1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ህገ ወጥ የጦር መሣሪያ ንግድ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 3 2008

ከአውሮጳ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ የሚካሄደው የጦር መሣሪያ ንግድ እያወዛገበ ነው ። ብዙ ገንዘብ በሚገኝበት በዚህ ንግድ አማካይነት ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ከሚገባው የጦር መሣሪያ የአብዛኛው መጨረሻ ሶሪያ መሆኑ አሳስቧል ።

https://p.dw.com/p/1JeuC
Syrien Aleppo Panzer
ምስል picture alliance/abaca/B. el Halebi

አውሮጳና ጀርመን

በዚህ ንግድ ውስጥ የምትሳተፈው ጀርመን የጦር መሣሪያዎቿ ከታሰበላቸው ዓላማ ውጭ እያዋሉ ነው የሚል ወቀሳ እየተሰነዘረባት ነው ።ወደ መካከለኛ ምሥራቅ ሃገራት የጦር መሣሪያ ከሚሸጡት መካከል የባልካን ሃገራት የሚባሉት በርካታ ምሥራቅ አውሮጳ ሃገራት ይገኙበታል ። በዓመት እስከ አንድ ቢሊዮን ዩሮ እንደሚያስገኝ ከሚገመተው ከዚህ የጦር መሣሪያ አብዛኛው ወደ ሳውዲ አረብያ ነው የሚገባው ። ሆኖም የጦር መሣሪያዎቹ ሳውዲ አረብያ እንደማይቆዩ መጨረሻቸው ወይም መድረሻቸው ሶሪያ መሆኑን አንድ የምርመራ ዘገባ አጋልጧል ።የባልካን ሃገራት የጦር መሣሪያ ንግድ ላይ አትኩሮ የምርመራ ዘገባ ያቀረበው BIRN የተባለው የጋዜጠኞች ቡድን እና የተደራጀ ወንጀል እና የሙስና ዘገባ ፕሮጀክት በእንግሊዘኛው ምህጻር OCCRP ለዓመታት የጦር መሣሪያ የሚጓጓዝበትን መስመር ሲያጠኑ ነበር ። በዚሁ ጥናት መሠረት በጦርነት በተመሰቃቀለችው ሶሪያ ውስጥ በአሁኑ ጊዜ በሺህዎች የሚቆጠሩ AK 47 ጠመንጃዎች ፣አውቶማቲክ ጠመንጃዎች አዳፍኔዎች ፣ የሮኬት ማስወንጨፊያዎች ፣ ፀረ-ታንክ መሣሪያዎች እና T -55 እና T-72 የተባሉ ታንኮች ይገኛሉ ። ከነዚህ የጦር መሣሪያዎች አብዛኛዎቹ ከምሥራቅ አውሮጳዎቹ፣ ከቦስንያ፣ ከቡልጋርያ ፣ከክሮኤሽያ ፣ከቼክ፣ ሪፐብሊክ ፣ ከስሎቫኪያ ከሞንቴኔግሮ ከሰርብያ እና ከሩማንያ ይመጣሉ ተብሎ ነው የሚታመነው ።ሶሪያ የሚገቡትም በቀጥታ ሳይሆን በተጠማዘዘ መንገድ ነው ። መጀመሪያ በአውሮፕላና ወደ ሳውዲ አረብያ ፣ ዮርዳኖስ ፣ ዩናይትድ አረብ ኤምሪቶች ወይም ቱርክ ይወሰዳሉ ከዚያ ደግሞ ወደ ጦር ቀጠናዎች ይወሰዳሉ ። ይህ የጦር መሣሪያ ንግድ 1.2 ቢሊዮን ዩሮ የሚወጣ መሆኑ ነው የሚነገረው ። የቢርን እና የኦ.ሲ.ሲ.አር ፒ የምርመራ ጋዜጠኞች እነዚህን መረጃዎች ያፋ ያደረጉት የጦር መሣሪያዎች የውጭ ንግድ ሰነዶችን እና የተመ ዘገባዎችን ካገላበጡበመቶዎች የሚቆጠሩ ጦር መሣሪያዎቹ የሚጓጓዝባቸውን የመርከብ የአየር መስመሮች የሚያሳዩ ቪድዮዎችን ካጠኑ እና የጦር መሣሪያ ውሎችን ከመረመሩ በኋላ ነው ።ለምሳሌ ቢርን እና ኦ.ሲ.ሲ.አር ፒ የደረሱበት በጎርጎሮሳዊው 2013 የተገኘ አንድ ሚስጥራዊ ሰነድ የሰርብያ የመከላከያ ሚኒስቴር ባለሥልጣን የጦር መሣሪያዎቹ እንዴት ከሳውዲ አረብያ ወደ ሶሪያ እንዲሄዱ እንደሚደረግ ያሳያል ። ከዚህ ሌላ በእቃ ጫኝ አውሮፕላኖች ጉዞ ላይ ላይ በተካሄደ ጥልቅ ምርመራ አውሮፕላኖች ከ70 ጊዜ በላይ የግጭት ቀጣና ወደ ሆኑ አካካቢዎች በመመላለስ ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ የጦር መሣሪያ ያቀብሉ እንዳቀበሉ መረጃዎች አግኝተዋል ። የጀርመን የግራዎቹ ፓርቲ ይህን መሰሉን የጦር መሣሪያ ሽያጭ በጥብቅ ይቃወማል በጀርመን ምክር ቤት የፓርቲው ቃል አቀባይ አግኒስዝካ ብሩገር የምርመራ ዘገባ ሥራውን አድንቀዋል ። ምክንያቱም የምርመራ ዘገባው የጦር መሣሪያዎቹ ከሳውዲ አረብያ ወደሶሪያ እንደሚሄዱ ማረጋገጥ ችሏልና
«ጋዜጠኞቹ ከባልካና ከመካከለኛው እና ከምሥራቅ አውሮጳ ሃገራት ስለሚካሄደው የጦር መሣሪያ ንግድ ያወጡት ዘገባ የሚያስመሰግናቸው ነው ።ጋዜጠኞቹ የሰጡት መረጃ ንግዱ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ እና ሃላፊነት የጎደለው የደህንነት ፖሊሲ እንዳለ የሚያሳይ ነው ። »
ሮበርት ስቴፋን ከጎርጎሮሳዊው 2011 እስለ 2014 በሶሪያ የአሜሪካን አምባሳደር ይህን መሰሉ የጦር መሣሪያ ንግድ የሚቀነባበረው በአሜሪካን የስለላ ድርጅት CIA መሆኑ እና ንግዱም በቱርክ እና በባህረ ሰላጤው ሃገራት በኩል እንደሚካሄድ ለቢርን እና ለኦ.ሲ.ሲ.አር ፒ ተናግረዋል ።ርሳቸው እንዳሉት የመጀመሪያው የጦር መሣሪያ ጉዞ ወደ ማይጠረጠር ሃገር ሲሆን ፣ከዚያ በኋላ ደግሞ ወደ ጦርነት ቀጣናዎች እንዲሄድ የሚደረገው ። ቢርን እና ኦ.ሲ.ሲ.አር ፒ የመረመሩዋቸው የእቃ ጫኛ አውሮፕላኖቹ ሰነዶች በሺህዎች የሚቆጠር ቶን ክብደት ያላቸው እቃዎች ስለተጓጓዙባቸው አውሮፕላኖች ምንም መረጃ የለም ።ለምሳሌ ከቡልጋርያ እና ከስሎቫክያ የሚሄዱ እቃ ጫን አውሮፕላኖች ምንነታቸው የማይታወቅ ጭነት ተብለው ነው እንዲበሩ የሚደረገው ።ከጦር መሳሪያዎቹ አብዛናዎቹ በ1990 ዎቹ የተመረቱ ሲሆኑ ወቅቱም ከባልካን ጦርነት መጨረሻ ጋር የተገጣጠመ ነው ።በዚህ ወቅት በባልካን ሃገራት የተበተኑት የጦር መሣሪያዎች ድንበር እየተሻገሩ ወደ ሌሎች የአውሮጳ ሃገራትም ይገባሉ ። ለምሳሌ ከአንድ ዓመት ከ8 ወር በፊት ከሞንቴኔግሮ የመጣ ሽጉጦች እና ፈንጂዎችን ጨምሮ ልዩ ልዩ የጦር መሣሪያዎችን የጫነ መኪና በጀርመንዋ ግዛት ባቫሪያ በፍተሻ ወቅት ተይዟል ።እነዚህን የመሳሰሉ የጦር መሣሪያዎች ሶሪያ ውስጥ ጥቅም ላይ ይውላሉ ። መሣሪያዎቹ የሶሪያን መንግሥት በሚወጉት ነፃ የሶሪያ ጦር በሚባሉት በሚባሉት አምጽያን ብቻ ሳይሆን ራሱን እስላማዊ መንግሥት ብሎ ከሚጠራው ቡድን እና ከአልቃይዳ ጋር ህብረት አላቸው የሚባሉ ጽንፈኛዎቹ ተዋጊዎችም እጅ ውስጥ ገብተዋል ነው የሚባለው ።ይህን መሰሉ የጦር መሣሪያ ንግድም የጦር መሳሪያ የውጭ ንግድን የተመለከቱ የአውሮጳ ህብረት ህጎችን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ብሔራዊ እና ዓለም ዓቀፋዊ ህጎች የሚጥስ እንደሆነ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታውቋል ። እነዚህ ከምሥራቅ አውሮጳ የሚሄዱ የጦር መሣሪያዎች ሶሪያ ውስጥ ለሚደርሰው ሞት እና የንብረት ውድመት ዋነኛዎቹ ምክንያቶች ናቸው እንደ ምርመራ ዘገባው ።
ወደ መካከለኛ ምሥራቅ በሚካሄድ የጦር መሣሪያ ንግድ ወቀሳ ከሚቀርብባቸው ውስጥ የጀርመን መንግሥት አንዱ ነው ። በጀርመን ምክር ቤት በተለይ የግራዎቹ እና የአረንጓዴዎቹ ፓርቲ ቀውስ ውስጥ ወዳሉ አካባቢዎች እና ወደ ጦርነት ቀጣናዎች ጦር መሣሪያ መላኩን ይቃወማሉ ። መንግሥት በዚህ ጉዳይ ላይ በተለይ ከአረንጓዴዎቹ ፓርቲ በኩል ለቀረበtt,ለት ጥያቄ በሰጠው መልስ የችግሩ ምንጭ በሆኑት በበልካን ሃገራት የተበተኑትን የጦር መሣሪያዎች ለመሰብሰብ እና ለማውደም የበኩሉን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አስታውቋል ። መንግሥት እንደሚለው ለዚሁ ተግባር 1 ሚሊዮን ዩሮ በየዓመቱ ወጪ ያደርጋል ። ተቃዋሚዎች ግን ይህ በጣም አነስተና ነው ሲሉ ይከራከራሉ ። በጀርመን ምክር ቤት የግራዎቹ ፓርቲ ቃል አቀባይ አግኒስዝካ ብሩገር ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ በተለይ ጀርመን ወደ ሳውዲ አረብያ የጦር መሣሪያ መላኳን አጥብቀው ተቃውመዋል ።
«የጀርመን መንግሥት በበነዚህ ጉዳዮች ላይ ግልፅነት እንዳለ ለማሳመን ይሞክራል ። ለምሳሌ ሁልጊዜ በጆሮዮ ላያ የሚያቃጭለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር መግለጫ ነው ። ይኽውም ሳውዲ አረብያ አካባቢውን የምታረጋጋ ምልህቅ ስለሆነች በመልካም ግንኙነታችንን መቀጠል ።አለብን ያሉት ነው ። በሳውዲ አረብያ የሰብዓዊ መብቶች ይዞታ ተባብሷል ፤አልተሻሻለም ። »
የጀርመን ምክትል መራሄ መንግሥት እና የኤኮኖሚ ጉዳዮች ሚኒስeር ዚግማራ ገብርዬል ይህን አይቀበሉም ። ጋብርየል በቅርቡ የወታደራዊ ጦር መሣሪያዎች የውጭ ንግድ ዘገባ ባቀረቡበት ወቅት የጀርመን የጦር መሣሪያዎች በህገ ወጥ መንገድ ለሌሎች ተላልፈው እንደሚሰጡ በግልጽ ተናግረዋል ።ከመካከላቸውም መጨረሻቸው የጦርነት ቀጣና የሆነ እንዳሉም ተናግረዋል ።በዚህ የተነሳም ጀርመን የጦር መሣሪያዎች ወደ ውች ከተላኩ በኋላ ያደረሰቡበትን ቦታ የመቆጣጠር ሥራ ተግባራዊ እንደሚሆንም ጋብርየል አስረድተዋል ።
«ያ ማለት የጦር መሣሪያዎቹ ተቀባዮች የተላኩት መሣሪያዎች በትክክል መድረስ ያለባቸው ቦታ መድረስ አለመድረሳቸውን የጀርመን ባለሥልጣናት እዚያ ተገኝተው እንዲያረጋግጡ መስማማት ይኖርባቸዋል ። ይሁን ብሩገር ይህ ቁጥጥር ገና አልተጀመረም ሲሉ ይተቻሉ ። ከዚህ ሌላ ጋብርየል ከዚህ ቀደም ተግባራዊ ይሆናል ያሉትን የጦር መሣሪያ የውጭ ንግድ ህግም ተግባራዊ ማድረግ ተስኗቸዋል ይላሉ ።

Syrien Kämpfe um Palmyra
ምስል picture-alliance/dpa
Syrien Waffenlieferungen
ምስል picture alliance/AP Photo
Kampfpanzer Leopard 2
ምስል picture-alliance/dpa
Symbolbild Deutschland Waffenexporte Leopard 2 A6
ምስል picture-alliance/dpa

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ