1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አቶ በቀለ ነጋ ቁም እስር ላይ ናቸው

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 21 2008

በእስር ላይ የሚገኙት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ በምኅፃሩ(ኦፌኮ)ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ መታመማቸው እየተነገረ ነዉ። እንዲያም ሆኖ አቶ በቀለ ገርባ ከቤተሰቦቻቸውም ሆነ ከሌሎች ሰዎች ጋር እንዳይገናኙ መከልከላቸውም ተሰምቷል።

https://p.dw.com/p/1HWdk
Dr. Merera Gudina Addis Abeba Äthiopien Oromo Pressekonferenz PK
ምስል DW/Y.Egziabhare

[No title]

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ በምኅፃሩ (ኦፌኮ) ዋና ጸሓፊ አቶ በቀለ ነጋ ደግሞ ዛሬ የእጅ ስልካቸው ተቀምቶ በቁም እስር እንደሚገኙም ተገልጧል። አቶ በቀለ ገርባ በጠና ታመዋል፤ ህክምናም ተከልክለዋል መባሉን በተመለከተ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ዛሬ በስልክ ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል። በእስር ላይ የሚገኙት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ ከቤተሰባቸውም ሆነ ከማንኛውም ሰው ጋር እንዳይገናኙ መከልከላቸውን ጠቅሰዋል። የኦፌኮ ዋና ጸሓፊ አቶ በቀለ ነጋ ደግሞ ዛሬ ጠዋት ስላካቸው ተቀምቶ «በቁም እስረኝነት» እንደሚገኙ ተገልጧል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሸዋዬ ለገሰ