1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አነጋጋሪው የፕሬዚዳንት ዑመር አልበሽር ጉብኝት

ቅዳሜ፣ መጋቢት 19 2001

የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ዑመር አልበሽር በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ተይዘው እንዲቀርቡ የእስር ትዕዛዝ ቢቆረጥባቸውም፤ ለውሳኔው ቁብም ሳይሰጡ አንዳንድ ሀገራትን በመጎብኘት ላይ ይገኛሉ።የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት በብዙዎች ዘንድ አነጋጋሪ ሆኗል።

https://p.dw.com/p/HLpo
የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ዑመር አልበሽር
የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ዑመር አልበሽርምስል AP

አልበሽር በሰሩት ወንጀል ተይዘው ለፍርድ ይቅረቡ ሲል ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት የእስር ትዕዛዝ ማስተላለፉ ይታወቃል። ሁኔታው ታዲያ ዓለምን በሶስት የከፈለ ይመስላል። ገሚሱ ውሳኔው ተገቢ ነው፤ ፕሬዚዳንቱ ውለው ሳያድሩ ለፍርድ ይቅረቡ ሲል፤ ሌላው ደግሞ፤ የለም! የአንዲት ሉዓላዊት ሀገር መሪ በስልጣን እያሉ መክሰስ ፍትሀዊ አይደለም ሲል ተደምጧል። ቀሪው አካል ደግሞ ዩናይትድ ስቴትስን ጨምሮ ማለት ነው አስተያየት ከመስጠት የተቆጠበ ይመስላል።

ታደሰ እንግዳው

ማንተጋፍቶት ስለሺ