1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አክራ፥ የኢትዮጵያ እቃ ጫኝ አውሮፕላን አደጋ

ቅዳሜ፣ ጥር 2 2007

ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ የእቃ ማመላለሻ አውሮፕላን ዛሬ ጋና መዲና አክራ ውስጥ ለማረፍ በሚያደርገው ሙከራ የመንሸራተት አደጋ እንደገጠመው የፈረንሳይ ዜና ወኪል ዘገበ።

https://p.dw.com/p/1EIQg
Boeing 787 Ethiopian Airlines
ምስል Reuters

መነሻውን ከቶጎ ዋና ከተማ ሎሜ ያደረገው ቦይንግ 737 ሮፕላን ከረፋዱ 5 ሰዓት ከ 05 ደቂቃ ለማረፍ ባደረገው ሙከራ ነው ችግር እንደገጠመው የተገለጠውአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩት ሦስት ራተኞች ህክምና ተደርጎላቸው ከሐኪም ቤት መውጣታቸውን የዜና ምንጩ አክሎ ገልጿል። የጋና የበረራ ተቆጣጣሪ ባለስልጣናት፤ የአደጋውን መንስኤ ማጣራት ጀምሯል። አውሮፕላኑ በሚያርፍበት ወቅት የአየሩ ኹናቴ ንፋሣማ እና እይታን የሚጋርድ እንደነበረም አንዳንድ ዘገባዎች ጠቅሰዋል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ልደት አበበ