አስደንጋጩ የላይቤሪያ ተማሪዎች ውጤት
ሐሙስ፣ ነሐሴ 23 2005ማስታወቂያ
ለላይቤሪያ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች በሙሉ መውደቃቸው ላይቤሪያውያንን ብቻ ሳይሆን በዓለም ዙሪያ እያነጋገረ ነው ። በአዲሱ የትምሕርት ዘመን ላይቤሪያ ዩኒቨርስቲ ያመለከቱ 25 ሺህ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተናውን መውደቃቸው የላይቤሪያ የትምህርት ደረጃ ዝቅተኛ መሆኑን እንደሚያመለክት የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ ሳይቀሩ አምነዋል ። ፕሬዝዳንቷ የተማሪዎቹ የፈተና ውጤት ለላይቤሪያ አሳፋሪ መሆኑንም ሳይጠቅሱ አላለፉም ዩኒቨርስቲው ወደ ተቋሙ መግባት የሚያስችለውን ነጥብ ዝቅ በማድረግ 1600 ፈተና ማለፍ ያልቻሉ ተማሪዎችን ለመቀበል ተገዷል ። ዝርዝሩን ይልማ ኃይለ ሚካኤል አዘጋጅቶታል ።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ