1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዉሮጳና ጀርመን

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 6 2005

ከሶስት መቶ ዓመታት በላይ የታላቋ ብሪታኒያ አካል የሆነችው ስኮትላንድ እአአ በ2014 በህዝበ ውሳኔ እድሏን ትወስናለች። በብሪታኒያው ጠቅላይ ምኒስትር ዴቪድ ካሜሩንና ና የስኮትላንድ ግዛት መሪ አሌክስ ሳልሞንድ የስምምነት ፊርሚያውን ትናንት ከወረቀት አስፍረዋል።

https://p.dw.com/p/16R39
File picture shows supporters and members of Bulgaria's Roma community behind a European Union flag during a protest in front of the French embassy in Sofia September 18, 2010. The European Union won the Nobel Peace Prize on October 12, 2012 for its historic role in uniting the continent. Picture taken September 18, 2012. REUTERS/Stoyan Nenov/File (BULGARIACIVIL DAY - Tags: CIVIL UNREST SOCIETY)
የአዉሮጳ ሕብረት አርማምስል Reuters

ባሳለፍነው ዓርብ የአውሮፓው ህብረት የኖቤል የሰላም ሽልማትን ተቀብሏል። አብዛኛውን ጊዜ ለፖሊቲከኞች፣ ለሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎችና ግለሰቦች የሚሰጥ ሽልማት ነው። የሽልማቱ ለአውሮፓ ህብረት መሰጠት ከየጎራው ውዳሴና ወቀሳን አስተናግዷል።  

ብራሲልስ ላለፉት ወራት  በአውሮፓ የፊናንስ ቀውስ ምክንያት ድምዝዝ ብላ ቆይታለች። ይህ ብራሲልስን የተጫጫነ ቀውስ ሌሎች የህብረቱ ሀገራት ላይም ታይቷል። አውሮፓ በዚህ ሁኔታ እያለች ነበር የኖቤል ሰላም ሽልማት ለአውሮፓ ህብረት እንደሚሰጥ የተሰማው። ይህ የኖቤል ሽልማት ውሳኔ የተለያዩ አስተያየቶችን አስከትሏል። ባንድ ጎን አውሮፓን ከጦርነት አውድማ አንስቶ የሰላም ተምሳሌት እንድትሆን ስላደረገ፣ ህብረቱ ሽልማቱ ይገበዋል የሚሉ ሲኖሩ፣ በሌላ ጎኑ በአውሮፓ በተፈጠረው የፊናንስ ቀውስና በሰበቡ እየሰፋ በሄደው የኢኮኖሚ ልዩነት  ምክንያት ህብረቱ ለዚህ ክብር መታጨት አልነበረበትም የሚሉ  አልጠፉም።

ብዙ የአውሮፓ ፖሊቲከኞች አህጉሯ በፊናንስ ችግር በተከበበት በዚህ ሰዓት ሽልማቱ የህብረቱ ሀገራት ችግራቸውን እንዲፈቱ ብርታት ይሰጣቸዋል ሲሉ ተናግረዋል። ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት ፍጻሜ  በኋላ ህብረቱ ለማቋቋም የመጀመሪያዎቹ ን እርምጃዎች የጀመሩት ፈረንሳይና ጀርመን፣ የሽልማቱን ለአውሮፓ ህብረት መሰጠት «ድንቅ ውሳኔ» ሲሉ አሞካሽተዋል።   የጀርመኗ መራሄተ-መንግስት አንጌላ መርከል  ሽልማቱ ኃላፊነትንም እንደሚያሸክም ተናግረዋል።

«የኖቤል ሽልማት ኮሚቴው ይህንን ሐሳብ፣ ማለትም አውሮፓን አንድ የማድረጉን ሂደት፣ ማድነቁ ለኛም ሆነ ለነ በግሌ፣  ተነሳሽነትን የሚሰጠን  ሲሆን  ኃላፊነትንም ያሸክመናል።»

የአውሮፓው ኮሚሽን ሊቀመምበር ጆዜ ማኑኤል ባሮሶ  በሽልማቱ ምክንያት መደሰታቸውን ሲገልጹ የኢጣሊያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ማሪዮ ሞንቲ ደግሞ የአውሮፓ ህብረት አሁን ካለበት ቀውስ እንድወጣ ሽልማቱ ብርታት ይሆነዋል ሲሉ ተናግረዋል።

 የአውሮፓው ህብረት ፓርላማ ፕረዝዳንት ማርቲን ሹልዝ ሽልማቱ የአውሮፓን እርቅና ለተቀረውን ዓለም ምሳሌ መሆኗን ያሳያል ብለዋል፥

«ይህ የሚያሳየው፣ ብልሁ የኖቤል ሽልማት ኮሚቴ አውሮፓን አንድ የማድረግ ሥራ ውስጥ   የአውሮፓ ህብረት ለወከለው እሴት ያ ማለትም፣ የውስጥ ሰላምና ብልጽግናን ማረጋገጥና እሴቱንም ለሌላው ዓለም ለማሳየቱ  እውቅና መስጠቱን ነው።»

አውሮፓ በታሪኳ በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ አስተሳሰቦች የፈለቁባት አህጉር ናት። በምድሯ ውስጥ የበቀሉ እነኚ አስተሳሰቦች በዛው ሳይወሰኑ ሌሎችንም ያለማችንን ክፍሎች ነክተዋል። የሚሊዮኖችን ህይወትና ለግምት የሚያዳግት ንብረት ያጠፉ ሁለቱ የዓለም ጦርነቶች የተጀመሩትና የተፈጸሙት በአውሮፓ ምድር ነው። ጦሱ ግን ለሌላም ዓለም ተርፏል።   በአውሮፓ ኢኮኖሚ  ማህበር ትስስር የተጀመረው የአውሮፓ ህብረት፣ እንደ ስፔን ላሉ ለ30 ዓመታት በፈላጭ ቆራጭ መንግስት ስር ለነበሩ ሀገራት የዲሞክራሲ ጮራን ፈንጥቋል። እንደ ፖርቹጋልና ግሪክ ያሉ አምባ ገነን መንግስታት በአውሮፓ ህብረት ጥላ ስር ሆነው ለዜጎቻቸው ሰብዓዊ መብት መጠበቅ መሰረት ጥለዋል።

እአአ በ1993 የበርሊን ግምብ መፍረስ ተከትሎ የሶቪዬት ቁጥጥር ስር የነበሩ ሀገራት የፈለጉትን ነጻነትና እድል በአውሮፓ ህብረት ስር ሆነው አግኝተዋል። አውሮፓ ውስጥ ዛሬ አምባ ገነንነት ያረጀ  ታሪክ ሆኗል።  

አውሮፓ የፋይናንስ ችግሩና የሰሜንና የደቡብ አውሮፓ ፖሊቲካዊ  የውስጥ አለመግባባቱ እያመሳት እያለ ነው የኖርዌዩ የኖቤል ሽልማት ኮሚቴ ብዙም ያልተለመደውን ውሳኔውን ያሳወቀው። ሽልማቱ በተሰጠበት እለት ስፔን ውስጥ አንድ ብሔራዊ በዓል ሲከበር ነበር። ዘንድሮ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ በበዓሉ የተገኙ ሰዎች ቁጥር አነስ ያለና በዓሉም ድምዝዝ ያለ ነበር። የተለመደው ዓመታዊ የወታደሮች ትርዒት ላይ የተገኙት ጥቂት ወታደሮችና ተመልካቾች ነበሩ። ብዙ ስፔናዊያን የአውሮፓ ህብረት ሐብታም ሀገራት አጋርነትን ይፈልጋሉ፣ ስለ ሽልማቱ ሲናገሩ ግን ጠንቀቅ እያሉ ነው፣  

የህዝብ አስተያየት

«ይህ ሽልማት ብዙም አያረካኝም»

«በርግጥ ደስ ብሎኛል። እውነት በጣም ኮርቻለሁ።»

«አዎን ለአውሮፓ ህብረት እንዲህ ዓይነቱን ሽልማት መስጠቱ  ከበስተጀርባው አንድ  ነገር እንዳለ ያሳያል።  ያ ፍትሐዊ  አይመስለኝም።»

በፊናንስ ቀውሱ ክፉኛ የተመታች በግሪክ የሽልማቱ ዜና ከቀን ተቀን ኑሮ ጋር እየተጋፈጡ ላሉ ነዋሪዎቿ ብዙም የደስታ ምንጭ አልሆነም።

«የአውሮፓ ዩኒየን ለመረጋጋቱ  ያበረከተው ነገር አለ ብዬ አላምንም። ቢሆን ኖሮ አሁን ወዳለንበት  ውጥንቅጥ አንገባም ነበር።»

«የኖቤል ሽልማት ነው? ሰሜኖቹ ደቡቦቹ ላይ የሚጮሁበት እዚህ አውሮፓ ውስጥ?»  

የኖቤል የሰላም ሽልማት ለአውሮፓ መሰጠቱን የግሪክ ዜጎች ብቻ ሳይሆን አንዳንድ የአውሮፓ ፖሊቲከኞችም ተቃውመውመታል። ማርቲን ካላናን የተባሉ ብሪታኒያዊው የአውሮፓ ፓርላማ አባል፣ የኖቤል ሽልማት ኮሚቴው ትንሽ ባያረፍድ ኖሮ ጥሩ የአፕሪል ዘፉል ቀልድ ይወጠወዋል ሲሉ አፊዘዋል።   የአውሮፓ ህብረት ፖሊሲዎች የፊናንስ ቀውሱን አባብሰው ለዘመናት ወዳልታየው ማህበራዊ አለመረረጋጋት መርተውናል  ሲሉም ሽልማቱ ለህብረቱ መሰጠቱን አጣጥለውታል። የታላቋ ብሪታኒያ የነጻነት ፓርቲ አባል ናገል ፋራጌ ላለፉት ሁለት ዓመታት የአውሮፓ ህብረት በሰሜንና ደቡብ አውሮፓ ሀገራት መካከል ጠላትነትን አስፍኗል ሲሉ ይከሳሉ።

 
ባጠቃላይ አብዛኛዎቹ አውሮፓውያን አህጉሯ ያንን ዘግናኝ የጦርነት ታሪክ ካስወገደች አሁን ያለውን የፊናንስ ቀውስ ማስወገዱ አይሳናትም ብለው ሲያምኑ፣  አውሮፓን አንድ የማድረጉ ስራ ከስሟል ብለው የሚያምኑም አልጠፉም።

Britain's Prime Minister David Cameron (L) is greeted by Scotland's First Minister Alex Salmond on the steps of St Andrews House in Edinburgh, Scotland October 15, 2012. Scotland takes a big step on its path towards an independence referendum on Monday when its leader meets Britain's prime minister to finalise arrangements for a vote which could lead to the demise of Scotland's three-centuries-old union with England. REUTERS/David Moir (BRITAIN - Tags: POLITICS)
ካሜሩንና ሳልሞንድምስል Reuters
HANDOUT - Undatierte Aufnahme zeigt die Vorderseite der Medaille des Friedensnobelpreises, die 1902 von dem norwegischen Künstler Gustav Vigeland enworfen wurde. Das Nobelkomitee in Oslo hat den Friedensnobelpreis 2012 nach offiziell noch unbestätigten Angaben an die EU vergeben. Das berichtete der Osloer Rundfunksender NRK am 12.10.2012 kurz vor der Bekanntgabe der Entscheidung. Die EU ist in den letzten Jahren als «erfolgreiches Friedensprojekt» immer wieder für die Auszeichnung nominiert worden. Foto: Berit Roald dpa (zu dpa 0377 «Rundfunk: Friedensnobelpreis 2012 an die EU» am 12.10.2012) +++(c) dpa - Bildfunk+++
ኖቤል አርማምስል picture-alliance/dpa
epa03394032 Flags are seen in front of the European Parliament in Strasbourg, France, 11 September 2012 during the plenary session of the European Parliament. EU member states must for the first time implement binding energy-saving measures in a push to reduce the bloc's energy consumption by 20 per cent by 2020, compared to 1990 levels. The measures, agreed to Tuesday by the European Parliament, include a 1.5 per cent year-on-year reduction in energy sector sales to consumers, the partial renovation of government-owned buildings and energy audits for large companies. EPA/PATRICK SEEGER
የአዉሮጳ ሕብረትምስል picture-alliance/dpa

በርካታ የአውሮፓ ክፍለ ግዛቶች ከማዕከላዊ መንግስታት ነጻ ለመውጣት ይፈልጋሉ፣  ስኮትላንዳዊያን ከብሪታኒያ, የባስክና የካታላን ህዝቦች ከስጳኝ፣ ፍሌማዊያንና ዋሉናዊያን  ከቤልጂዬም። ለዘመናት በብሪታኒያ ግዛት ስር የምትገኘው ስኮትላንድ በህዝበ ውሳኔ እድሏን ለመሰን ትናንት ከብሪታኒያ ጋር ከስምምነት ደርሳለች።

ከሶስት መቶ ዓመታት በላይ የታላቋ ብሪታኒያ አካል የሆነችው ስኮትላንድ እአአ በ2014 በህዝበ ውሳኔ እድሏን ትወስናለች።  በብሪታኒያው ጠቅላይ ምኒስትር ዴቪድ ካሜሩንና ና የስኮትላንድ ግዛት መሪ  አሌክስ ሳልሞንድ የስምምነት ፊርሚያውን ትናንት ከወረቀት አስፍረዋል።  የስኮትላንድን ከብሪታኒያ መለየት በጽኑ የሚቃወሙ ዴቪድ ካሜሩን የሁለቱ ግዛቶች ህዝቦች ከመለያየት ይልቅ አብሮ መኖርን እንደሚመርጡ ያላቸውን  ተስፋ ገልጸዋል፣

«ስኮትላንድ ከብሪቲኒያ ጋር ብትሆን፣ ብሪታኒያም ከስኮትላንድ ጋር በአንድነት ብትቀጥል ለሁለቱም ሀገራት ይበጃል የሚል ልባዊ እምነት አለኝ ። አብረን ስንኖር የተሻለን እንሆናለን። አብረን ስንኖር የበለጠ ብርቱዎች እንሆናለን። አብረን ስንኖር የጋራ ደህነት ይኖረናል። አብረን ስንኖር የተሻለን እንሆናለን። አሁን እሰጣ ገባውን ልተወውና፣ ህዝቦች እኒኚን ሁለቱ ሀገራት አስተሳስሮ የሚያኖር ውሳኔ ይወስናሉ ብዬ ተስፋ ላድርግ።»

የስኮትላንድ ግዛት መሪ አሌክስ ሳልሞንድም ከፊትለፊት ያሉ ሁለት ዓመታት የስኮትላንድን እድል የሚወስኑ መሆናቸውን ተናግረዋል፣

«ይህ ታሪክ ነው። የታሪክ እጅ ትከሻዬ ላይ ነው ባልልም፣ ዛሬ በግልጽ ታላቅ ቀን ነው። ለስኮትላንድ ይህ ታላቅ ቀን ነው። ያገራችንን የወደፊት እድል የሚወስኑ ሁለት ታላቅ ዓመታትም እየመጡ  ናቸው።»

በአውሮፓ ከማዕከላው መንግስት መለየት የሚፈልጉ የአውሮፓ ግዛቶች አብዛኛውን ጊዜ በኢኮኖሚው ጠንካራ የሆኑ ናቸው። እንደ የአውሮፓ ስታቲስቲክስ ባለስልጣን ከሆነ እጎአ በ2009 አንድ ሶስተኛ የሚሆን የስፔን አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ገቢ  የሚመነጨው 10 በመቶ የስፓኝ ጠቅላላ ግዛት  ከሚሸፍኑ ከባስክናና  ካታላን ነው። በጥሩ የኢኮኖሚ ሁኔታ ላይ የሚገኙ የሰሜን ኢጣሊያ ግዛቶችና ደቡብ ቲሮል እንዲሁም እንደ ሚላን ያሉ ትላልቅ ከተሞች በኢኮኖሚው ደከም ያለውን የደቡብ ኢጣሊያን ክፍል በገንዘብ መደገፉን መቀጠል አይፈልጉም። ስኮቲላንዳዊያንም ከነዳጅ ዘይት ምርት የሚገኘውን ገቢ ለራሳቸው ማስቀረት ይፈልጋሉ። ከሁሉም በላይ አስቸጋሪው በቤልጂዬም የሚገኙ የፍሌማውያን ከፈረንሳየኛ ተናጋሪው የደቡብ ክፍል መገንጠል መፈለግ ነው። የፍላንደር ግዛት በርግጥ የሚሸፍነው የሀገሪቷ አንድ ሶስተኛው መሬት ነው፣ ሆኖም ግን 60 በመቶ አጠቃላይ የሀገሪቷ  የውስጥ ገቢ ከዚህ ክልል ይገኛል።

ከኢኮኖሚው ጥቅምም ባሻገር፣  ከዋናው ሀገር ነጻ የመሆን ጥያቄን ሊያስነሱ በሚችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ብዙ የክርክር ሐሳቦች ይታያሉ ይላሉ በኪል ዩኒቨርስቲ የስነ-ህዝብ ምርምር ፕሮፈሰሯ ሲልኬ ጉትሽ-ኤልተን።  ሁሉም ግን የሚያመለክቱት ያንድን ቡድን ማንነት ወደሚያሳዩ እንደ ቋንቋ፣ የጋራ ታሪክና  ባጠቃላይ እንደ ባህል ሊታዩ ወደሚችሉ ነገሮች ናቸው። ሐይማኖትና የቦታ አቀማመጥም ትልቅ ሚና ልጫወቱ ይችላሉ።  

እንደ ስፔንና አየርላንድ ባሉ ሀገራት ውስጥ አልፎ አልፎ በተገንጣይ ቡድኖች የመገንጠል ሙከራዎች ቢደረጉም የዓለም አቀፍ ህግ ባለሙያው ክርስቲያን ሂልግሩበር፣ በኤርትራና ምስራቅ ቲሞር እንዲሁም በሱዳን እንደሆነው  ከባድ የፖሊቲካ መገለል አይከሰትም ባይ ናቸው።

አሁን በስኮትላንድ  የሚታያየውን ከማዕከላው መንግስት የመለየትን ፍላጎት የዓለም አቀፍ ህግ ባለሙያው  በተለየ ዓይን ይመለከቱታል ። እንደ ባለሙያው እምነት አንድ ሀገር መገንጠል ከፈለገች የመገንጠል ሂደቱ ሊያመጣ የሚችል የሐብትና የዕዳ ክፍፍል ሊታይ ይገባል።  ስኮትላንድ የብሪታኒያን መንግስት እዳዎች በግማሽ የማትካፈል ከሆነ ሙሉ ነጻነት ሊኖራት አይችልም። ስኮትላንዳውያን ሙሉ በሙሉ ከብሪታኒያ ሳይገነጠሉ  የኢኮኖሚን ነጻነት ከሎንዶን ቢያገኙ የሚሻለው በዚህ ምክንያት  ነው።

ገመቹ በቀለ

አርያም ተክሌ   
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ