1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኤኮኖሚ

ውይይት፦አቤቱታ ያስከተለዉ የግምት ገቢ ግብር ትመና

እሑድ፣ ሐምሌ 9 2009

የኢትዮጵያ የገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን በአዲስ አበባ የሚገኙ የቁርጥ ግብር ከፋዮች የሚላቸዉ እና በደረጃ« ሐ» ሥር የመደባቸዉ ነጋዴዎች የሚከፍሉትን አመታዊ ግብር ተመን ከማዉጣቱ በፊት አማካኝ የቀን ገቢ ግምት ለዉጥ ማድረጉን የሚገልጽ ደብዳቤ መስጠት ከጀመረ ሳምንታት አልፈዋል።

https://p.dw.com/p/2gaCx
Äthiopien Addis Abeba Kaffee Wirtschaft Roza Melese
ምስል DW/James Jeffrey

ውይይት፥ አቤቱታ ያስከተለዉ የግምት ገቢ ግብር ትመና

 ብዙዎቹ የቀን ገቢ የግምት ስሌቱ እና ዓመታዊ ሽያጫቸዉ ይሆናል በሚል ተጣለብን ያሉት የግብር መጠን የተጋነነ እና ከአቅማቸዉ በላይ እንደሆነ ይናገራሉ። አቤቱታቸዉንም ከመገናኛ ብዙሃን አልፈዉ ለሚመለከተዉ የክፍለ ከተማ እና የወረዳ ጽሕፈት ቤት ለማቅረብ እንደሞከሩ ይገልጻሉ። ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ ከሚያዝያ ወር አጋማሽ ጀምሮ እስከ ግንቦት መጨረሻ ድረስ የነጋዴዎቹን የቀን ገቢ የገመተበት ጥናት ማድረጉን ይናገራል። ባካሄደዉ ቅኝት መሠረት የደረጃ ለዉጦች ያንንም ተከትሎ የግብር ለዉጥ መኖሩንም ያስረዳል። በዚህም መሀል ግብር ከፋዮች ከገቢያችን በላይ ግብር ተጠየቅን በማለት እያማረሩነዉ። ዶቼ ቬለ በጉዳዩ ላይ የቅሬታዉን መንስኤ እና መፍትሄን ለመቃኘት ያካሄደዉን ዉይይት ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ።

ሸዋዬ ለገሠ