1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አቋራጭ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 24 2005

«Back Road To Ethiopia» ይሰኛል በሚቀጥሉት ሳምንታት በጀርመኑ የሙዚቃ መድረክ የሚለቀቀዉ አፍሪቃዊ በተለይም የኢትዮጵያ ባህላዊ ሙዚቃዎችን ያካተተዉ የሙዚቃ አልበም።

https://p.dw.com/p/18QxN
CD Cover Karibuni @ddis Back Road to Ethiopia Neue CD Bild: Westpark (Indigo)
ምስል Westpark Indigo

ይህ የሙዚቃ አልበም  እንግሊዘኛና ጀርመንኛ አማርኛ እንዲሁም ሌሎች የአፍሪቃ ቋንቋዎች ያጣመረ፤ በዓለም የሙዚቃ አፍቃሪዎች ጆሮ እንዲንቆረቆር ሆኖ የተሰራ  የሙዚቃ አልብ መሆኑን ሙዚቃዉን ያዳመጡ ይመሰክራሉ። የጀርመኑ ካሪቡኒ አዲስ የሙዚቃ ቡድን ከሁለት ሳምንት ግድም በኋላ በጀርመን የሙዚቃ መድረክ ከሚያቀርበዉ ሙዚቃዉ ጋር የለቱ የባህል ዝግጅት እንግዳችን ነዉ።ወደ ኢትዮጵያ አቋራጭ መንገድ ይሰኛል፤ የዛሪ ሁለት ሳምንት ግድም ይፋ የሚሆነዉ የሙዚቃ አልብም። በስዋሂሊ ቋንቋ "Karibuni"   እንኳን ደህና መጣችሁ  የሚል መጠርያን የያዘዉ የሙዚቃ ቡድን መስራቾቹ ጀርመናዊዉ ፒት ቡደ እና በእናትዋ ኢትዮጽያዊት የሆነችዉ ባለቤቱ ጆሴፊነ ክሮንፍሊ  በጀርመን ለመጀመርያ ግዜ የዓለም ሙዚቃ ለህጻናት በሚል የሙዚቃ አልበም በማቅረባቸዉ ይታወቃሉ። እስከዛሪም ከአስር በላይ ሙዚቃ አልብምን ለሙዚቃ አፍቃሪዎች በጀርመን መድረክ አቅርበዋል። በቅርቡ ለገበያ የሚያቀርቡት አልብማቸዉ አብዛኛዉ ዘፍኖች የኢትዮጵያ ባህላዊ ሙዚቃን በጀርመንኛ  በእንግሊዘኛ ተርጉሞ እንዲህ በመሰናዶዉ ላይ እንደሚደመጠዉ የቀረበ ነዉ።የዚህ ቡድን መስራች የሆኑት ጆሴፊኒ ክሮንፍሊ አዲሱ የሙዚቃ አልብም አድማጭን በአቋራጭ ወደ ኢትዮጵያ የሚወስድ ነዉ ባይ ናቸዉ። 

Karibuni" bedeutet "Willkommen" in der afrikanischen Sprache "Kiswahili". Genauso nannten Josephine Kronfli und Pit Budde ihre Gruppe, mit der in Deutschland erstmals das Konzept einer "Weltmusik für Kinder" realisiert wurde. Die aktuelle CD der Gruppe, "Tadias! Kommt mit nach Afrika" beinhaltet eine bunte Mischung von Liedern vielen afrikanischen Ländern. Die meisten Lieder werden in der Originalsprache und einer deutschen Übertragung gesungen, sind fantasievoll musikalisch arrangiert mit traditionellen und modernen Instrumenten. Ergänzt werden die Lieder aus Äthiopien, Kenya, Tansania, Sambia, Südafrika, Nigeria, Marokko, Benin, Mali usw. durch erklärende Moderationen sowie Geschichten und Weisheiten der afrikanischen Völker. www.karibuni-kinderweltmusik.de Eingestellt Juli 2010
ምስል Karibuni

ካሪቡኒ የሜዚቃ ቡድን የዓለም ሃገራት የተለያዩ ባህሎችን በማጣመር ሙዚቃን በማዉጣቱ በጀርመን ሀገር የተለያዩ ሽልማቶችን አግኝቶአል፤ በተለይም ለህጻናት የሚሆን ሙዚቃዎችን በማሳተሙም ቡድኑ እጅግ ይታወቃል።
በእናትዋ ኢትዮጽያዊት እና ከሶርያዊ አባትዋ የምትወለደዉ ከያኒ ጆሴፊን ለኢትዮጵያ ያላት ፍቅርን ከፍተኛ በመሆኑ የዓመቱ ቢያንስ በየሁለት ዓመቱ  ኢትዮጵያ ወዳሉት ዘመዶችዋ ቤተሰቦችዋን ይዛ እንደምትሄድ ትናገራለች። በጀርመን ስትኖር ሰላሳ አመት የሆናት ጆሴፊን ኢትዮጵያ እስከ አስራ ስምንት ዓመት እድሜዋ እንደኖረች እና የጀርመን ትምህርት  ቤት ተማሪ እንደነበረች አጫዉታናለች። ሆያ ሆዬ እቴሜቴ የመሳሰሉ የልጅነት ትዝታዎችዋ አሁንም፤ እዚህ  በአዉሮጳ  ኑሮዋ አልጠፋም። ካሪቡኔ አዲስ በሚል መጠርያ የባህል ድልድይን ዘርግታ ባህሏን እያስተዋወቀች ትገኛለች።  ሙዚቀኛ ጆሴፊነ ክሮንፍሊ በህጻንነትዋ እናትዋ  የኢትዮጽያን ባህል ጠንቅቀዉ አስተምረዋታል። በሚቀጥሉት ሳምንታት በሚወጣዉ Back Road To Ethiopia በተሰኘዉ የሙዚቃ አልብ ላይ የምታዜመዉ ጀርመናዊት ዶሮትያ ኢትዮጵያ ዉስጥ በንጉሰ ነገስቱ ዘመን ቤተሰቦችዋ የጀርመን ኤንባሲ ሰራተኛ ስለነበሩ ኢትዮጵያ እንደኖረች ትናገራለች። ሰላምታ እና አማረኛ መናገር እንደማትችል ብቻ በአማረኛ መናገር እንደምትችል የምትናገረዉ

« ዶሮትያ የኢትዮጵያ ትዝታዋን እንዲህ ስትል ትተርካለች፤   በአስር አስራ አንድ አመቴ የጀርመን ትም ህርት ቤት ተማሪ ሳለሁ አስተማሪዬ ስሜን ጠይቃኝ ዶሮትያ መሆኑን እና ስሜ ሲያጥር ሲያጥር  ዶሮ እባላለሁ ብዪ ስነግራት የክፍሉ ተማሪ ሳቀብኝ፤ ከዝያን ግዜ ወዲህ የክፍሉ ተማሪ ሁሉ ዶሮ ወጥ ሲል ይጠራኝ ጀመር። ከዝያንግዜ ወዲህ የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግብ ዶሮወጥ ሆንክ ስትል ፈገግ አድርጋናለች። ወደ  ኢትዮጵያ ከ ጎርጎረሳዉያኑ 1977 ዓ,መ ወዲህ ሄዳ እንደማታዉቅም ነግራናለች። ከካሪቡኒ የሙዚቃ ቡድን ጋር ሙዚቃን በመጫቴ እኮራለሁ የምትለዉ ዶሮትያ ወደ ኢትዮጵያ መሄድ እንደሚያስፈራት ግን ከመናገር ወደ ኋላ አላለችም።

Tadias! Kommt mit nach Afrika. Lieder, Spiele, Tänze und Musik aus Afrika. Weltmusik. Karibuni" bedeutet "Willkommen" in der afrikanischen Sprache "Kiswahili". Genauso nannten Josephine Kronfli und Pit Budde ihre Gruppe, mit der in Deutschland erstmals das Konzept einer "Weltmusik für Kinder" realisiert wurde. Die aktuelle CD der Gruppe, "Tadias! Kommt mit nach Afrika" beinhaltet eine bunte Mischung von Liedern vielen afrikanischen Ländern. Die meisten Lieder werden in der Originalsprache und einer deutschen Übertragung gesungen, sind fantasievoll musikalisch arrangiert mit traditionellen und modernen Instrumenten. Ergänzt werden die Lieder aus Äthiopien, Kenya, Tansania, Sambia, Südafrika, Nigeria, Marokko, Benin, Mali usw. durch erklärende Moderationen sowie Geschichten und Weisheiten der afrikanischen Völker. www.karibuni-kinderweltmusik.de Eingestellt Juli 2010

«በጎርጎረሳዉያኑ 1973ዓ,ም እስከ 1977 ዓ,ም ከቤተሰቦቼ ጋር  አዲስ አበባ  ኢትዮጵያ ዉስጥ ኖሪአለሁ። የአስራአራት ዓመት ልጅ ነበርኩ። ከዝያ 1977ዓ,ም ከቤተሰቦቼ ጋር ኢትዮጵያን ለቅቄ ከወጣሁ በኋላ አልተመለስኩም። ዳግም ተመልሼ መሄድም እፈራለሁ ወታደራዊዉ መንግስት መፈንቅለ መንግስት ባካሄደበት ግዜ እዝያ ስለነበርኩ እና አስከፊ የሆነዉን የአብዮት ገጽታ በማየቴ ነዉ። በኛ በዉጭ ዜጎች ላይ የደረሰ ነገር ባይኖርም በዜጋዉ ላይ የነበረዉን እንግልት አይቻለሁ።

ንጉሰ ነገስት አጼ ሃይለስላሴ በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት የዘመን መለወጫ በአልን በማስመልከት የዲፕሎማት ልጆችን ጋብዘዉ ሳለ ቤተ-መንግስት ግቢ ዉስጥ ግብዣዉ ላይ ነበርኩ ጨብጠዉኛልም፤ የኢትዮጵያ ትዝታዪ ያ ነዉ በተረፈ ከካሪቡና ጋር ሙዚቃ እንድጫወት ስለተፈቀደልኝና አብሪ በማዜሜ፣ ኩራት  ይሰማኛል»የካሪቡኒ አዲስ የሙዚቃ ቡድን መስራች ጀርመናዊዉ ፒት ቡደ የኢትዮጵያዉያን ባህል በተለይ ደግሞ ሙዚቃን ዘንቅቀዉ ያዉቃሉ፤ እዚህ በምዕራቡ ዓለም በተለይ ደግሞ በጀርመን በሙዚቃዉ ረገድ ኢትዮጵያዉያንን ባህል በማስተዋወቁ ረገድ እጅግ ይታወቃሉ።  ከዚህ ቀደም የአስናቀች ወርቁን ሙዚቃዎች እራስዋን አስናቀችን ወደ ጀርመን ሀገር በተደጋጋሚ በመጋበዝ ሙዚቃዎችዋን በአልብም አስቀርጸዋል፤ የበገና አባት ተብለዉ የሚታወቁትን መጋቢ ስብሃት ዓለሙ አጋንም እንዲሁ በጀርመን በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች የበገና ድርደራቸዉን እንዲያቀርቡ በማድረጋቸዉ ይታወቃሉ፤ ባክ ሮድ ስለተሰኘዉ አዲስ የሙዚቃ አልብም ፒት ቡደ፤ «ከተለያዩ ሀገሮች የተለያዩ ሙዚቃዎችን የተለያየ ባህል አሰባስበን ነዉ ይህን ሙዚቃ ያቀናበርነዉ ለምሳሌ ጀርመን አገር ነዋሪ የሆነዉ አንድ የአንጎላ ተወላጅ ለብዙ ግዜ ኮንጎ ዉስጥ የኖረ ባህሉን ጠንቅቆ የሚያዉቅ ሙዚቀኛ አብሮን አዚሞአል። በርካታ የኢትዮጵያ ባህላዊ ዘፈኞችንም ተጫዉተናል። በርግጥ ሙዚቃዉ ለምራባዉያኑ እንዲገባና ቀሉ እንዲደመጥና በጆሮ እንዲቆረቆር አድርገን ነዉ የሰራነዉi። የጀርመን ሙዚቃም አለበት። እና በአጠቃላይ የተለያዩ ባህሎችን አሰባስበን ይህን አልብም ስንሰራ በጣም ደስ ብሎን ነዉ። እናም ይህ አዲሱ ሙዚቃችን ሰዎች ይወዱልናል በተለይም ደግሞ በኢትዮጵያ ያሉ ይወዱልናል ብለን ተስፍ እናደርጋለን» የሙዚቃ ትምህርትዋን በከፍተኛ ትምህርት ደረጃ በመከታተል ላይ ያለችዉ የሁለቱ ሙዚቀኞች ልጅ ራሄል ቡደ፤ ሌላዋ የዚህ የሙዚቃ አልብም ተሳታፊ ናት፤ ከናት ከአባትዋም ጋር በመሆን በተለያዩ መድረኮች ሙዚቃን ትጫወታለች፤ ኢትዮጵያን በየግዜዉ ትጎብኝ ባህሉን ትወቅ እንጂ አማርኛ ብዙም ስለማትችል በጀርመንኛ እና በእንግሊዝኛ ብትናገር ትመርጣለች፤ በዚህ የሙዚቃ አልብም ትላለች ራሄል  «በዚህ የሙዚቃ አልብም ላይ በተለይ የእንግሊዘኛዉን ትርጉምን ነዉ ያዜምኩት። ሌላ ደግሞ አንድ በጀርመንኛ  ሙሉ ዜማን ተጫዉቻለሁ። በተረፈ በአማርኛ ሌሎች ባልደረቦቼ የሚያዜሙትን እኔ በእንግሊዘኛ ነዉ ያዜምኩት»በጀርመን ታዋቂ ለሆኑት ከያኒ ኡዶ ሊደድንበርግ ሙዚቃ መሳርያን የሚጫወቱት ሽቴፊ ሽቴፈን የአፍሪቃን የሙዚቃ ስልት ሲጫወት የመጀመርያዉ ነዉ። ካሪቡኒ ባንድ ጋር ሰሞኑን በሚዛወጣዉ አዲስ የሙዚቃ አልበም ላይ በመጫወቱም ደስተኛ መሆኛቸዉን ገልጸዋል።

CD Cover Karibuni @ddis Back Road to Ethiopia Neue CD Bild: Westpark (Indigo)
ምስል Westpark Indigo

ካሪቡኒ አዲስ የኢትዮጵያን ባህል በዓለም የሙዚቃ መድረክ እያቀረበ ማስተዋወቁ ይበል የሚሰኝ ነዉ። ቡድኑ  ሙዚቃዉን  ማግኘት ለሚሻ ሁሉ  በድረ-ገጽ አድራሻ ካሪቡኒ ዶት ኮም ብሎ የሙዚቃ አልብሙን በአድራሻ ሊደርሰዉ እንደሚችል ከወዲሁ ይገልጻል።

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሃመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ