1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አብን የጠራው ሰልፍ መከለከሉ የገጠመው ተቃውሞ 

ረቡዕ፣ ጥቅምት 18 2013

የፓርቲው ሊ/መንበር አቶ በለጠ ሞላ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ከታሰሩት መካከል በተለያዩ አካባቢዎች ዛሬ ሰልፍ የወጡ አባላቱ ይገኙበታል። ሰልፉ መታገዱን የተለያዩ ፓርቲዎች «የሕገ መንግሥታዊ መብት ክልከላ» ሲሉ ነቅፈዋል።

https://p.dw.com/p/3kYmo
Äthiopien Addis Abeba - Nama Hauptquartier
ምስል DW/ S. Mantegaftot Sileshi

አብን የጠራው ሰልፍ መከለከሉ የገጠመው ተቃውሞ 

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ መከልከሉ አግባብ ካለመሆኑ በላይ ከትናንት ጀምሮ አባላቶቹ እየታሰሩበት መሆኑን ለዶይቼ ቬለ ተናገረ። የፓርቲው ሊ/መንበር አቶ በለጠ ሞላ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ከታሰሩት መካከል በተለያዩ አካባቢዎች ዛሬ ሰልፍ የወጡ አባላቱ ይገኙበታል። ሰልፉ መታገዱን የተለያዩ ፓርቲዎች «የሕገ መንግሥታዊ መብት ክልከላ» ሲሉ ነቅፈዋል። እገዳውን ከተቃወሙት መካከል የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)፣ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ)ና ፣የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ ይገኙበታል። የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ተጠቃሚዎችም ድርጊቱን ኮንነዋል። ሰሎሞን ሙጬ ከአዲስ አበባ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል።
ሰሎሞን ሙጬ 
ኂሩት መለሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ