1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አወዛጋቢው የድንበር መከፈት ጉዳይ በጀርመን

ሐሙስ፣ መጋቢት 29 2008

የባየርን ጠቅላይ ሚኒስትር በጉዳዩ ላይ ትናንት በርሊን ውስጥ ከጀርመን መራሄ መንግሥትና ምክትል መራሄ መንግሥት ጋር ተነጋግረዋል ።

https://p.dw.com/p/1IRZJ
Deutschland Regierungskoalition Seehofer Merkel und Gabriel Symbolbild
ምስል picture-alliance/AP Photo/B. von Jutrczenka

[No title]


የጀርመን የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ቶማስ ደ ሚዜር ጀርመንን ከኦስትሪያ ጋር የሚያዋስናት ድንበር በቅርቡ ሊከፈት እንደሚችል መናገራቸው ያስነሳው ውዝግብ እልባት አላገኘም ። ስደተኞች በብዛት ወደ ጀርመን የሚገቡበት የደቡባዊ ጀርመንዋ የባቫርያ ፌደራዊ ክፍለ ሃገር አስተዳዳሪና የጀርመን ተጣማሪ መንግሥት አካል የሆነው የክርስቲያን ሶሻል ህብረት ፓርቲ ድንበሩ ይከፈታል መባሉን ተቃውሟል ። የፓርቲው መሪ የባየርን ጠቅላይ ሚኒስትር በጉዳዩ ላይ ትናንት በርሊን ውስጥ ከጀርመን መራሄ መንግሥትና ምክትል መራሄ መንግሥት ጋር ተነጋግረዋል ። ስለ ውዝግቡና ስለ ንግግሩ የበርሊኑን ወኪላችንን ይልማ ኃይለ ሚካኤልን በስልክ አነጋግሬዋለሁ ።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ