1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አወዛጋቢዉ የሰንዳፋ የቆሻሻ መጣያ

እሑድ፣ ነሐሴ 29 2008

ለመዲና አዲስ አበባ የደረቅ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ እንዲሆን ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበት የተገነባዉ የዘመናዊዉ የ«ሰንዳፋ ሳኒተሪ ላንድ ፊልድ» በነዋሪዎች ተቃዉሞ ካስነሳ በኋላ መታገዱ የሚታወቅ ነዉ።

https://p.dw.com/p/1JvWK
Äthiopien Addis Abeba Müll
ምስል DW/Y. Geberegiabeher

አወዛጋቢዉ የሰንዳፋ የቆሻሻ መጣያና የመዲናዋ የቆሻሻ ክምር

እገዳዉ በአዲስ አበባ ላይ ተፅኖ አሳድሮአል። በየመንገዱ፣ በየበሩ አጥርና ግምብ ሥር አልያም ሜዳ ላይ የሚጣለዉ ቆሻሻ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን፣ እንግዶችዋን ሁሉ ለከፍተኛ ጉዳት እየዳረገዉ ነዉ። ተቃዉሞ የገጠመዉን የሰንዳፋ የደረቅ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ጉዳይ በተመለከተ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና የኦሮሚያ ክልል ውይይት ቢያካሂዱም ስምምነት ላይ አለመድረሳቸው ተገልጿል። አገልግሎት ከጀመረ ሰባት ወራት በኋላ የተዘጋዉ ዘመናዊ የደረቅ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ በተገነባበት የመሬት ይዞታ ላይ የአካባቢዉ ነዋሪ እንዲገነባ የፈቀደዉ ልማትን የሚያራምዱ ማዕከላት እና የአዉሮፕላን ማረፍያ ይገነባል በመባሉ እንደነበር ተጠቅሷል። የአካባቢው አርሶ አደሮችም ይህንኑ በመናገር ይከሳሉ። በአዲስ አበባ ይህ የቆሻሻ አለመነሳት ችግር የተከሰተበት ወቅት ክረምት በመሆኑ የቆሻሻ ማጠራቀምያዎች እየሞሉ በአካባቢዉ መጥፎ ሽታ ከመፈጠሩ ሌላ እጅግ አሳሳቢ የጤና ችግር አስከትሏ። በመሆኑም አፋጣኝ መፍትሄ መፈለግ እንዳለበት ነዋሪዎች በተደጋጋሚ አመልክተዋል።

ሙሉ ዉይይቱን፦ የድምፅ ማዳመጫውን በመጫን መከታተል ይቻላል።


አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ