1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አቶ ተማም ፍቃዳቸዉን ተቀሙ

ዓርብ፣ ሐምሌ 3 2007

የኢትዮጵያ ፍትሕ ሚንስቴር የታዋቂዉን ኢትዮጵያዊ የሕግ ባለሙያና ጠበቃ የአቶ ተማም አባቡልጎን የጥብቅና ፍቃድ ቀማ።

https://p.dw.com/p/1Fwjh
Symbolbild Justitia Justizia
ምስል picture-alliance/dpa

አቶ ተማም እንደሚሉት ፍቃዳቸዉ የታገደዉ ለአንድ ዓመት ከሰባት ወር ነዉ።ለመታገዱ የተሰጣቸዉ ምክንያት ደግሞ «የዲሲፒልን ጉድለት» የሚል ነዉ። አቶ ተማም የኢትዮጵያ መንግሥት በተለያየ ክስ ላሠራቸዉ ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ መሪዎች፤ ለተለያዩ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ባለሥልጣናትንና አባላት ጥብቅና ቆመዉ ከአቃብያነ ሕግ ጋር የሚሟገቱ ባለሙያ ናቸዉ። አቃቤ ሕግ ተጠሪነቱ ለፍትሕ ሚንስቴ ነዉ። የፍትሕ ሚንስቴር ባለሥልጣናት ፍቃዱን ያገዱበትን ምክንያት እንዲያስረዱን በተደጋጋሚ በሥልክ ለማግኘት ያደረግነዉ ሙከራ አልተሳካም። አቶ ተማምን ነጋሽ መሐመድ አነጋግሯቸዋል።

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ