1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አራት የሥነ-ህንፃ ባለሙያዎችና ድርጅታቸው

ዓርብ፣ መጋቢት 30 2008

የዛሬው የወጣቶች ዓለም እንግዶቻችን አራት የስነ ህንፃ ባለሙያዎች ናቸው። ከከፍተኛ ተቋም ጀምሮ ይተዋወቃሉ። ተምረው ሲጨርሱም በጋራ አንድ ድርጅት መስርተዋል።

https://p.dw.com/p/1IS9f
Duka interior and elements design
ምስል Duka

አራት የስነ-ህንፃ ባለሞያዎችና ድርጅታቸው


በአዲስ አበባ ዮንቨርስቲ አብረው የተማሩ አራት ወጣት የየሥነ-ህንፃ ባለሙያዎች ናቸው። ከአንድ ዓመት በፊት አዲስ አበባ ውስጥ ዱካ የሚል ድርጅት በጋራ መስርተው ይንቀሳቀሳሉ። የእነዚህ ወጣቶች ሄኖክ ተሾመ፣ ኤፍሬም ሚሊዮን፣ ዳግማዊ ጥላሁን እና ምንተስኖት ተክሌ ይባላሉ።
የድርጅታቸው ትኩረት ከህንፃው ወይም ከውጪው ውበት ይልቅ የውስጡ ውበት ላይ ነው። ይህም የቁሳቁሶቹን አቀማመጥ እና አይነትን መቅረፅ ( ዲዛይን) ማድረግ የመሳሰሉትን ይመለከታል።
አብዛኛውን ጊዜ ጠባብ ለሆኑ ክፍሎች የሚስማሙ ቁሳቁሶች በሀገሪቱ ገበያ ላይ ማግኘት ከባድ ሆኖ አግኝተንዋል ይላሉ የሥነ-ህንፃ ባለሙያዎቹ፤ ታድያ ኢትዮጵያ ውስጥ ስራቸውን እስካሁን ምን ያህል እውን ማድረግ ችለዋል? የወጣቶቹ የወደፊት ዓላማስ ምንድን ነው? የሥነ-ህንፃ ባለሙያዎቹ ስለ ድርጅታቸው ምንነት እና አላማ ገልጸውልናል። ከድምጽ ጸገባው ያገኙታል።
ልደት አበበ

አዜብ ታደሰ