1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አነጋጋሪዉ የሶማሊያ ሰላም

ሰኞ፣ የካቲት 23 2001

አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝደንት ሼኽ ሸሪፍ ሼኽ አህመድ አገራቸዉን ወደሰላም መንገድ ለመምራት የሸሪዓ ህግን መተዳደሪያ ለማድረግ መዘጋጀታቸዉን ይፋ አድርገዋል። የተኩስ አቁም ለማድረግም ዝግጁነታቸዉን ገልፀዋል።

https://p.dw.com/p/H49w
ሼኽ ሸሪፍ ሼኽ አህመድ
ሼኽ ሸሪፍ ሼኽ አህመድምስል AP Photo/Mohamed Sheikh Nor

በአንፃሩ በአገሪቱ የሚንቀሳቀሱ እስላማዉያን ተዋጊዎች ርምጃዉን በማዋደቅ በመንግስትና ደጋፊዎቹ ላይ የጀመሩትን ዉጊያ አጠናክረዉ እንደሚቀጥሉ አስታዉቀዋል። አንዳንድ ወገኖች አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር በሶማሊያ ሰላምን ለማምጣት ይሳካላቸዋል ቢሉም የቀድሞዉን ፅንፈኛ እስላማዊ ቡድን የእስላማዊ ፍርድ ቤቶች ኅብረት ይመሩ ለነበሩት ለሼኽ ሸሪፍ ከእስላዋዉያኑ የተሰጠዉን ምላሽ በማገናዘብ የሚሆን አይመስልም ማለት ጀምረዋል።