1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አወዛጋቢው የዓለም ዓቀፉ ፍርድ ቤት ብይን

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 20 2002

«የኮሶቮ ነፃነት የማይቀለበስ ሂደት ነው ። የህዝቤም ነፃነትም እንዲሁ ። ዛሬ አሸናፊዎችም ተሸናፊዎችም የሉም ። ፍርድ ቤቱ በኮሶቮ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ተቀብሏል ። ለሐገሬ ለክፍለ ሐገሬ ለህዝቤ እና ለአካባቢው አዲስ ምዕራፍ ነው ። » ከሁለት ዓመት በፊት ነፃነትዋን ያወጀችው የኮሶቮ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀሺም ታቺ ፥

https://p.dw.com/p/OW0W
ምስል AP

« ማንም ዕውቅ ዓለም ዓቀፍ ተሰሚነት ያለው ኃይል በዚህ በጣም ጠባብ አሰተሳሰብ በተሰጠ የፍርድ ቤት ብይንና እና ቴክኒካዊ ውሳኔ በኮሶቮ ላይ ያለውን አቋም ይለውጣል ብዮ አልጠብቅም ።ሰርቢያን በተመለከተ እርግጥ ነው የህገ መንግስታችንን አቋም በምንም ዓይነት አንለውጥም »

የሰርቢያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቩክ የርሚክ

ኔዘርላንድስ ዴንሀግ የሚገኘው ዓለም ዓቀፉ ፍርድ ቤት የኮሶቮ ነፃነት ዕወጃ ዓለም ዓቀፍ ህግን የጣሰ አይደለም ሲል ባለፈው ሳምንት የሰጠው ይህ ብይን ኮሶቮን ተጨማሪ ዕውቅና ለማግኘት ሲያተጋ ሰርቢያን ደግሞ በኮሶቮ ጉዳይ ላይ አዲስ ድርድር እንዲካሄድ ጥያቄ ለማቅረብ አነሳስቷል የዛሬው አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅታችን ትኩረት ነው

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ