃዎችን ለመሰብሰብ ብቻ እንደሚዉል ሲያወሱ ነበር። ይሁንና ላለፉት አራት ዓመታት ከአርባ ምንጭ የሚነሱ የአሜሪካ ሰዉ አልባ አዉሮፕላኖች የቀድሞዉን የአል ሸባብ መሪ አሕመድ አብዲ ጎዳኔን ጨምሮ በርካታ ሰዎችን ገድለዋል።ሌሎች በርካታዎችን አቁስለዋል።በጥቃቱ ከታጣቂዎች በተጨማሪ ሠላማዊ ሰዎች መጎዳታቸዉንም ዘገባዎች ያትታሉ።

Karte Äthiopien englisch

የአየር ጦር ሠፈሩ አሁን የተዘጋበት ምክንያት ልክ ሲከፈት እንደነበረዉ ሁሉ ግልፅ አይደለም።መዘጋቱን ግን የአሜሪካ ባለሥልጣናት አረጋግጠዋል።በአዲስ አበባ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባስ የመረጃ እና የፕሬስ ሐላፊ ካቴርን ዲኦፕ ለዶቼ ቬሌ በለኩት ኢሜል፤ የአሜርካ ጦር ሃይል አርባምንጭን ለቆ እንደሄደ ካብራሩ በዋላ ይህ የሰዉ አልባ አዉሮፕላን ጣብያዉን ለመዝጋት ምክንያት የሆነዉ በሁለቱ ሐገራት የመከላከያ ስምምነት ላይ ተመስርቶ ነዉ ብለዋል።ዲኦብ አክለዉም «የአርባ ምንጭ ቆይታችን ከዚሕ በዋላ እንደማያስፈልግ ዉሳኔ ላይ ደርሰናል» ብለዋል።ለአሜሪካ ጦር የአርባ ምንጭ ቆይታዉ መጀመርያዉኑ ጊዚያዊ ሞሆኑን ባለሥልጣንዋ አትቶዋል።


ይህ የሰዉ አልባ የአየር ጠብያ መዘጋት ምክንያት ሊሆን ይችላል የሚሉት የምስራቅ አፍሪቃ የሰላም እና የደህነት ባለሙያ የሆኑት ዶክተር መሐሪ ታደለ ሲናገሩ፣ «በሶማሊያ መንግስት ቁጥጥር ወይም AMISOM-የአፍርቃ ህብረት የሰላም አስከባሪ ወታደሮች በሶማሊያ የሚቆጣጠራቸዉ ቦታዎች በጣም እጅግ የተወሰኑ፣ ለጥቃት የተጋለጡ ነበሩ። አሁን ይሄ ሁኔታ በተወሰነ ሁኔታ ተቀይሮዋል። አሁን ጥቃቶች ቢኖሩም ግዛቶችን በከፍተኛ ደረጃ በመቆጣጠር አልሸባብ በይፋ ተቆጣጥሮዋቸዉ መንቀሳቀስ የሚችሉ አይደሉም። አሁን የኃይል ሚዛኑ ወደ አሚሶም እና ሶማሊያ መንግስት ዞሯል። በዚህ ምክንያት ምናልባት የምገምተዉ እዛዉ በሶማሊያ ዉስጥ ጦር ሰፈር መስርተዉ ይሆናል። ይሄ ሁኔታ ካለ በብዙ መልኩ ለአሜሪካ ጠቀሜታ ይኖራዋል፤ በቅርበትም ለመከታተል እና መረጃዎችን ለማግኘት ከአርባ ምንጭ ይልቅ።»


በፀረ ሽብር ዘመቸዉ የዩናይትድ ስቴትስ የቅርብ አጋር የሆነችዉ ኢትዮጵያ በጎርጎሮስያዉያኑ አቆጣጠር 2006 ጀምሮ በሶማሊያ ጦርነት ከፍተኛ ሚና እየተጫወተች ትገኛለች። ይሁን እንጂ የሰዉ አልባ የአየር ጣብያ ለመክፈት የተደረጉት የአቪዬሽን ትብብሮች እንዳሉ ሆነዉ ደሕና አየር ጣብያ መኖሩ፣ ለሎች የመከላኪያ ትብብሮች አንዱ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ዶክተር መሃር ተናግረዋል። ይሁን እንጂ ይላሉ ዶክተር መሃሪ አሜርካ በሰዉ አልባ አዉሮፕላን በከፈተችዉ ጥቃት አራት የአልሻባብ መሪዮች በመገደላቸዉ ለአልሻባብ መዳከም አስተወእፆ አድርጎዋል ይላሉ። ይሁን እንጂ ተቀሜታዉ ይሕን ያሕል የጎላ አይደለም ይላሉ፣ ምክንያቱም አብዛኛዉን ጊዜ ሰላማዊ ህዝብ ላይ ጉዳት ስላምያደርሱ ይላሉ ባለሙያዉ።
የዩናይትድ ስቴትስ አየር ሃይል የሰዉ አልባ የአየር ጠብያ መዝጋቱ በፀጥታ ዙርያ የሚያመጠዉን ጥቅም ወይም ጉዳት ከዛም አልፎ ለሶማሊያ መረጋጋት ወይም ለችግሮቹ መፍትሔ ሊሆን የሚችለዉን አስመልክቶ ዶክተር መሃር ሲያብራሩ፣ «እኔ በመሰረቱ የማምነዉ የሶማሊያን ችግር እና የአልሸባብ ችግር የሚፈታዉ መሬት ላይ በሶማሊያ በሚኪደዉ የፖለቲካ እና የልማት ሥራዎች ላይ ነዉ የሚመሰረተዉ። ፖለቲካ ስል ሶማሌያዊያን እራሳቸዉ የአልሻባብን የፖለቲካ ርዕዮተ-ዓለም፣ የእስልምና አክራሪነትን እና የምያደርሰዉን ጥቃቶች፣ ንፁሃን ዜጎች ጭምር ላይ የሚደረጉ ጥቃቶች በሚመለከተዉ አቋም ነዉ መፍትኄ የሚያመጣዉ፣ እንጅ ከዉጭ ኃይሎች፣ ይቅር እና የአሜርካ ድሮን የአሚሶም ኃይል እንኳን ራሱ አጋዢዥ ነዉ እንጅ ዋናዉ ሊሆን አይችልም። ዋና መፍትኄ ሊያመጣ የሚችል የሶማሊያ ኃይል ብቻ ነዉ።»

Afghanistan Drohne
ምስል picture-alliance/AP Photo/K. Wigglesworth

መርጋ ዮናስ
ነጋሽ መሃምድ