1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አካል ጉዳተኞች በኢትዮጵያ

ሐሙስ፣ ኅዳር 26 2006

በያዝነዉ ሳምንት ህዳር 24፤ የዓለም የአካል ጉዳተኞች ቀን ለ22 ኛ ግዜ ታስቦ ዉሎአል። የተመድ ያወጣዉ ዘገባ እንደሚያመላክተዉ በዓለም ከሚኖሩ ህዝቦች መካከል 15 ከመቶዉ ቀላል እና ከባድ የአካል ጉዳተኞች ናቸዉ። በኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ላይ የሚደርስዉ ተፅኖ እና በተለያዩ ዘርፎች ያላቸዉ እንቅስቃሴ ምን ይመስላል?

https://p.dw.com/p/1ATV5
Symbolbild Behinderung
ምስል Fotolia/apops

የአካል ጉዳተኞች በየዕለተ ኑሮአቸዉ በማህበራዊ ኑሮ፤ በኤኮኖሚ እንዲሁም፤ በአካላዊ ጉዳት ከባድ ችግር ይደርስባቸዋል። ዓለም አቀፉ የአካል ጉዳተኞች ቀን በኢትዮጵያ ለ 21ኛ ግዜ ታስቦ ዉሎአል። በኢትዮጵያ የሚገኙ አካል ጉዳተኞች ባህላዊ፤ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መሰናክሎች፤ እንዳይገትዋቸዉ ምን እየተደረገ ነዉ፤ የለቱ ቅንብራችን የሚዳስሰዉ ጉዳይ ነዉ ።

Rainer Schmidt, Serie Glück, Tischtennis
ታዋቂዉ የጠረቤዛ ቴኒስ ተጫዋች ራይነር ሽሚድምስል Johannes Hahn

ህዳር 24 ቀን በኢትዮጵያ ለ 21 ኛ ግዜ ዓለማቀፉ የአካል ጉዳተኞች ቀን ተከብሮ መዋሉ ተነግሮአል። በአዲስ አበባ ከተማ በሀገር ፍቅር «ሁሉን አቀፍ ኅብረተሰብ ለመገንባት መሰናክሎች ይወገዱ፤ በሮችም ይከፈቱ» በሚል መርህ ቃል በድምቀት እንደተከበረ፤ አይነ ስዉሩ የብስራት ፕሮሞሽን ዋና ሥራ ስኪያጅ ጋዜጠኛ ገድለሚካኤል አበበ ይገልጻሉ። ዓለማቀፉ የአካል ጉዳተኞች ቀንን ፤ በማስመልከት በርካቶች ተሳታፊ በሆኑበት ዝግጅት እጅግ መደሰታቸዉን የነገሩን በኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ካሳሁን ይበልጣል፤ እንደሚሉት በአጉል ልማድ ህብረተሰቡ ዉስጥ ሰርጾ የቀረዉን ልምድ ማስወገድ ያስፈልጋል፤ባህል ከተባለ፤ እንግዲያዉ ከአነጋገር እንጀምር ያለን የብስራት ፕሮሞሽን ዋና ሥራ ስኪያጅ አይነስዉሩ ጋዜጠኛ ገድለሚካኤል አበበ፤ አይነ ስዉር፤ የዓይን ብርሃን የሌለዉ፤ እጅ የሌለዉ ቆማጣ፤ ሽባ ከሚለዉ የቃላት መረጣ ይልቅ፤ ቅን የሆነዉ ልባዊ ሃሳቡ ከሁሉ በላይ ለአካል ጉዳተኛዉ የተሻለዉ ነዉ።

በኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ካሳሁን ይበልጣል፤ እንደሚሉት በሀገራችን የአካል ጉዳተኞችን በተመለከተ የሚታየዉ መሰረታዊ ችግር በሃዘኔታ የተቃኘ ባህላዊ የአመለካከት ሌላዉ አላስፈላጊዉ ጉዳይ ነዉ።

Berlin Demonstration von Taubblinden
ምስል picture-alliance/dpa

እንደ ጋዜጠኛ ገድለሚካኤል፤ ከሁሉ ከሁሉ አካል ጉዳተኞችን በህብረተሰቡ እንቅስቃሴ ማካተት ይኖርብናል፤ ሲል በአንክሮ ገልጾልናል። በኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ካሳሁን፤ ፌደሬሽን መስሪያ ቤታቸዉ ባህልን አስታኮ የሚታየዉን አጉል ልማድ ለማስቀረት በትጋት ላይ ቡሆነም አሁንም በቂ እንዳልሆነ ሳይገልጹ አላለፉም። አካል ጉዳተኞች የአንዳ ማህበረሰብ አካል ናቸዉና፤ በሁሉም የስራ ዘርፍና የትምህርት መስክ ተሳታፊ እንዲሆኑ መንግሥት የበለጠ ጥረት ሊያደርግ ይገባል ያሉንን፤ የለቱን እንግዶቻችንን ለሰጡኝ ቃለ ምልልስ እናመሰግናለን። ሙሉዉን ዝግጅት የድምፅ ማድመጫዉን በመጫን ይከታተሉ!

አዜብ ታደሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ