1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አርብቶ አደሮችና የተፈጥሮ አካባቢ

ማክሰኞ፣ የካቲት 9 2002

አርብቶ አደሮች ከብቶቻቸዉን ከቦታ ወደቦታ በማዘዋወር ኑሯቸዉን የሚገፉ የኅብረተሰብ ክፍሎች ናቸዉ። ከተፈጥሮ ጋ ያላቸዉ ቁርኝትም በግልፅ ያታያል።

https://p.dw.com/p/M38u
አርብቶ አደሮች በቀብሪ ደሃርምስል dpa - Fotoreport

የኑሯቸዉ መሠረት ለሆኑት ከብቶቻቸዉ ግጦሽና ዉሃ ፍለጋ ከአንድ ቦታ ወደሌላዉ ወቅቱን ተከትለዉ ሲዟዟሩ እግረ መንገዳቸዉን ታዲያ የአካባቢ ተፈጥሮን ያግዛሉ ይላሉ የአካባቢ ተፈጥሮ ተቆርቋሪዎች። በአንፃሩ ከከብቶች ፍግና እበት የሚወጣዉ ጋዝ አካባቢን ይበክላል፤ እንቅስቃሴያቸዉም እንዲሁ ችግር አለዉ የሚሉ ወገኖች ከቦታ ቦታ ከሚዟዟሩ ይልቅ በአንድ አካባቢ ረግተዉ ከከብቶቻቸዉ የሚያገኙትን ጥቅም በተሻለ ስልት ቢጠቀሙና ሌላዉንም ማኅበረሰብ ቢጠቅሙ እንደሚበጅ ይናገራሉ።

ሸዋዬ ለገሠ፤ ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር

አርያም ተክሌ