1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

Merga Yonas Bula
ሐሙስ፣ ኅዳር 14 2010

በጤና፣ በሕግ እንዲሁም በቴክኒክ ሙያ መስክ የከፍተኛ ትምህርታቸዉን ያጠናቀቁ ተማሪዎች የብቃት ምዘና፣ COC ፈተና መዉሰድ ከጀመሩ 10 ዓመት ሆኖዋል። በት/ሚንስቴር የፌ/የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የሚዘጋጀዉ ፈተና ዓላማ ተማሪዎቹ ስራ ከመጀመራቸው በቂ ዕውቀት እና ተግባራዊ ክህሎት እንዳላቸዉ ለመመዘን ነው።

https://p.dw.com/p/2o5HB
12.06.2013 DW Online Karten Basis Äthiopien Englisch

CoC Saga - MP3-Stereo

በኢትዮጵያ የብቃት ምዘና ፈተና ወይም በተለምዶ COC ተብሎ የሚጠራዉን ስራ ላይ መዋል ከተጀመረ 10 ዓመት አስቆጥረዋል። በጤና፣ በሕግ እንዲሁም በቴክንክና ሙያ መስክ ያሉ ተማሪዎች አሁንም እየወሰዱ ይገኛሉ። ተማሪዎች ወደ ስራ ዓለም ከመግባታቸው በፊት በተማሩት የትምህርት መስክ የተማርዎቹን የaptitude/ስጦታ/፣ የክህሎትና የእዉቀት ደረጃ ለመመዘን ሲባል ፈተናዉ እንደሚሰጥ በትምህርት ሚንስቴር የፌዴራል የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የሙያ ደረጃና የብቃት ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ንግስት መላኩ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል።

ፈተናዉን የሚፈተኑ ወይም የተፈተኑት ተማሪዎች ፈተናዉ ይዘት እነሱ ከተማሩት ጋር የተራራቀ እንደሆነ፣ ፈተናዉን ለመፈተን ወጭዉ ከአቅማቸዉ በላይ እንደሆነ እንድሁም ረጅም ጊዜ እንደምወስድ ቅሬታቸዉን ያሰማሉ።

ስማቸዉን ሳይጠቅሱ ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ከሆሳና ከተማ ለፈተናዉ የሚወጣዉን ወጭ በተመለከተ በዋትስኣፕ ላይ የድምጽ አስተያየታቸዉን ልኮውልናል።

ሌላ አሁን በሳዉድ አረቢያ የሚኖሩ አንድ ግለሰብ ለስደት ያበቃኝ COCን መዉደቀ ነዉ ይላሉ።

ምዘናዉ ረዥም ግዜ ይወስዳል መባሉን እንደማይቀበሉት ወ/ሮ ትግስት ይናገራሉ። በጀርመን አገር ምዘናዉ በዓመት ሁለቴ ብቻ እንደሚሰጥ የተናገሩት ወ/ሮ ትግስት ኤጀንስዉ ምዘና የሚያካሄደዉ በየሶስት ሳምንቱ ነዉ ይላሉ።

መርጋ ዮናስ

አርያም ተክሌ