1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አቶ አንዳርጋቸው ፣ ዩናይትድ ስቴትስና ና አውሮፓ

ረቡዕ፣ ነሐሴ 6 2007

ደብዳቤው የእንግሊዝ የአሜሪካና የአውሮፓ ፓርላማ እንደራሴዎች የፈረሙበትና አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲፈቱ የሚጠይቅ መሆኑን የአውሮፓ ህብረት ቃል አቀባይ ለዶቼቬለ አስታውቀዋል ።

https://p.dw.com/p/1GEQF
Brüssel Europäische Kommission Außenansicht
ምስል picture-alliance/dpa/D. Kalker

[No title]

የአሜሪካና የአውሮፓ ባለስልጣናት የኢትዮጵያ መንግሥት ያሠራቸውን የተቃዋሚው የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ መሪ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን እንዲፈታ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ መላካቸው ተዘግቧል ።ደብዳቤው የእንግሊዝ የአሜሪካና የአውሮፓ ፓርላማ እንደራሴዎች የፈረሙበትና አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲፈቱ የሚጠይቅ መሆኑን የአውሮፓ ህብረት ቃል አቀባይ ለዶቼቬለ አስታውቀዋል ። አቶ አንዳርጋቸው ከየመን ተወስደው ኢትዮጵያ ውስጥ ከታሰሩ አንድ ዓመት አልፏቸዋል ። ገበያው ንጉሴ ከብራስልስ ዘገባ አለው ።
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ