1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«አናሎግ» ና «ዲጂታል»

ሐሙስ፣ የካቲት 12 2007

ባለፈው ሳምንት ማለቂያ ላይ ፤ የኬንያ መንግሥት የመገናኛ ብዙኀን የሥርጭት አገልግሎትን፣ ከቆየው «አናሎግ» ወደ ዘመናዊው ሥነ ቴክኒክ አያያዝ «ዲጂታል »ማሸጋገሩ የታወቁትን ዐራት የግል ቴሌቭዥን ተቋማትንና ደንበኞቻቸውን ቅር ማሰኘት ብቻ ሳይሆን ማናደዱ ነው የተነገረው።

https://p.dw.com/p/1Edut
DW Sendung Shift - Leben in der digitalen Welt
ምስል DW/D. Späth

NTV KTN «ሲቲዘን TV» እና QTV በሚሉ ምሕጻረ ቃላት የታወቁት ዐራት የቴሌቭዥን ተቋማት የተናደዱት፣ «ትንሽ የመዘጋጂያ ጊዜ ሳይሰጠን »በማለት እንጂ ዘመናዊ ወደሚሰኘው የዲጂታል አቅድ ሽግግር መደረጉን በመሠረተ ሐሳብ ተቃውመው አይደለም። የዛሬው ሳይንስና ሕብረተሰብ ፤ ቅንብር ስለ አናሎግና ዲጂታል ምንነት የአንድን ባለሙያ ትንተና ያቀርባል።

Von Analog zu Digital
ምስል picture-alliance/dpa

ወደ ቴክኒኩ ዓይነት ስንመለስ ፣ ሽግግር የተደረገው «አናሎግ » ከሚሰኘው ወደ «ዲጂታል» ነውና ፤ አናሎግ ምንድን ነው ዲጂታልስ? በዩናይትድ ስቴትስ ፤ ሜሪላንድ ፌደራል ክፍለ ሀገር ሐዎርድ ማሕበረሰባዊ ኮሌጅ ፤ የኮምፒዩተር መረብ (ኔትወርክ) ና የኢንተርኔት ደኅንነት ጥበቃ ጉዳይ ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶ/ር መንግሥቱ አዱኛ እንዲህ ያብራራሉ።

አምና የህዝቧ ቁጥር 45,941,977 መድረሱ በተነገረላት ኬንያ፤ ከ 90 በላይ በመካከለኛ ሞገድ የሚሠሩ ራዲዮ ጣቢያዎች ፣ 15 ያህል የቴሌቭዥን ጣቢያዎች ይገኛሉ። የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚው ህዝቧ መጠን 32,2 ሚሊዮን ገደማ ሲደርስ በኢንተርኔት የሚገለገለውም ከ 19 ,6 ሚሊዮን በላይ መሆኑ ነው የሚነገረው ። በመገናና ብዙኀን ሰፋ ያለ አገልግሎት የምታገኘው ሀገር ናት እንግዲህ በ«አናሎግ » ከማሠራጫ ደንብ ወደ ዲጂታል ሥርዓት የተሸጋገረችው። ዲጂታል ምንድን ነው ? ዶ/ር መንግሥቱ አዱኛ--

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ