1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አረና “ማሰር እና ማስፈራራቱ ቀጥሏል” ብሏል

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 30 2010

የአረና ትግራይ ፓርቲ ሁለት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላቱ ከቀናት በፊት ታስረው በዋስ መፈታታቸውን ገለጸ። 

https://p.dw.com/p/2qWxH
Andom Gebreselassie  Sprecher von ARENA
ምስል DW/Y. Gebreegziabher

አረና “ማሰር እና ማስፈራራቱ ቀጥሏል” ብሏል

ኢሕአዴግ “የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን እና አባላትን እፈታለሁ” ሲል ቃል በገባበት ሳምንት ሁለት የአረና ትግራይ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ታስረው እንደነበር ፓርቲው ገለጸ። ከቀናት በፊት ታስረው በዋስ የተፈቱት የፓርቲው የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በቆላ ተምቤን የጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ዜናዊ አስመላሽ እና በውቅሮ ከተማ የአረና ተወካይ አቶ ኃይለኪሮስ ታፈረ መሆናቸውን ፓርቲው አስታውቋል።

በትግራይ ክልል በተለያየ ጊዜ በአባሎቹ ላይ ተፈጸሙ ባላቸው ግድያ እስራት እና ማስፈራራት በድርጅቱ እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ጫና መፍጠሩን ፓርቲው ሲገልጽ ቆይቷል። ሰበብ አስባብ እየለጠፉ የማሰር እና ማስፈራራቱ እንደቀጠለ እና በፖለቲካዊ ስራቸው ላይ እንቅፋት እንደሆነባቸው የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አንዶም ገብረስላሴ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። የዮሐንስ ገብረእግዚአብሔርን ዝርዝር ዘገባ ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ። 
 

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር
ተስፋለም ወልደየስ
አርያም ተክሌ