1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አወዛጋቢው የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን

ሐሙስ፣ ጥር 30 2011

የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ በቅርቡ በነጋሪት ጋዜጣ ይታተማል። ይሕ ኮሚሽን በትግራይ ክልላዊ መንግሥት ተቃውሞ ገጥሞታል። በየሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ዳባ አዋጁ የቀረበበትና የጸደቀበት መንገድ ከሕገ-መንግሥቱ ጋር የሚቃረን አይደለም ብለዋል።

https://p.dw.com/p/3CwbD
Tesfaye Daba
ምስል Privat

አቶ ተስፋዬ የኮሚሽኑ መቋቋም ከሕገ-መንግሥቱ አይጋጭም ብለዋል

የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን 41 አባላትን አፅድቋል። የኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ በቅርቡ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ይፋ ይሆናል። ይሕ ኮሚሽን ግን በትግራይ ክልላዊ መንግሥት ተቃውሞ ገጥሞታል። ኮሚሽኑን ያቋቋመው አዋጅ ሲጸድቅ ሕገ-መንግሥታዊ ጥሰት ተፈፅሟል ሲል የከሰሰው የትግራይ ክልል ምክር ቤት የትግራይ ክልል መንግስት ስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት ጉዳዩን በዝርዝር አይቶ የትርጉም ጥያቄ ለፌደሬሽን ምክር ቤት እንዲያቀርብ አሳስቧል። በኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ዳባ ግን አዋጁ የቀረበበት እና የጸደቀበት መንገድ ከሕገ-መንግሥቱ ጋር የሚቃረን አይደለም ብለዋል።

እንዳልካቸው ፈቃደ

እሸቴ በቀለ

ኂሩት መለሰ