1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አትሌት አበባ አረጋዊ ከውድድር መታገዷ

ቅዳሜ፣ የካቲት 26 2008

በዓለም አቀፍ ደረጃ ስዊድንን ወክላ የምትወዳደረው አትሌት አበባ አረጋዊ የኃይል ሰጪ መድሃኒት ወይንም ዶፒንግ ተጠቃሚ እንደሆነች የዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር (IAAF) ከትናንት በስትያ ይፋ አድርጓል።

https://p.dw.com/p/1I6to
Adidas Leichtathletik
ምስል picture alliance/dpa/B. Thissen

[No title]

ይኽን ተከትሎ የስዊድን ስፖርት ፌዴሬሽን አትሌቷ በማንኛውም አይነት ውድድር እንዳትሳተፍ ማገዱን በመግለጫው አስታውቋል። በተመሳሳይ መንገድ አትሌት አበባ አረጋዊ የታቀፈችበት ሀማርቢ በመባል የሚታወቀው የስፖርት ቡድን ከአትሌቷ ጋር ያለውን ትስስር እንዳቋረጠ በድረ-ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫ ይፋ አድርጓል። አትሌት አበባ አረጋዊ በ1,500 ሜትር የቤት ውስጥ የሩጫ ውድድር የዓለም ሻምፒዮን ናት። የስዊድኑ ወኪላችን ቴድሮስ ምኅረቱ ዝርዝር ዘገባ አለው።

ቴድሮስ ምኅረቱ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አርያም ተክሌ