1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አሳዛኙ የኤርትራውያን ስደተኞች ዕጣ ያስከተለው ወቀሳ

ሰኞ፣ ነሐሴ 18 2001

በሜዴትራንያን ባህር በኩል በጀልባ ወደ አውሮፓ ለመሻገር የሞከሩ 73 ኤርትራውያን ስደተኞች የሚደርስላቸው አጥተው በውሀ ተበልተው መቅረታቸው አውሮፓውያንን ለክፉ ትችት ዳርጓል ።ከተችዎቹ አንዷ የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ናት ።

https://p.dw.com/p/JHVL
ስድተኞች በባህር ላይምስል AP

በጀልባ ይጓዙ የነበሩት ስደተኞች የሚታደጋቸው አጥተው በረሀብና በውሀ ጥም መሞታቸው ያስቆጫት ቤተክርስቲያኗ ሠለጠነ የሚባለው ህብረተሰብ ከዕውቀት ዕጦት ብቻ ሳይሆን በራስ ወዳድነት የውጭ ዜጎችን ያለመቀበል አዝማሚያ በማሳየት ወቅሳለች ። የትች ናዳ የወረደባት ኢጣልያ እንዲሁም ማልታ በስደተኞቹ ጉዳይ እየተነታረኩ ነው ። የአውሮፓ ህብረት በበኩሉ በሀያ ሰባቱ አባል ሀገራት የሚሰራ አንድ ወጥ የስደተኞች ህግ በማርቀቅ ላይ መሆኑን አስታውቋል ።

ጌታቸው ተድላ ሂሩት መለሰ