1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዉሮጳ ኅብረት፤ ስደተኞችና ቱርክ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 2 2008

የአዉሮጳ ኅብረት ወደ አባል ሃገራቱ የሚገቡትን ስደተኞች ቁጥር ለመግታትና በስደተኞች ምክንያት በአህጉሩ ተፈጥሯል የተባለዉን ቀዉስ ለማስወገድ ከቀየሳቸዉ ዘዴዎች መካከል አንዱና ዋንኛዉ በቅርቡ ከቱርክ ጋር የገባዉ ዉል ነዉ።

https://p.dw.com/p/1Il8T
Symbolbild Aufhebung Visumspflicht für türkische Staatsbürger
ምስል Getty Images/C. McGrath


የስምምነቱ ዋና ጭብጥ ከቱርክ እየተነሱ ወደ ግሪክና ወደ አዉሮጳ የሚገቡትን ስደተኞች ቱርክ እንድትቆጣጠርና በሕገ ወጥ መንገድ ግሪክ የደረሱትንም መልሳ እንድትወስድ የሚጠይቅ ሆኖ በምትኩም በተለይ የሶርያ ስደተኞች ወደ አዉሮጳ እንዲመጡ የሚደረግ መሆኑን የሚገልፅ ነዉ። ለዚህም ቱርክ በሶስት አመታት ውስጥ 6 ቢሊዮን ዩሮ ርዳታ ይሰጣታል፤ አንዳንድ ቅድመ ሁኔታዎች ከተሟሉም ዜጎችዋ ወደ ኅብረቱ አባል ሃገሮች ያለቪዛ መግባት ይችላሉ። ቱርክ የአዉሮጳ ኅብረት አባል ለመሆን የሚያስችላት ድርድርም ይቀጥላል ተብሎ ነበር።

ሆኖም ግን ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ከወደ አንካራ በኩል ዋና ተደራዳሪና አጋር የነበሩት የቱርክ ጠቅላይ ሚኒስትር አኽሜት ዳቮቱግሉ ከስልጣናቸዉ የሚነሱ መሆናቸዉ መሰማቱና ፕሬዚዳንት ራቺብ ታይብ ኤርዶዋን ለቱርኮች ያለቪዛ ወደ ኅብረቱ አባል ሃገራት መግባት መፈቀድ የጠየቀዉን ሁኔታ ማጣጣላቸዉ የተደረሰዉን ስምምነት ጥያቄ ዉስጥ አስገብቶታል። የቱርክ የፖለቲካ ዉዝግብ በኅብረቱና በቱርክ ላይ ያለዉ አንደምታ በስደተኞች ጉዳይ የተደረሰዉ ስምምነትና እጣ ፈንታው በዚህ መሰናዶ የምንቃኘዉ ይሆናል።

ገበያዉ ንጉሴ

አዜብ ታደሰ