1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አከራካሬው የወንዶች ልጆች ግርዛት በጀርመን

ማክሰኞ፣ ሰኔ 26 2004

የኮሎኝ የጀርመን ፍርድ ቤት ባለፈው ሳምንት ወንዶች ልጆችን መግረዝ በአካል ላይ ጉዳት ማድረስ ነው ሲል ያሳለፈው ውሳኔ እያወዛገበ ነው ። ይህ ውሳኔ ያስነሳው ክርክር የዛሬው አውሮፓና ጀርመን ዝግጅታችን ትኩረት ነው በዓለም የጤና ድርጅት ግምት ከዓለማችን ወንዶች 1/3 ተኛው ተገርዘዋል ።

https://p.dw.com/p/15Qis
In this Sunday, May 15, 2011 photo, Benjamin Abecassis rests on a pillow sounded by family members, immediately following his Bris, a Jewish circumcision ceremony in San Francisco. San Francisco voters in November will be asked to weigh in on what was until now a private family matter: male circumcision. City elections officials confirmed Wednesday, May 18, 2011 that an initiative that would ban the circumcision of males younger than 18 in San Francisco has received enough signatures to appear on the ballot. The practice would become a misdemeanor. (Foto:Noah Berger/AP/dapd)
ምስል AP

የኮሎኝ የጀርመን ፍርድ ቤት ባለፈው ሳምንት ወንዶች ልጆችን መግረዝ በአካል ላይ ጉዳት ማድረስ ነው ሲል ያሳለፈው ውሳኔ እያወዛገበ ነው ። ይህ ውሳኔ ያስነሳው ክርክር የዛሬው አውሮፓና ጀርመን ዝግጅታችን ትኩረት ነው በዓለም የጤና ድርጅት ግምት ከዓለማችን ወንዶች 1/3 ተኛው ተገርዘዋል ። ከነዚህም አብዛኛዎቹ ሙስሊሞች አይሁዶች ና ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ናቸው ። በአንዳንድ ባህሎችም ከጤናና ከንፅህና አጠባበቅ ጋር በተያያዙ ምክንያቶች ወንዶች ይገረዛሉ ።የወንዶች ልጆች ግርዛት በአንዳንድ ሃይማኖቶች የማይቀር ልምድ ሲሆን ግርዛት በባህል አስገዳጅነት የሚከናወንባቸው ሁኔታዎች አሉ ። ወንዶች የሚገረዙበት እድሜ እንደ ሃይማኖቱ ባህሉና ይለያያል ። አይሁዶች ወንድ ልጅ በተወለደ በስምንተኛው ቀን ይገርዙሉ ። በሙስሊሞችም ሆነ በአንዳንድ የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ዘንድ ወንዶች ልጆች በህፃንነታቸው ወይም ከፍ ሲሉ መገረዛቸው ሲወርድ ሲዋረድ የመጣና አሁንም በየአካባቢው የሚከናውወን ልምድ ነው ። በአንዳንድ ባህሎች ደግሞ ግርዘት ቤተሰብ ተሰባስቦ በድግስና በፈንጠዝያ የሚያከብረው ስርዓት ነው ። ጀርመንን ጨምሮ በብዙ የዓለም ክፍል የሚከናወነውን ይህን የተለመደውን

A Turkish boy, in traditional circumcision costumes, sits as female worshippers perform prayers during the noon prayers at Eyup Sultan mosque in Istanbul, Turkey, Friday, Aug. 17, 2007. In accordance with Islamic tradition Muslim boys are circumcised before they reach puberty. (ddp images/AP Photo/Ibrahim Usta)
ምስል AP

የወንዶች ግርዛት የምዕራብ ጀርመንዋ የኮሎኝ ከተማ ፍርድ ቤት ህገ ውጥ ና በአካል ላይ ጉዳት ማድረስ ሲል ተቃወሞታል ።ድርጊቱ በወላጆች ስምምነት ቢፈፀምም እንኳን የጀርመንን ህግ ይፃረራል ሲል የወንዶች ልጆችን ግርዘት ተቃውሞ ውሳኔ አሳልፏል ። ውሳኔው ብዙዎችን ግራ አጋብተል ። ከሙንስተር ዩኒቨርስቲ በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት ዶክተር ሞግሃደም ፋታህ በወላጆች ፈቃድ የሚካሄደው ግርዛት ቀላልና የጤና ጠንቆች የማስከተሉ ሁኔታም እጅግ ዝቅተኛ ነው ። የሚታወቁ የጤና ጥቅሞችም እናዳሉት እየታወቀ የኮሎኙ ፍርድ ቤቱ በአንድ አጋጣሚ መነሻነት ይህን መሰል ውሳኔ ማሳለፉ ብዙዎች ያደናግራል ይላሉ ።
«እንደሚመስለኝ በኮሎኝ ፍርድ ቤት የተላለፈውን ብይን ጉዳዩ በሚመለከታቸው ወላጆችን ግርዘትን በሚፈፅሙና ለመፈፀም ምንጊዜም ዝግጁ በሆኑ ሐኪሞችና ክሊኒኮች ዘንድ በጣሙን ግራ የሚያጋባ ሁኔታ ነው የሚፈጥረው ። »
የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ጀርመን የሚገኙ የአይሁድና የሙስሊም ማህበረሰቦችን አስቆጥቷል ። ጀርመን የሚኖሩ ሙስሊሞችን ከሚያስተባብረው ምክር ቤት አሊ ኪዚልካያ ውሳኔውን የሰሙት ከታላቅ ሃዘን ጋር መሆኑን ነው የተናገሩት ። በርሳቸው አገላለፅ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ በሃይማኖት ጉዳዮች በሰፊው ጣልቃ የሚገባ ነው ። በሺህ ዓመታት ለሚቀጠር ዘመን ሲፈፀም የቆየን ልማድ የኮለኙ ፍርድ ቤት ህገ ወጥ ሲል መበየኑ ለእምነቱ ተከታዮች አስገራሚ እንደሆነ ነው ኪዚልካያ የተናገሩት ። በራሳቸው አገላለፅ ይበልጡን የሚያስደንቀው ይህ ዓይነቱ ውሳኔ የተላለለፈው በጀርመን ብቻ መሆኑ ነው ። ካዚካልያ በመላው ዓለም በአሜሪካም የወንዶች ግርዘት ሳይከለከል በጀርመን ህገ ውጥ መባሉ ሊገባቸው ያልቻለ ጉዳይ ነው ። ከእስልምናም ሆነ ከሌሎች ህይማኖቶች አስቀድሞ የነበረን የሰው ልጆች ልምድ ህገ ወጥ መባሉን ሊረዱት አልቻሉም


ሙዚቃ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
እስከዛሬ በጀርመን በየሆስፒታሉና በየክሊኒኩ ህጋዊ ሆኖ ሲፈፀም የቆየው ግርዛት እንዲህ ትልቅ ጉዳይ ሆኖ ፍርድ ቤት ሊደርስ የበቃው የ4 ዓመት ሙስሊም ወንድ ልጅ ከተገረዘ በኋላ ለውስብስብ የጤና ችግሮች በማደረጉ ነው ። ልጁ ከተገረዘ ከጥቂት ቀናት በኋላ ከባድ የደም መፍሰስ ስላጋጠመው ተመልሶ ወደ ሐኪም ቤት ይገባል ። ከዚህ በኋላም አቃቤያነ ህግ ልጁን የገረዘውን ሐኪም በልጁ አካል ላይ ከባድ ጉዳት በማድረስ ከሰውታል ። ፍርድ ቤቱ ድርጊቱ ህገ ወጥ መሆኑን ስለማያውቅ በርሱ ላይ መፍረዱ አግባብ አይደለም ሲል ሐኪሙን በነፃ አሰናብቶ ስለራሳቸው መወሰን የማይችሉ ህፃናትን በሃይማኖት ሰበብ መግረዝ በአካላቸው ላይ ጉዳት ማድረሰ ነው ሲል ወስኗል ። ፍርድ ቤቱ በዚሁ ውሳኔው በጉዳዩ ላይ ከወላጆች መሰረታዊ መብቶች ይልቅ የህፃኑ አካል እንዳለ ተጠብቆ የመቆየቱ መብት ሚዛን ይደፋልም ሲል ነው ያስታወቀው ። በዚህ ውሳኔ ክፉኛ ያዘኑት የአይሁድ ማህበረሰብ ተጠሪ አሮና ራን ቬርኒኮቭስኪ በይሁዲ እምነት ግርዘት ከጥንታዊዎቹ ትዕዛዛት አንዱ መሆኑንና ከእግዚአብሔር ጋራ የሚያስተሳስራቸው ና የእምነታቸውም መሰረት መሆኑን ነው ያስረዱት ። ግርዘት ከአይሁዶች ሊለይ የማይችል መሆኑን ያስረዱት ቬርኒኮቭስኪ የእምነቱ ተከታዮች ህፃናት ልጆች በተወለዱ በጥቂት ቀናት እንዲያስገርዙ የሃይማኖቱ መሪዎች ዘወትር እንደሚሰብኩ አስታውሰው ይህ ደግሞ በጀርመን ህገ ወጥ ሆኖ ከተከለከለ ልጆቻቸውን ለማስገረዝ ድርጊቱ ህጋዊ ወደ ሆነባቸው አገሮች ለመሄድ መገዳደቸው አይቀርም ይህ ደግሞ ለእምነቱ ተከታዮችም ሆነ ለሃይማኖት አባቶች አስቸጋሪ ነው ይላሉ ። ግርዛት እዚህ መከልከሉ ደግሞ ይላሉ ዶክተር ሞግሃደም ሌሎች መዘዞችን ማስከተሉ አይቀርም

Algerian boys dressed up in traditional outfits play around as they wait for their turns to be circumcised on the last week of the Muslim holly month of Ramadan at a hospital in Algiers, Algeria, 27 September 2007. Male circumcision is practised all over the world, for medical, religious, and ritual reasons. The operation involves cutting away all or part of the foreskin of the penis, and is usually undertaken either in infancy or at puberty. Muslims around the world practice circumcision for religious and cleanliness reasons, Ramadan is considered as an auspicious time to operate it, the event is often viewed communally as a joyous occasion and celebrated with sweets, gifts for the little boys and the purchase of a traditional outfit for that special day. EPA/MOHAMED MESSARA +++(c) dpa - Report+++
ምስል picture-alliance/dpa


«የኮሎኙ ብይን የሚያስከትለው አደጋ ምናልባት ሃይማኖታዊ ግርዘት ለሚያከናውኑ ወገኖች ከመደበኛ ክሊኒኮች ውጭ ጥራትም ሆነ ንፅህናው ያን ያህል ባልተሟላ ቦታ ተግባራዊ እንዲያደርጉ የሚገፋፋ መሆን መቻሉ ነው ። እዚህ ላይ እኔ የምሰጋው እርስ በርሱ የሚቃረን ሁኔታ እንዳይፈጠር ነው ። ጉዳዩ የሚመለከታቸው ልጆች የጤንነት አጠባበቅ ደረጃ በብይኑ ምክንያት ከመሻሻል ይልቅ እንዳይባባስ ያሰጋል ። »
ዶክተር ሞግሃደም ወላጆች ልጆቻቸውን ማስገረዛቸው ልጅን የማሳደግ መብታቸውን አለአግባብ መጠቀም ማለት እንዳይደለም ያስረዳሉ ። በአሁኑ ጌዚ ትኩረት የተሰጠው በልጃገረዶች ላይ የሚፈፀመው ግርዘት ያለ አንዳች ማመንታት እንዲከለከል መደረጉ ነው ። አንዳንዶች አስተያየት ሰጭዎች አሁን የተከሰተውን ችግር ለማስቀረት በጀርመን በህግ አንድ አዲስ አንቀፅ መከታቱ ይጠቅማል ይላሉ ። ማርቲን ቦዘ ግን በሃይማኖት ሳቢያ ወንዶች ልጆች እንዲገረዙ የማይከለክ ልዩ የሆነ የህግ አንቀፅ ይፈቀድ መባሉን ይህን ያህል የሚሰምር ሆኖ አይታያቸውም
« የልጃገረዶችን ግርዘት የማዋለጃ አካልን ክፉኛ በመጉዳት የሚከናወን ተግባርን በቀጥታ የሚፃረር ረቂቅ ህግ ቀርቧል የዚህም ረቂቅ ህግ ዋና ትኩረት የእንዲህ ዓይነቱን አካልን የመተልተል እርምጃ በአንፃሩ የሚያስቀር ነው ። ሃይማኖታዊ ልምዶችን መሠረት ያደረገና ለይቶ የሚተውና ከቅጣት ነፃ የሚያደርግ መመሪያ ይውጣ ከተባለ ደንቡ ወደፊት ምን መዘዝ እንደሚያስከትል ለማወቅ
ያዳግታል ። »

Undatiertes Archivbild zeigt den türkischen Beschneider Murat Özkan (r), der in Istanbul die Hose eines Jungen öffnet, um ihn anschließend zu beschneiden. Allein beim Gedanken an eine Beschneidung verziehen die meisten Europäer vor Schmerz das Gesicht und legen schützend die Hand über ihr Geschlecht. In der Türkei und zahlreichen anderen moslemischen Ländern gehört das Beschneidungsfest aber zum Leben jedes Mannes wie in Deutschland religiöse Feste wie Taufe, die Kommunion oder die Konfirmation. dpa (zu dpa-Reportage "Kleiner Schnitt, großes Ereignis...")
ምስል picture-alliance/dpa

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ